>

የትግራይ የበላይነት አለ! የለም! ለእኛ የተሰጠን አጀንዳ! - ትግራይ የግል ኢትዮጵያ የጋራ! የነሱ አጀንዳ(መንግስቱ ሙሴ)

ሰሞኑን በየቦታው የህወሓቷ ጠባብ ቡድን መሪወች አይን ባወጣ የኢትዮጵያዊነት ጠብታ በሌለው የእኔ የሚሉትን ሕዝብ እየሰበሰቡ የተዘጋጁ እና የእንነሳሳ ቅስቀሳ ጀምረዋል። በግልጽ ለ27 አመታት የታየው የትግራይ ጠባብ ቡድን የቅኝ አገዛዝ በሚመስል ያካሄዱት ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ ውስጥ አንዱ እና ከባዱ ወንጀል ሕዝቡን እኛ እነሱ (ትግሬ እና ቀሪው በሚል) የከፋፈሉት ሀገር በአንድ ቆሞ ስለአንድ ሀገር እንዳያስብ አድርጎ የእነርሱን የከፋ የውስጥ በቅኝ ግዛት የማስቀጠል አላማ አራማጅ አጋዥ እንዲሆን አርገዋል። ጺወናዊት እስራኤል በፍልስጤም እና በአረቦች መሀል ተጠናክራ እና እራሷን አጠናክራ የመቀጠልን ምሳሌ የህወሓት ጠባቦች ሙሉን በመውሰድ ኢትዮጵያ የጋራ/ትግራይ የግል በሚል የአውሮፓ የቅኝ ገዥወች መንፍስ ስልጣኗን በወታደራዊ ኅይል እያስቀጠለች ለመሆኑ አሌ ተብሎ የሚካድ አልሆነም። ግን ከየት መጡ የማንላቸው በጎን የትግራይ የበላይነት አትበሉ። የትግራይ የበላይነት የለም። ትግራውያንን ያገለለ ፖለቲካ ልክ አይደለም እያሉ በእነርሱ ሴረኛ መጣጥፎች እንድንደነክር ይፈልጋሉ።
እውነታው ግን በቅኝ ግዛት ስር ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማንነቱን ተገፎ። የኢትዮጵያዊነት ብሄራዊ ዜግነትን ተነጥቆ ተለያይቶ እና ተበታትኖ ለትግራይ ጠባብ ቡድን እንዲመች ሆኖ የተሰራ የፖለቲካ አሻንጉሊት ከሆነ ለሦስት አስርታት ጥቂት ፈሪ የቀረው እውነታ ሆኗል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ማንንም ሆነ የትኛውንም ዜጋ የዜግነት እና የአብሮነት እሴቱን ያልተጋፋ። አሁንም አብሮ መኖርን ከፍቅር ጋር የቀጠለ እና ያስቀጠለ አንዳንድ ተቀዋሚ ነን ወይንም በሉን ባዮች እንደሚሉት የሌላውን በዘር እና በማንነት ተጋፍቶ የዘር ማጽዳት ያደረገ ሳይሆን የዘር ጽዳቱ እና ማጥፋቱ በግፍ እየተካሄደበት ያለ ለመሆኑ በጀርመን ፍራንክፈርት በጌታቸው እረዳ እና በአዲስ አበባ በአንድ የህወሓት ፖሊት ቢሮ አባል የትግራይን ተወላጆች ሰብስበው ያስተላለፉት መልእክት አፋሽ አጎንባሾች ከሚሉት የተጻራሪ መሆኑን አሳይተውናል። ተጋሩ በቀጣይ ህወሓት ለምትወስደው ጸረ አማራ ጸረ ኦሮሞ ዘመቻ እንዲዘጋጁ አፍ ሞልተው የተናገሩት ተራ አባላቱ ሳይሆን የህወሓትን ተሀድሶ ተቀብለናል ብለው በአዲስ የተመረጡት የፖለቲካል ቢሮው መልእክተኞች ናቸው።
በእርግጥ ነው ዛሬ እነዚያ አንባ ገነንነትን ተቃውመው በጽናት የወደቁ የትግራይ ታጋዮች አልነበሩም ማለት አይደለም። ግን ያተለውጦ በመሀል ሀገር በህወሓቷ ጥይት ዜጎች በየቦታው ሲረፈረፉ በነጻ ሀገር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በተለይም የተማሩት የወንድማማችነት ስሜት አደባባይ ወጥተው አለማሳየት እጅግ የሚያሳዝን ተውኔት ሆኖ ሳለ። የዘፈን አዳማቂ በሚመስል የትግራይ የበላይነትን እንደመታገያ ሊወስዱ የፈለጉ ጸጉር ሰንጣቂ አድርባዮችን ስናይ ባናፍር እናዝናለን ማለት ነው።
 ይህ ለትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር የመጨረሻው ጊዜ ይመስላል። አመፁንና ክህደቱን ደደቢት እንደጀመረው ሁሉ ሞቱንም ትግሬዎቹን ይዞ ሊሞት ይፈልጋል። የትግራይን ሕዝብ አስታጥቆ ከ100 ሚልዮን በላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሊዋጋ ይፈልጋል። በዙሩያው ያሰፈራቸው ጥቂት ግብረ-በል አማሮች፣ኦሮሞችና የደቡብ ጎሳዎች በመጨረሻ እንደማያዋጡት ከእነርሱ ይልቅ እርሱ የተረዳው ይመስላል። ስለዚህም ከመሰናበቱ በፊት “የአብረን እንሰናበት እሪታውን “የትግሬ የበላይነት”  ለዝንተ ዓለም ተጠብቆ እንዲኖር ይወተውታል። ዙሪያውን ከበውት ለሚርመጠመጡ ትግሬ ያልሆኑ ባሪያዎቹም “በተጠንቀቅ እንዲቆሙና ለመጨረሻው ፍልሚያ እንዲዘጋጁ ያዛል።  ለእነዚህ አታሞዎች እያቀረበ ያለው ትእዛዝም ተቀባይነት አገኘ አላገኘ በስልፉ እፊት አድርጎ ከሁዋላ በጥይት እየነዳ የመጀመሪያው ገፍት ቀማሽ እንደሚያደርጋቸው እሙን ነው። ከዚህ ቀደም በኤርትራ ጦርነት እንዳደረገው ማለት ነው። በኤርትራ ጦርነት ከተስዋው 85000 የኢትዮጵያ ጦር ሰንት ትግሬ ሞተ? ስንት ኦሮሞስ ስንት አማራስ ሞተ? የሞተው ዘማች ቤተ ሰቦች መርዶ ስላልተነገራቸው ቁጥሩ ተለይቶ ባይታወቅም ከአህያ ቀጥሎ በተቀበረ ፈንጅ ላይ ረግጠው እንዲስዉ ከተገደዱት ውስጥ አንድም ትግሬ እንዳልነበር ተረጋግጡዋል። የትግሬ አቀንቃኝ የሆኑ ኦሮሞዎች፣አማሮችና ደቡቦች እንዲሁም አፋሬችና ቤንሻንጉሎች የሚጠብቃቸው እድል ይኽው ነው። በውትድርናው ክፍል ደግሞ ይህ አይኑን ያፈጠጠ ጥርሱን ያገጠጠ ሃቅ ነው። ወታደሩ የኢትዮጵያ ወታደር ነኝ ካለ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደህንነት መቆም እለበት እንጂ ለጥቂት አምባ ገነን ገዥዎች ልእልና ሊሰዋ አይገባውም። በአሁኑ ጊዜ ወያኔ በሕዝብ ላይ እያንዣበበ ያለው እልቂት እንዲታገድ  “የሽግግር መንግስት” እንዲመስረት በተባበሩት መንግስታት የሚታዘዝ ሃይል ጣልቃ እንዲገባና ሕዝቡን እንዲታደግ አንዳንድ የአፍሪካ መንግስታት መጠይቅ መጀመራቸው ሰሞኑን ተሰምቷል። ይህም በዓለም የኢትዮጵያ ወታደር ለሕዝብ ያለው ታማኝነት አጠራጣሪ መሆኑን ያሳያል። ያሳዝናል። ነገር ግን ሃቁ ይኸው ነው። ወታደሩ ለጥቂት የትግሬ መኮንኖች ታማኝ ሆኖ ሞያሌ ላይ ሕዝብ ላይ በመተኮስ አያሌ ስዎች ከመሞታቸው በላይ ከ30000 ሰው ያላነስ ይጠብቀኛል በሚለው ሠራዊት እምነት አጥትቶ ወደ ጎረቤት አገር ተሰዷል። ከዚህ በላይ ለኢትዮጵያ ሠራዊት ምን እዓይነት ሃፍረት ይገኛል? የገዛ ወገኖቹን ገደለ። የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት እራሱን ሊመረምር ይገባል? “እንዴት እኔ እያለሁ ከተመድ የተውጣጣ ሠራዊት  ወገኖቼን ከእልቂት ሊያድን ይመጣል?” ብሎ እያንዳንዱ ወታደር እራሱን ሊጠይቅና ሚናውን ሊያስተካክል ይገባል።  ድህጣን ትግሬ አብዛኛውን ኢትዮጵያውያን በሃይል ልታንበረክክ አትችልም! ቅጥር ትግሬ-ያልሆኑ ጸረ-ሕዝብ ሲቭልና ወታደሮች ከቆሙላት ግን መስዋእቱን ሊያበዙት ይችሉ ይሆናል። በመጨረሻ ግን ሕዝብ ማሸነፉ አይቀሬ ነው።
“የሕዝቡ ጥያቄ የሽግግር መንግስት አሁኑኑ” ነው!
ለሁሉም የጌታቸው እረዳን የፍራንክፈርት የዝግ ስብሰባ ላደመጠ አሁንም ትግራይ እና ኢትዮጵያ ብለው ጦርነቱን ለማስቀጠል እንዲህ አይነት ዲስኩር ለእኛ ለሚሉት ሲሰብኩ ከሌሎቻችን በላይ ሊያሳስባቸው የሚገባ ለትግራይ ምሁራን መሆኑን ማሰብ እና ይህች የጋራ ሀገራችንን ወደ አጣብቂኝ የከተታትን ዘረኛ አንባ ገነን ቡድን ወግድ ብሎ መነሳት ከሁላችንም በላይ ለነሱ ሊሆን በተገባ። ይህን አዳምጠው ያጨበጨቡትን ሰምተን ብናዝንም ግዜው ከመምሸቱ እና ጀንበር ከመጥለቋ በፊት ኢትዮጵያዊነትን አጉልተው ለጌታቸው እና ለህወሓቷ ቡድን ማሳየት የሚገባ እነሱ ሊሆኑ ግድ ይላል።
የመለስ ዜናዊን እና የህወሓት የኤርትራ ዘር የነበራቸውን የአይናቸው ቀለም ካላማረን እናባርራለን የምትለው የታሪክ ጠባሳ ዛሬም በታሪክ ፊት ትሳለቃለች እና።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
Filed in: Amharic