>
5:13 pm - Sunday April 19, 7503

ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ መርሻ በወያኔ ካድሬዎች ወደ ጃፓን ተመልሶ እንዳይሄድ ታፍኗል

የጀርመን ድምፅ የአማርኛው ክፍል የጃፓንና የሩቅ ምስራቅ ዘጋቢ እንዲሁም የዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተእራካሪ የሆነው IFJ(international freedom  of Journalist)ጃፓን ኢታባሺ ከሚገኘው ጋር በመተባበር የሚሰራው  ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ መርሻ  ወደኢትዮጵያ ከመሄዱ በፊት በአንቅፅ 61-2 Immigration Control and Refugee Recognition  መሠረት የጃፓን  መንግሥት ፍትህ ሚኒስቴር ሠርተፍኬት ሰጥቶት በአገሪቱ ውስጥ ለ10 አመት ያህል ከቆየ በዋላ በጃፓን አገር ባደረገው ቆይታ ሙያውን ግዴታውን ህሊናውን ሳይሸጥ በሚያቀርባቸው ሚዛናዊ ሪፖርቶች የተለያዩ ተፅዕኖዎች ቢቀርቡበትም ሁሉንም ነገር በመቁዋቁውም ሲያቀርብ ከቆየ በዋላ ተጽዕኖዎች እየበረከቱበት በመሄዱ ለጀርመን   የሚያቀርበውን ዘገባ ለጊዜው በማቆም ወደ መጽሐፉና ወደ ኤሌክትሮኒስ ሚዲያ ላይ በማቶከር ጥናት ሲያደርግ ቆይቶ ይህንንም አገር ቤት ገብቶ  ሲተገብር ቆይቱዋል። አምስት መጽሐፍቶችን በተለይም በሩቅ ምስራቅ ላይ የሚያተኩር «አውሬው»፤«ውሸትና ጥንቁልና»፤«ሦስትዮሽ»፤«ውጋት» እና «ባቢሎን» የሚባል መጽሐፍቶችን ውጣ ውረድ በበዛበት ሁኔታ በማሳተም በአንባቢያን ዘንድ መጽሐፍቶቹ ተቀባይነት ሲያገኙ። ከዘመነ  አክሱም ጀምሮ የሰራው የቀን አቆጣጠርና የሂሳብ ቀምር በቤተክርስቲያን ሰዎችና በሙሁራኖች ዘንድ ተቀባይነት ቢያገኝም በአንዳንድ የወያኔ ካድሬዎች አማካይነት ባይዋጥላቸውም ሳይወዱ በግዳቸው እየመረራቸው መቀበላቸው ታውቁዋል።

ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ መርሻ ከዚህ ሌላ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት ዙሪያ ጥናት አድርጎ እንዲያቀርብ የዓለማቀፍ ድርጅቶች በጠየቁት መሰረት ጋዜጣ አዙዋሪዎች፤ ጋዜጠኞችን፤ ጋዜጣ እንዳይሰሩ ተከለከልን ያሉ ወገኖችን፤አንባቢዎችን በማናገር የ2017 የፕሬስ ሪፖርቱን ኢትዮጵያ ውስጥ የፕሬስ ነፃነት እንደሌለ አስረግጦ አቅርቡዋል።ከዚህ ሌላ በሶሻል ሚዲያ ላይ አፈናእንዳለና ኢንተርቤቶች በአብዛኛው በትግራይ ተወላጆችና በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ የወያኔ ምልምሎች የሚሰራ እንደሆነ አብዛኛው የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎችም እነሱ እንደሆኑ የሱን ጨምሮ በአብዛኛው  የተዘጋባቸው እንደሆነ የተከፈቱት የቴሌቪዥን ጣብያዎች ሰርበር እየተስጣቸውና እየተደገፉ እንዲሰሩ መደረጉን እሱ  በውድ ዋጋ በመግዛት ከ30 ሺህ ብር በላይ ግብር ከፍሎ ከፕሬስ ሰዎች ጋር ለመክፈት ያሰበው የቴሌቪዥን  ጣቢያ ስላልተሳካለት ለነዚህ የቲሊቪዥን ጣቢያ ለመሸጥ ያሰበውም ሳይሳካለት ምንም ነገር እንዳይሰራ ማስጠንቀቅያ ጭምር የተሰጠው መሆኑም ታውቁዋል።

ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ መርሻ  ወደ ጃፓን ማርች 1 ቀን በእኛ የካቲት 22 ቀን ለመብረር በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጋር በመነጋገር አሳቸው በአቀረቡት አማራጭ መሰረት ሁሉን ነገር አሙዋልቶ ያስገባ ቢሆንም የጃፓን መንግስት የሰጠው ሰርተፍኬት የኢማባሲው ሰራተኞች የሆኑት ኢትዮጵያውያን ለማን እንደሚሰሩ እንኩዋን ባልታወቀ ሁኔታ ወደ ወያኔ መንግስት በማድላት የስደተኛው ሰርተፍኬት ሕጋዊ አይደለም ሌላ ጊዜ መታወቂያ ቀይር ሌላ ጊዜ  እንደገና ኢምግሬሽን ሄደክ ሰው ያምልክትል በማለት የጃፓንን ሕግ የሚጣረዝ ተግባር በመፈሰም ላይ መሆናቸውን በመገንዘብ ከጃፓኖች የስደተኞች ማህበርና ከጠበቃው ጋር የተነጋገረ ቢሆንም ኢሜሎችናና የስልክ ጥሪዎችን ቢያደርጉም እስካውን ድረስ ምላሽ አለማግኘቱ ታውቁዋል።

እንዲያውም የስልክ ጥሪዎች በሚያደርግበት ወቅት በመታፈኑለአምስቲ፤ለሂማን ራይት ዎች፤ለስፒጂ፤ለአይፍጂ መላኩም ታውቁል።ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ መርሻ  ሚስቱንና ልጁን ትቶ ውደ ኢትዮጵያ የሄደው አንድ የጃፓን ፕሮፌሰር የኢምግሬሽን ኦፊሰሮችን አስፈቅደውለት ያለምንም ችግር ወደ ኢትዮጵያ የገባ ቢሆንም  ከቤተሰቡ ተለይቶ ቤተሰቢም ሆነ እሱ ችግር ሲገጥመው የጃፓን መንግስት እስካውን ዝም ማለቱ አብዛኛውን ሰው አስገርሙዋል። በኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ አምባሳደሮች ዱርዬዎች እንደሆኑና  የሚሰጣቸውን  ጊዜ ሴተኛ አዳሪዎችን እያመሹ ኢማባሲያቸው ውስጥ ለሊት 8 ሰዓትና 9 ሰዓት የዘው በመግባት እንደሚወሰልቱ፤በማጅራት መቺዎች የተዘረፉ፤ ጭፈራ ቤት የሚያመሹ የኢምባሲ ሰዎች መኖራቸውን የዓይን እማኞች ይገልጻሉ።

Filed in: Amharic