>

አባዱላ Team ለማን ለማስበላት ቆርጦ ተነስቷል

የዘንዶው አፍ ተከፍቶ እየጠበቃቸው ነው

ዋዜማ ራዲዮ:- የለማ ቡድን ለመበላትም ሆነ ነፃ ለመውጣት የመጨረሻው ሰአት ላይ ነው።የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) የተወሰኑ ከፍተኛ አመራሮች በመጪው ቅዳሜ ከሚካሄደው የገዥው ግንባር ኢህአዴግ የስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ራሳቸውን ለማግለል እየመከሩ ነው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የፀቀበት ሂደት ትክክል አይደለም፣ የዓዋጁን መፅደቅ ተከትሎ በኦሮምያ ክልል አስተዳደራዊ መዋቅር ላይ ያነጣጠረ የማፍረስ ዘመቻ እየተደረገ ነው፣ ዛሬም የፌደራሉ መከላከያ ሀይል ሰላማዊ ስልፈኞችን መግደል አላቆመም የሚሉና ሌሎችም ቅሬታዎችን ያቀረቡ አመራሮች ከቀሪ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ጋር ለመሰብሰብ ፍላጎት የለንም ብለዋል። 

በአፈጉባዔ አባዱላ ገመዳ፣ በኦሮምያ ክልል ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ እና በኦህዴድ ሊቀመንበር ዶ/ር አብይ አህመድ መካከል ከፍ ያለ የአቋም ልዩነት የታየ ሲሆን፣ ከፍተኛ ካድሬዎችና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የደህንነት ክፍሉ ከፍተኛ ክትትል እያደረገብን ነው ማለታቸውን በማውሳት፣ ጨፌ ኦሮምያም ሆነ ኦህዴድ በጉዳዩ ላይ ወጥ አቋም መያዝ አለበት የሚል ሀሳብ አቅርበዋል።
ከመድረክ በመሸሽ ችግሩን መፍታት አይቻልም የሚል ሀሳብ ያላቸው አባዱላ ገመዳ በዚህ ሳምንት ሁለት ረጃጅም ስብሰባዎችን ከኦህዴድ አመራሮች ጋር ማድረጋቸውን ለጉዳዩ ቅርብ ነን ያሉ ምንጮች ነግረውናል።

Filed in: Amharic