>

ስዩም ተሾመ በኮማንድ ፖስቱ ታፍኖ ተወስዷል

እሙ ሰላም 
መቶዎች ፈቶ ሽዎችን ለማሰርና ትንፋሽ አግኝቶ የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም የ”አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ”ን በለመደው ማጭበርበር በተወካዮች ምክር ቤት አጽድቄያለሁ ያለው የህወሀት አገዛዝ ኮማንድ ፖስት ብሎ ባቋቋመው የአፈና ቡድን ዛሬ ደግሞ ታዋቂውን ጸሃፊና የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህር ስዩም ተሾመን አስሮ ወደ አዲስ አበባ ወስዷል።
 ስዩም ኢትዮጵያ  ውስጥ ስላመንክበት ነገር መናገርም ሆን መጻፍ ዋጋ እንደሚያስከፍል በማንም ሳይሆን በራሱ ላይ በደረሰው ግፍ እና መከራ ጠንቅቆ ቢረዳውም ያለአንዳች የፍርሀት ስሜት ያመነበት ጉዳይ ሲጽፍና የስርአቱን አስከፊነት በተባ ብእሩ በመከተብ ይህን ፋሽስታዊ መስተዳደር ሲወቅስ እንዳንዴም እንደ ምሁር ቀናውን መንገድ ሲያመላክት ቆይቷል።
 ጎበዝ እንቃ ይህ ገደል አፋፍ ላይ የቆመ ገዥ ቡድን ጥቂቶችን እየለቀቀ ብዙዎችን ያስራል ቶርቸር ያልተደረገን ቶርቸር ለማድረግ የማሸማቀቅ ስራ ይሰራል። ይሁሉ የክፋት አዙሪታቸው በስነልቦና ምሁሮቻችንን  ለማዳከም  የሚደረግ ጦርነት ነው።  በአንድነት እንቁም ። ልጅ ውለህ ግባ መባል በቀረበት  ሰአት ሌላ አናውራ ።እናት በር ዘግታ ከፋች አጥታለች ልጅ መገድ ላይ መጫወት ቀርቷል። ምን እስከሚሆን እጠብቃለን♥ ያማል ያማል!!!
Filed in: Amharic