>

ሀበሻዋ ሆስተስ በሜሪላንድ ግዛት " በአሲድ  ተቃጠልኩ" ስትል እሪታና ጩኸት ታሰማለች (አርአያ ተስፋማሪያም)

በዲሲ አሰቃቂ ድርጊት በኢትዮጵያዊቷ ወጣት ላይ ተፈፅሟል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ በበረራ አስተናጋጅነት 12 አመት ሰርታለች። የ35 አመት እድሜ የምትገመተው ይህቺ ወጣት አሜሪካ – ዲሲ ከመጣች 2 አመት ሆናት። በአንድ የሀበሻ ሬስቶራንት ተቀጥራ ትስራለች። ያለፈው ሳምንት ስራ አምሽታ ወደ ቤቷ ታመራለች። ሩም ሜቷ ከሆነው ኢትዮጵያዊ ወጣት ጋር አለመግባባት ይፈጠራል። “አዘጋጅቶ ሳይሆን አይቀርም” የተባለውን አሲድ በጠይሟ ቆንጆ እህታችን ፊት ላይ ይደፋል። “ተቃጠልኩ” ስትል እሪታና ጩኸት ታሰማለች። ወጣቷ በአሲዱ በጣም ተጎድታለች። በተኛችበት ሆስፒታል ከአንድ የቅርብ ዘመድ በስተቀር ሌላ ጠያቂ እንዲጎበኛት አልፈቀደችም። የተፈፀመባት የጭካኔ ድርጊት እጅግ አሳዛኝ ነው! ይህን ምን ይሉታል!?..

ተጠራጣሪው ተይዟል
በሜሪላንድ የ35 አመቷ ወጣቷ ኢትዮጵያዊት ላይ አሲድ የደፋው በክሪ አብደላ ድርጊቱን ፈፅሞ ከተሰወረ ከሁለት ቀን በኋላ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ማረጋገጥ ተችሏል። በተደፋባት አሲድ ከፊቷ እስከ ጡቷ ድረስ ክፉኛ የተጎዳችው የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ አስተናጋጅ በአሁኑ ወቅት በዋሽንግተን ሴንተር ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ይገኛል። ትላንት ከሰመመን የነቃች ሲሆን በደረሰባት ጉዳት ሰው እንዲጠይቃት አልፈቀደችም። ከፍተኛ ህክምና እንደሚያስፈልጋት ተጠቁሟል። በወጣቷ የተፈፀመው ድርጊት የአሜሪካ ሚዲያዎች መነጋገሪያ ከመሆኑ በተጨማሪ በተለያዩ አካላት መደነገጥን ፈጥሯል። ወጣቷ በከፍተኛ ደረጃ ተጎድታለች።
( በፎቶው ድርጊቱን ፈፅሟል ተብሎ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው በክሪ አብደላ)

ወጣት ሰላማዊት ተፈራ ቀልቤሳ 

በሜሪላንድ ግዛት በአሲድ ጉዳት የደረሰባት ናት። ቤተሰብ ጉዳዩን ስለሰማ ማንነቷን በምስል በማስደገፍ ይፋ ተደርጓል። ይህቺ ምስኪን ወጣት የደረሰባት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ..ያልተቋረጠ ህክምና ያስፈልጋታል። የሰላማዊት የኢሚግሬሽን ስታተስ የሚፈለገውን ህክምና ለመሸፈን ኢንሹራንሱ አያስችልም ብቻ ሳይሆን አይታሰብም። በአካልም፣ በመንፈስም ጉዳት የደረሰባት ወጣት ሰላማዊትን በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ድጋፍ ሊያደርጉላት ይገባል። በቅርብ ጤንነቷን ከሚከታተሉት አጎቷ ጋር በመነጋገር የምትረዳበትን መንገድ በይፋ የሚገለጽ ይሆናል። ጎፈንድ አካውንቱ ..በራሷ በተጎጂዋ አሊያም በአጎቷ ስም ይሁን የሚለው እንደተወሰነ ይፋ ይደረጋል።

Filed in: Amharic