>

የምርኮ ሥነ ልቦና እንደ አባዱላ  (ሙሉቀን ተስፋው)

በHBO እየተዘጋጀ የሚቀርብ Game of Thrones የሚባል ረዥም ተከታታይ የታወቀ ሙቪ አለ፤ ሙቪው Westeros እና Essos በሚባሉ ምናባዊ አገሮች የንግሥና ሥልጣን ታሪክን የሚያትት ቢሆንም ታሪኩ በትክክል በአውሮፓውያን የሥልጣን ሽኩቻ የተከናወነ ይመስለኛል፡፡
ከዚህ ሙቪ አንድ እንደ አባዱላ ዓይነት ሪክ የተባለ ገጸ ባሕሪ አለ፡፡ የማእረግ ስሙ ግሬይጆይ የተባለ የልዑላን ቤተሰብ ነበር፡፡ ነገር ግን ራምሴ የተባለ ክፉ ጠላት ማረከው እና ሪክ የተባለ የዳረጎት ስም ወጣለት፡፡ እነዓባይ ፀሐዬ ምናሴን ማርከው አባደሉ እንዳደረጉት ማለት ነው፡፡
ግሬጆይ ወደ ሪክ እስቀሚቀየር ድረስ በርካታ ሒደቶችን አልፏል፡፡ አስተሳሰቡ ጭምር ተኮላሽቶ በትክክል እንደ ሪክ እንዲያስብ ሆኖ ነው የተፈጠረው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን የግሬይጆይ እህት ጦር አሸነፈና ግሬይጆይን ከታሰረበት ሒዳ እህቱ ‹‹ግሬይጆህ እንሒድ ቶሎ በል›› አለችው በናፍቆት፡፡ እሱ ግን ‹‹እኔ ግሬይጆይ አይደለሁም ሪክ ነኝ፤ የራምሴ አገልጋይ ነኝ አልሔድም›› አላት፡፡ እህቱ እርሱን ለማዳን ጎበዝ የሚባሉት ተዋጊዎቿን ማስገደሏ ቆጫት ለማይበጅ ሰው፡፡
የአባ ዱላ ታሪክ ከሪክ ጋር ተመሳሳይ ነው፤ እነ ለማ መገርሳ የግሬይጆህ እህትን ሚና ቢይዙም እርሱ ግን ከጌቶቹ ጋር ነበር፡፡ አባዱላ ትክክለኛው የምርኮ ሥነ ልቦና ማሳያ ወደፊትም እንደምሳሌ ሆኖ ሊገለጽ የሚችል ነው፡፡
በሳይኮሎጂ  Operant conditioning የሚባል ቲዎሪ አለ፤ በOperant conditioning የኤሌክትሪክ ንዝረት ያለበት ሽቦ ላይ አንድ ውሻ እንዲሔድ ሲደረግ የሚረገጠው ሁሉ ስለሚነዝረው በመጨረሻ የረዳትአልባትና የአቅመቢስነት ስሜት ያዳብራል፡፡ በዚህም ተመሳሳይ የሆነ ነገር ላይ (ኤሌክትሪክ ንዝረት የሌለው ቢሆንም) ከተደረገ ውሻው ሁሌም የሚሰማው አቅመ ቢስነት ይሆናል፡፡
እነ አባዱላ በዚህ መልኩ ኮንዲሽን የተደረጉ ናቸው፡፡ አባዱላ እነ አባይ ፀሐየን ሲመለከት የሚሰማው ያኔ ሲማረክ ያደረሱበት ችግር ነው የሚታሰበው፤ ዘመን ቢለወጥም ያ ሞመንት ግን በኅሊናው ዝንተ ዓለም ተጽፎበት ይኖራል፡፡ እናም ከሕወሓት ውጭ ምንም ሊያደርግ አይችልም፡፡ በአጪሩ እስትንፋስ ያለው የሕወሓት አሸንጉሊት ነው ማለት ነው፡፡ እናስ በዚህ ሰው ላይ እንዴት ቂም መያዝ ይቻላል?,
Filed in: Amharic