>

ህወሀት ቁርጥ ያለ አቋሟን አሳውቃለች "መካላከያውና ደህንነቱን በእኛ ሆኖ ቀሪውን ተመራጩ ጠ/ሚ ይምራው"

አባኮስትር በላይ
ያፈተለከ የስራ አስፈጻሚው ውሎ:-
በደረሰን አስተማማኝ የውስጥ መረጃ እንደሆነ የኢህ አዴግ ስራ አስፈጻሙሚ ውዝግብ እንደሚከተለው ይጠቃለላል፡፡
በመጀመርያዎቹ ሁለት ቀናት ጠቅላይ ሚ/ሩን እጅ በማውጣት እንዲመረጥ ሀሳብ ቀረበ ለማ መገርሳ እጩውን በደንብ አውቀንና ገምግመን ካልሆነ እንዲሁ ከፓርቲ ማንነቱ ሳይ’ጠራ መምረጥ የለብንም በሚል ፉርሽ አደረገው፡፡
ቀደም ሲል ቀድመው በወጠኑት መሰረት በረከትና አዲሱ ምርጫው እስከሰኔ ይለጠጥ የሚል ሀሳብ አቀረቡ ቆፍጣናው ለማ አልተስማማም፡፡ ቀጥሎም ግምገማው ተካሄደ ዶ/ር አብይ ቁልፉ ሰው ሆነ፡፡ በመጨረሻም መግለጫ ለመስጠት በተዘጋጁበት ሁኔታ ህወሀት ወገቤን አለች፡፡የጠቅላይ ሚ/ሩ ስልጣን መገደብ አለበት፡፡መካላከያውና ደህንነቱን በህወሀት ሆኖ ቀሪው ላይ ተመራጩ ጠ/ሚ ይምራው እንደማለት ነው፡፡ ይህ ከይሲ ሀሳብም በኦህዴድ ከሸፈና የእሮቡ የስራአስፈጻሚው ፕሬስ ገለጻ ተሰረዘ፡፡እሮቡ ማምሻውንም የመከላከያ ሚ/ር የህወሀቱ ደብረጽዮን እንዲሆን ሀሳብ ቀረበ፡፡ይህም በኦህዴድ በድጋሜ ውድቅ ሆነ፡፡
ሀሙስ እለት ደመቀ መኮንን መከላከያውን እንዲጠረንፍ ሀሳብ ቀረበ፡፡ ይህም ሊሳካ ስላልቻለ የኦህዴዱ ወርቅነህ ገበየሁ እንዲሆን ሀሳብ ቀረበ የተከበሩ ለማ መገርሳም ይህ ግለሰብን የማመረጥ ወይም ብሄርን የማየት ጉዳይ አይደለም፡፡ይህ ስልጣን ማለትም አዲስ ካብኔ የመሾም እና የማደራጀት ሥራ በህገመንግስቱ መሰረት የሚመረጠው ጠቅላይ ሚኒስቴር ስልጣን ብቻናብቻ መሆን አለበት አዲዎስ ሲል ለማ የማይናወጥ አቋሙን በአውሬዎች ተከቦ እንቅጩን አስቀመጠ፡፡
ስብሰባው በዚህ አላለቀም የፊታችን ማክሰኞ ቀጣዩን አቀርባለሁ፡፡
የህዝብ ትግል ያሸንፋል!!
Filed in: Amharic