>
5:31 pm - Tuesday November 12, 6543

ታላቁ የጥበብ ሰው ሁለቱ ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጭ ሆኑ! የወገኖቹን ድጋፍ ጠይቋል፡፡

ሸገር ታይምስ መጽሄት
በሀገራችን ስማቸው ቀድሞ ከሚነሱ የመድረክ ፈርጦች አንዱ የሆነው ጋሽ ፍቃዱ ተክለማርያም ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጭ በመሆናቸው በከፋ ህምም ላይ እንዳለ እና የህዝቡ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ተገለጸ፡፡
  ላለፈው አንድ ወር በቤተሰብ እና ወዳጅ እገዛ ህመሙን ለመቆጣጠር መሞከሩን የገለጹልን የድጋፍ ኮሚቴ አስተባባሪዎቹ በቤተሰብ በኩል አስፈላጊውን የህክምና ክትትል እና ኩላሊት ለመለገስ ጭምር የተሞከረ ቢሆንም ለአርቲስቱ የሚያስፈልገው የኩላሊት እና የደም ሁኔታ ከፍቃደኞቹ ጋር ሊገጥም ባለመቻሉ  ሙከራው እንዳልተሳካም ነው ለሸገር ታይምስ የተናገሩት፡፡
 ከህክምናው አቅም ጠያቂነት እና ከተፈላጊው ኩላሊት ካለመገኘት አንፃር በቤተሰብ ብቻ ተይዞ የነበረውን ይህን ጉዳይ አማራጭ በማጣት ለህዝብ ይፋ ያደረጉት አርቲስቱ እና ቤተሰቦቹ በአስተባባሪዎች በኩል በነገው እለት   ከረፋዱ 4፡00  ጅምሮ በአፍሮዳይት ሆቴል ለመገናኛ ብዙሃን  አካላት መግለጫ እንደሚሰጡም ነው ለሸገር ታይምስ የጠቆሙት፡፡
 እባክዎት ይህን ሼር በማድረግ በርካቶች ጋር አንዲደረስ በማድረግ ይተባበሩን!!!
Filed in: Amharic