>

የጭቆና ወጭ (ገረሱ ቱፋ)

በኢትዮጵያ  ውስጥ ያሉ ሶስት ሺህ ቦቴዎች በኮማንድ ፖስት የሚታጀቡ ከሆነ የሚያስከትለው ከፍተኛ የነዳጅ፣ የውሎ አብል እና የምግብ ውጭ ሌላ ጣጣ ሳያመጣ አይቀርም።
አንድ ቦቴ በሁለት ፕካፕ የምታጅብ ከሆነ ስድስት ሺ ፕካፕ ከሆነ ምን ያህል እንደሚፈጅ መገመት አያዳግትም።
ሌላው አንድ ፕካፕ አምስት አምስት ሰው የሚያስፍልግ ከሆነ ለአንድ ቦቴ አስር ወታደር ያስፈልጋል ማለት ነው።
 ለሶስት ሺ ቦቴ ስልሳ ሺህ ወታዳር ያስፈልጋል ማለት ነው። ለአንድ ወታደር በቀን መቶ ሃያ እንኳን  ብከፈል ለስልሳ ሺህ ወታደር በቀን ስባት ሚሊዮን ብር ያሰፈልጋል ማለት።
 እዚህ ላይ የነዳጅ ዋጋ ከተጨመረብት ወጭው ከፍተኛ ነው የሚሆነው። በየቀኑ እየተሸመደመደ ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ይህንን ተሸክሞ የሚሄድ ከሆነ በቅርብ ጊዜ ቀውስ ውስጥ እንደሚገባ ነዋይ ገብረአብ ስራውን ካላቆመ በሰተቀር ብመክራቸው ጥሩ ነበረ።
ይህንን ሁሉ የጭቆና ውጭ ከሚያወጡ ቀላል የሆነውን የህዝቦች የነፃነት ጥያቄ መመለሱ ይጠቅማቸው ነበረ።
 ግን የመጨቆነ ሱስ የያዘው ሰው አቅሙን ስለማያውቅ ገድል እስክገባ ይቀጥላል።
ለጨቋኙ ሃይል ወደ ገደል የሚያደርገውን የቁልቅለት ጉዞ መልካሙን እንመኝለታለን።
Filed in: Amharic