>

የ«ያ» ትውልድ ነገር!  (አቻምየለህ ታምሩ)

በ«ያ» ትውልድ ትርክት መሰረት  የአማራ ባህል ተጭኖባቸው በዋለልኝ «የብሄር፣ ብሔረሰቦች እስር ቤት» ውስጥ ገብተው የብሔር ጭቆና ከተካሄደባቸው ብሔረሰቦች መካከል  ዋለልኝ መኮነን  በጽሑፉ እንደ ተጨቋኝ «ብሔሮች»  አድርጎ ካቀረባቸው ብሔረሰቦች መካከል ኦሮሞና ወላይታ ዋናዎቹ ናቸው።
ዋለለኝ መኮነን  በኦሮሞና በወላይታ ላይ የአማራ ባህል ተጭኖባቸዋል በማለት ተካሄደ ያለውን  የማንነት ማጥፋት ፖሊሲ ለማሳየት ያቀረበው ምሳሌ በኦሮሞና ወላይታ ላይ ሸማ ተጭኖባቸዋል የሚል ነበር። እስቲ የዋለልኝን ድንቁርና ለጊዜው  እውቀት ነው እንበልና በደርግና በፋሽስት ወያኔ ከአማራ የባህል ጭቆና  ተላቀቁ የተባሉትን ኦሮሞዎችና ወላይታዎች ከድህረ «የአማራ ጭቆና» በኋላ የሚለብሱትን እስመልከት።
ከዚህ ጽሁፍ ስር ሶስት   ፎቶዎች ታትመዋል። አንደኛው ፎቶ  የኦሮሞ አባገዳዎች ባህላዊ ልብሳቸውን ለብሰው በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ከኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ሲገናኙ የሚያሳይ ነው። ሁለተኛውና ሶስተኛው  ፎቶዎች   ደግሞ  ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬን የሚያሳዩ ናቸው። የኦሮሞ አባገዳዎችና ኃይለ ማርያም ከነ ባለቤቱ የለበሱት  ልብስ  ዋለልኝና ያ ትውልድ  በኦሮሞና በወላይታ ላይ ተጭኖባቸዋል የተባለውን  ሸማ ነው።
ያ ትውልድ እንዳለው ሸማን አማራ በወላይታና ኦሮሞ ላይ የጫነው ልብስ ከነበር ዛሬ ብሔሮች፣ ብሔሮችና ሕዝቦት ነጻ ወጥተዋል በተባለበት ዘመን
በኦሮሞ አባገዳዎችና  በወላይታዎቹ  በኃይለ ማርያምንና በወይዘሮ ሮማንን ላይ የአማራን ሸማ ማን ጭኖባቸው ነው የለበሱት? እስቲ ይህንን ጥያቄ  ሸማን አማራ  በወላይታና ኦሮሞ ላይ የጫነው ባህል ነው ብላችን የታገላችሁ የ ያ ትውልድ አባላት ይህንን ጥያቄ መልሱልን? እናንተ ከአማራ የብሔር ጭቆና አላቀቅናቸው ያላችሁን ብሔረሰቦች እንዴት ብለው ነጻ ካወጣችኋቸው በኋላ ጨቋኝ ያላችሁት አማራ ጫነባቸው ያላችሁትን ሸማ እንዴት እንዲህ በፎቶው ላይ እንደሚታየው የራሳቸው ባህላዊ ልብስ ሊያደርጉት ቻሉ?
የኦሮሞ አባገዳዎችና ወላይታዎቹ  ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ሮማን ተስፋዬ እንዲህ  ሸማ  ለብሰው  የሻዕብያው  ተላላኪ(*)  ዋለልኝ መኮነን  ቢያያቸው ኖሮ አማራ ጭኖባቸው ነው የለበሱት ይለን ነበር 🙂  በእውነት ግን የኦሮሞ አባገዳዎችንና  ወላይታዎቹን   ኃይለ ማርያም ደሳለኝንና ሮማን ተስፋዬን  ሸማ የለበሱት ማን ጭኖባቸው ነው? 🙂
(*) ዋለልኝ መኮነን  የሻዕብያ ተላላኪ እንዴት እንደነበር ጓደኛው ዶክተር አያሌው መርጊያው  «እናት ሀገር ! የኢሕአፓ እንቆቅልሽ» በሚል ርዕስ ጽፈው በቅርቡ ባሳተሙትን ባለ 1100 ገጽ መጽሐፍ  ውስጥ አንብቡ። ዶክተር አያሌው መርጊያው  ከአባዲና ፖሊስ ኮሌጅ  እንደተመረቁ  ኤርትራ ውስጥ የፖሊስ አዛዥ  ሁነው ይሰሩ በነበረበት ወቅት ዋለልኝ መኮነን  ኢሳያስ አፈርቂን ሊያገኝ  ወደ አስመራ ሲሄድ  እንዴት አድርገው ሽፋን ሰጥተው እንዳሳለፉት  በመጽሐፋቸው ያተቱበትን ታገኙታላችሁ።
ከዚህ በተጨማሪ ሻዕብያ  የሚሰራው ለኢትዮጵያ ነው  ካልተባለ  በስተቀር  ዋለልኝ መኮነን  የሻዕብያ ቅጥረኛ ስለመሆኑ  ተጨማሪ ማረጋገጫ  ለሚሻ  ዋለልኝ መኮነን የተገደለበትን  ሻዕብያ  የመራውና ያባቀነባበረውን  የኢትዮጵያን አውሮፕላን ጠለፋ ታሪክ  ከኢሕአፓው አምበል ከክፍሉ ታደሰ «ያ ትውልድ» መጽሐፍ ያንብብ። ክፍሉ ታደሰ እነ ዋለለኝ መኮነን  በሻዕብያ  መሪነትና አቀነባባሪነት ያካሄዱትን የኢትዮጵያ  አውሮፕላን የጠለፋ ታሪክና እነ ዋለልኝን ይመራ የነበረውን የሻዕብያን ጠላፊ ታሪክ  ከነ ስሙ  አስቀምጦታል!
Filed in: Amharic