>

የኢትዮጵያ ሠራተኞች! ለፍፃሜው ትግል!! (ዶ/ር ታደሰ ብሩ)

ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት የተጠናወተን የዘር ፓለቲካ የኢትዮጵያ ሕዝብን በሥራና ሙያ በኩል እንዳናገኘው እንቅፋት ፈጥሮብናል። አሁን ይህንን  እንቅፋት መወጣት ያለብን ወቅት ላይ ነን ብዬ  አምናለሁ።
ዛሬ ኢትዮጵያ ከገጠማት ችግር ወጥታ በብሩህ መንገድ እንድትጓዝ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ሚና  ወሳኝ ነው።  “የኢትዮጵያ ሠራተኛ”  ሁሉንም ዘውጎች፣ ሀይማኖቶችና ሁለቱንም ጾታዎች ያሰባስባል። ሁሉን አንድ የሚያደርጋቸው ኢትዮጵያዊነታቸውና  ሠራተኛነታቸው ነው።  ከዚህ የኅብረተሰብ ክፍል ብዙ እንጠብቃለን።
በተለይከዚህ በታች የዘረዘርኳቸው ኮርፓሬሽናችና ካምፓኒዎች ውስጥ የምትሠሩ የኢትዮጵያ ሠራተኞች የአገር ኃላፊነት ያለባችሁ መሆኑን እንዲሰማችሁ ጥሪ አደርጋለሁ።
1. የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ 
2. የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን፣
3. የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን፣
4. የብረታ ብረትና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን፣ 
5. የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ 
6. ኢትዮ ቴሌኮም፣ 
7. የኢትዮጵያ ፓስታ አገልግሎት፣
8. ባንኮችና ኢንሹራንሶች፣
9. የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን፣ 
10. የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ኮርፖሬሽን፣ 
11. የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ፓርክ ኮርፖሬሽን፣
12. የኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን፣ 
13. የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን፣ 
14. የኢትዮጵያ ማዕድንና ጋዝ ምርቶች አቅርቦት ኮርፖሬሽን፣ 
15. የኢትዮጵያ የማዕድን ሥራዎች ኮርፖሬሽንና 
የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ እያበቃለት ነው። “እያበቃለት ነው” ማለት ግን አበቃለት ማለት አይደለም። የኢትዮጵያ ሠራተኞች በግንባር ቀደምትነት ያልተሳተፉበት ትግል ዲሞክራሲያዊ ማድረግ ውጤታማና ዲሞክራሲያዊ ማድረግ ከባድ ነው። የትግሉ መሪዎች መውጣት ያለበት ከዚሁ ከሠራተኛው ማኅበረተሰብ ነው።  የኢትዮጵያ ሠራተኛ የሕዝባዊ እምቢተኝነት መሪ መሆን አለበት።
ለወደፊቱ ሊኖሩን ከሚገብ የፓለቲካ ፓርቲዎች ቢያንሱ አንዱ “የሠራተኛ ፓርቲ”  Labour Party  ቢሆን ብዬ እመኛለሁ።
Filed in: Amharic