>

"ከነ ክብሬ እንድሞት ፍቀዱልኝ?" (አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም)

ፍቃዱ አባይ

ለተወዳጁ አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም የህክምና ርዳታ ትብብር እንዲደረግ ተጠየቀ።
ዛሬ ረፋድ ላይ በአፍሮዳይት ሆቴል የአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያምን የኩላሊት ህክምና ትብብር እንዲደረግ የተዋቀረው ኮሚቴ ለመገናኛ ብዙሐን ባለሙያዎች እንደገለጠው ፍቃዱ ተ/ ማርያም አሁንም አልጋ አለመያዙንና በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል ብለዋል።ሁለቱ ኩላሊቶቹ ስራ ማቆማቸውን ተከትሎ በቤተሰብ ረገድ የኩላሊት መስጠት ሙከራዎች መከናወናቸውንና ያለመሳካቱን እንዲሁም የህክምና ወጭውን በመሸፈን የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ እንደቆየ ገልጠዋል።በጤና ችግር ላይ የሚገኘው አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም እርዳታ እንዳይጠየቅለትና ችግሩን በራሱ ጥረት እና በእምነቱ ለመዳን ባለው ጽኑ ፍላጎት አንዲሁም መስጠት እንጂ መቀበልን በማይወደው ባህሪው የተነሳ ለኮሚቴው “ከነ ክብሬ እንድሞት ፍቀዱልኝ፤”ማለቱንና ኮሚቴው ግን አርቲስቱ ያለበትን የጤና እክል በመገንዘብ ጥያቄውን እንዳልተቀበለው ተነግሮናል።አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ስራዎችን የሚያሳይ አጭር ዘጋቢ ፊልም በቴዲ ስቱድዮ አማካኝነት ተዘጋጅቶ ታይቷል።ከዚህ በተጨማሪም የኩላሊት ህመም መነሻዎች እና አርቲስት ፍቃዱ ያለበትን የኩላሊት ህመም ደረጃ የህክምና ባለሙያ አስረድተዋል።
በዚህም መሰረት ለአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም የኩላሊት ልገሳ የሚያደርጉ ስዎች እንደሚያስፈልጉት አንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጎዛ ቅርንጫፍ የባንክ ቁጥር 1000239345488 በአርቲስት መሰረት መብራቴ፣በአርቲስት መቅደስ ጸጋዬ እንዲሁም በአቶ ሳምሶን ብርሀኔ ስም ጊዜአዊ አካውንት ተከፍቷል።
አንዲሁም በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በGoogle.Go Fund me. please help save Fekadu. ላይ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻል ተነግሮአል።ሰዎችም ከተሰጡት አካውንቶች ውጭ በመሰል መልኩ ሊከፈቱ ከሚችሉ አሳሳች መረጃዎች እንዲጠነቀቅም ምክር ተላልፏል።ጊዜአዊ ኮሚቴው 7 የጥበብ ባለሙያዎች እና በጎ ፈቃደኞች እያስተባበሩት ይገኛል።በጋዜጣዊ መገለጫው ላይ ከመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች በተጨማሪም የአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም የስራ ባልደረቦች ታድመዋል።ለፍቃዱ ተ/ማርያም የኩላሊት ልገሳ ለማድረግ ለሚፈልጉ +251 911 86 43 96 ወይም +251 913 02 34 44 በመደወል መረጃዎችን ለማግኘት እንደሚቻልም ተነግሮአል።የፍቃዱ ተ/ማርያም የደም አይነቱ A ሲሆን የኩላሊት ልገሳ ለማድረግ የሚችሉ ስዎች A ወይም O የደም አይነት ያላቸው ስዎች ናቸው።
Filed in: Amharic