>

የኢትዮጵያ መንገዶች ከነዳጅ ቦቴ ነጻ ሆነዉ ዋሉ (እስራኤል ሰቦቃ)

በአጠቃላይ ሀገሪቷ በነዳጅ ቦቴዎች ላይ የተጣለው ነዳጅ ማቆም ኣድም ተግባራዊ ሆኗል።
ዋነኛዉን የሀገሪቷ የንግድ መስመሮች ከቦቴ ነጻ ሆነዉ መዋላቸዉን ከያቅጣጫዉ የሚደርሱ ዘገባዎች ያመለክታሉ።
ከነዳጅ ተኣቅቦው ጋር በተያያዘ መልኩ በርዕሰ መዲናይቷ ቤንዚን የሚሸጠዉ በውረፋ ሲሆን ኣንዳንድ ነዳጅ ማዲያዎች 5 ሊትር ብቻ ላንድ መኪና እንደሚሸጡ ለማወቅ ተችሏል(ይህ እንግድህ ኮታ መሆኑ ነዉ)።
ርዕሰ መዲናይቷ ሸገርም ሳትወድ በግድ አድማዉን የተቀላቀለች ሲሆን ቦቴዎቿን መንገድ ዳር ደርድራ ለሃገሪቷ ባለስልጣናት በጸጥታ ከቄሮ ጋር ሰልፍ መያዟን ኣሳይታለች።
በሌላ በኩል ደግሞ ከፋኖ የተገኘዉ ዜና እንደሚያመለክተዉ እየተተገበረ ያለው የነዳጅ ማዕቀብ ከሱዳን መተማ፣ ጎንደር፣ ባህርዳርና አዲስ አበባ ባለው አገር አቀፍ መስመርም ተግባራዊ ሆኗል። ማዕቀቡ ከታወጀ ከትናንትና ጀመሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከሱዳን ተነስተው ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት የሞከሩ የነዳጅ ቦቴዎች በትናንትናው እለት የመተማና አካባቢው ሕዝብ ባደረገው የተቀናጀ ትግል ወደ መጡበት ተመልሰው እንዲሄዱ አድርጓል። የነዳጅ ማዕቀቡ ከጀመረ እስካሁን ድረስ መተማን ያለፈ አንዳች የነዳጅ ቦቴ የለም።
እስካሁን በተጠናከረው ሪፖርት መሰረት አንዳችም ጉዳት በሰውም ሆነ በንብረት ላይ አልደረሰም። ይህም የሚያመለክተዉ የነዳጅ ቦቴ ባለንብረቶችና ሾፈሮች የተሰጠዉን መመሪያ በተገቢዉ መንገድ ተግባራዊ በመድረጋቸዉ ነዉ።
Filed in: Amharic