>

"..ኣንተ ብኣዴን ....! ..." ኣዲሱ ስድብ (አምዶም ገ/ሥላሴ)

በመቐለ ከተማ ኣዲስ ስድብ ተፈጥራለች። እቺ ስድብ ለማንኛውም በህወሓት መሪዎች ላይ የብቃት ጥያቄ ያነሳ ሰው እየተሰጠች ያለች ቃል ናት።
 በትግራይ የተለየ ሃሳብ ያንፀባረቀ፣ ከባድ የህዝብ ጥያቄ ኣንስቶ ተቀባይነት ያገኘ፣ የልማት ይሁን የመልካም ኣስተዳደር ጥያቄ ያነሳ ሰው ኳዂቶ(ኣቋቅማ) ሲወዱም ዓረና እየተባለ እንዲሸማቀቅ ይደረግ ነበር።
ህወሓት ኣርባዋ ባሳለፈችበት ወቅት ኣቶ በረከት በኣቶ መለስ የትግል ድርሻ ኣስመልክተው ባቀረቡት “..የብኣዴን ኣቋም የሚያንፀባርቅ ..” (እሳቸው ጥናታዊ ፅሁፍ ያሉት) ፅሁፍ ካቀረቡ በሗላ ግን ነገሮች ተቀያይረዋል።
ኣቶ በረከት በፅሑፋቸው ኣቶ መለስ ከእንግዲህ በትግራይ መሬት ከመቶ ኣመት በሗላ ካልሆነ በስተቀር እሳቸው የመሰለ (የሚተካ) መሪ ዳግም የማይፈጠር መሆኑ ተነበዩ። ይቺ ኣገላለፅ ለህወሓት ካሁን በሗላ ኣገሪቱ የመምራት ብቃት ያለው ሰው የላቹምና ለኛ ተውልን የሚል መልእክት ያዘለች ነበረች።
በመድረኩ ነበሩ ያተባሉት ኣቦይ ስብሓት “..በረከት ያለውን ሙሉ በሙሉ ኣልቀበለውም፣ ከፈልግሁ ሺዎች ከመልስ የበለጡ እኔ የማውቃቸው ወጣቶች ማቅረብ እችላለው።..”  በማለት በእጃቸው እያቃለሉ የኣት ስሙት መልእክታቸው ኣስተላለፉ።
ኣቶ ኣርከበ ዕቑባይም “..እኛ እዚህ ያደረሰን ህዝብ ነው። ትግሉ የመራን የትግራይ ህዝብ ነው። በግለ ሰው ወይም በቡድን ተመርቶ ለድል የበቃ ትግል ኣላውቅም..”  የሚል መልእክት በማስተላለፍ ኣቶ በረከትን “..የት ነበርሽ እኛ ኣይደለም ወይ መንገድ መሪ እንድትሆኚ ያደራጀንሽ ..” ኣይነት መልእክት ኣስተላለፉላቸው።
የመለስ ራኢ የሚል መፎክር የያዙት ግን ብኣዴኖች ብቻ ኣይደሉም። በትግራይም ጭፍራ ያላቸው መሆኑን ይታወቃል።
ወደ ዋናው ሃሳቤ ልመልሳቹና ኣንተ ባዴን …!  የሚል ቃል በመቐለ ስድብ ኣድርገው የሚጠቀሙበት ሰዎች እየበረከቱ ናቸው። ለነገሩ በፌስቡክም “…ብኣዴን ሲፏቁ ጉንበት 7 ናቸው..”  የሚል ዘመቻ እንደተጀመረ እያነበብን ነው።
የኣማራ “..እንገንጠል..”  የሚል ጥያቄም የብኣዴንና ህወሓት ልዩነት የወለደውና “..ብኣዴን ትግሉ የተለየ ኣቅጣጫ ሊያስይዘው ፈልጎ ያነሳው ሃሳብ ነው..”  የሚሉ ሰዎች ኣሉ።
በወልቃይት ያለው ኣለመረጋጋትም የብኣዴን እጅ ኣለበት እየተባለ ይወራል።
ለማንኛውም በመቐለ ከተማ የህወሓት ኣመራሮች ኣቅመ ቢስነት ያወራ ሰው “…ኣንተ ብኣዴን…” የሚል ስድብ እየወረደበት ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።
ብኣዴን የህወሓት የቦክር ልጅ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በትጥቅ ትግል  ከነበረው ሚና በላይ እነ ስየና እነ መለስ ልዩነት በፈጠሩበት ወቅት የመለስ መቺ ሃይል መሳርያ በመሆን የተጫወቱት ተራ ይልቃል።
ለብኣዴኖች የምለግሰው ምክር የነብር ጭራ ኣይያዙ ከያዙም ኣይልቀቁ ነው። ብኣዴኖች በኣቋማቸው ከፀኑ ህወሓት ኣፍርሶ በቦታቸው ሌላ ድርጅት ይተክልላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
‘…ኣንተ ባዴን …!”
 ነፃነታችን በእጃችን ነው..!
IT IS SO…!
Filed in: Amharic