ስለሺ ሙላቱ
ደርቤ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ጀግና አባል መሆኑን አስቀድመው ያወቁ አይመስለኝም።አውቀው ቢሆንማ በጉራጌ ዞን ያሠለፉትን ታንክ በእጥፍ ባሠለፉ ነበር። የወያኔ ሠራዊት ከ27 ዓመታት በፊት የረሡት የደርቤ ክንድ እንደገና ሲያርፍባቸው ምን እንደተሠማቸው መገመት ለማንም ዳገት አይሆንም። ግዳይ ሊጥል የሄደው ጭዳ ሆኖም የጀግናውን የሚፋጅ እጅ ለመያዝ አልታደለም። የገደለውን ገሎ ቀሪውን አቁሰሎ የደም ውርስ አለበትና የጀመረችውን ጣቱን ለመጨረሻም ትዕዛዝ ሠጣት ምላጩን ሣበችው። ይሕኛው ግና አፈሙዙ ከጠላት በተቃራኒው ነበር። እናም የቴዲን የክብር ሞት ተጋራ። እራሡን ለኛ ቤዛ አድርጎ ነፍሡ ወደ ገነት ሥጋው ወደ ተሠራበት ወደ አፈር ሊመለስ ተሠነባበቱ።
እዚሕጋ ልብ እንበል ትናንት ለሀገሩ ተዋድቆ ሣለ ያ ሁሉ በደል ሲፈፀምበት “የተዋደቅኩለትና የላከኝ ሕዝብ ዞር ብሎ አላየኝም” በሚል ዝም አላለም። ዛሬም ለዚሕ ትንታግ ትውልድ ምሣሌ ሆኖ በክብር ተሠዋልን። ከኛስ ምን ይጠበቃል? መቼ እነደምንሞት ቀነ-ገደብ ላልተሠጠንና ለማይቀር ሞት እንደዚህ የክብር ሞት መሞት ሕያውነት ነው። ጀግናው ደርቤ ሀገራችንን ከትግራይ ወራሪ ነፃ ለማውጣት ይታገል እንደነበረ አስረጂ የሚያሻን አይመስለኝም። አንድ ቀን የሆነው ሊሆን እንደሚችል ስለሚያውቅም ነው ያለቀጠሮ የሞት አለያም የቁም ሥቃይ ደግሠውለት እንዲታደም የጋበዙትን ተዘጋጅቶበት ያስተናገደው። አኩሪ ገድል። ሁሌም ሲዘከር የሚኖር ለቤተሠብና ለወገን የሚያኮራ ተግባር ከውኖ መሞት ታላቅነት ነው። እርግጥ ነው ሀዘኑ ልብ ይሠብራል። ነፍስ ይማር፤ ለቤተሠቡም ፈጣሪ መፅናናቱን ይስጥ። ምንጊዜም አንረሳሕም።
ዘራፍ ዘራፍ
እታይቤት ያላችሁ እላይቤት ያላችሁ
ወያኔን ዘረረው ጀግናው አባታችሁ
አባቴን ሸኙልኝ ወርቁን አጥፍችሁ
የተጋሩ ልጆች አገደፉላችሁ
እልልበል ጎጃሜ ከግድህ በሃላ አይመጣም ሰፈርህ !
አላወቀም ነበር የዛ የቆፍጣናው የበላይ መሆንህ!!
ታውቅበታለህ በፍቅር ለመጣ እግዳ መቀበል
ማኛውን አሲዘህ ማር ቂቤውን ቀድተህ
ሊገልህ ሲመጣ እድህ እያደረክ ትቀጣልኛለህ!!!
የወንድማችን ደም በከንቱ ፈሶ አይቀርም።
ሞት ለትግራይ ነፃ አውጪ!!