>

በነ አቡነ ማቲያስ የከሰረችው ኢትዮጵያ እነ ቄስ ቶሎሳን አግኝታለች! (አቻምየለህ ታምሩ)

ይንቃታል ሞትን ነፍሱን ያከበረ፣ 
ለልፋጭ ለእባሽ ለሆዱ ያልኖረ፤ 
ይህ ግጥም የተቋጠረው  ለቄስ ቶሎሳ  አይነት የቁርጥ ቀን  አገር አውሎች ነው። የየትኛውንም ሃይማኖት ተከታይ ቀልብ የሚስበው የቄስ ቶሎሳ ንግግር በኢትዮጵያ ምድር የሃይማኖት አባት  በጠፋበት ዘመን ያውም ከመዲናችን አዲስ አበባ የተላለፈ የሕዝብ ድምጽ ነው።
የፋሽስት ወያኔ  የሃይማኖት ክንፍ  በሆነችው  «የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስስቲያን» አቦ ወንበር  በአቡነ ማቲያስ የከሰረችው  ኢትዮጵያ  ቄስ ቶሎሳ ጉዲና የመሰሉ  ውድ  ልጆችን ያገኘች ይመስላል! የኢትዮጵያን ያለፉት 44 ዓመታት ችግሮች ከጥግ እስከ ጥግ ላጤነ  የአባታችን የቄስ ቶሎሳ ጉዲና ታሪካዊ ንግግር የመጪው ዘመን ኢትዮጵያ ፍኖተ መርህ  መሰረትና   የዛሬውና የመጭው   የትውልድ  ድምጽ  መሆን እንደሚገባው  የሚያምንበት ይመስለኛል!  ለአባታችን ለቄስ ቶሎሳ ጉዲና ረጅም እድሜና ጤና  ይስጥልን!
Filed in: Amharic