>
5:18 pm - Thursday June 14, 6627

ሁሉም እየሆነ ያለው በአጋጣሚ አይደለም ብዙሀንን ገድሎ አንድን ዘር የማንሳት ፕሮጀክት ነው!!! (ሉሉ ከበደ)

 በጦር መሳሪያ ብቻ አይደለም ህውሀት ኢትዮጵያዊውን ትውልድ እየገደለ ያለው።ያውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ዛሬ ሳይሆን ጥንት የወረሩት ሀገር ህዝብ ጠንካራ የማንነት ኩራትና ክብር ያለው ከሆነ፤ ምንም የጦር ሀይል የበላይነት ቢኖራቸውም ሳይፈራ ተጋፍጦ ብዙ ጉዳት የሚያደርስባቸው ከሆነና የያዙትን ሀገር ያስለቅቀናል ብለው ከሰጉ፤  ቶሎ ብለው ትውልዱ በሞራል፤ በአካል፤ በአእምሮ  ብቃት የተሽመደመደ ሆኖ እንዲቀር ያደርጋሉ።  ምንም ማሰብ እንዲያቅተውና ተገዝቶ ለዘለአለም እንዲኖር ።
ይህንን ስልት ህውሀት ባለፉት 27 አመታት ኢትዮጵያ ውስጥ እየሰራበት ይገኛል። በቅርቡ የራሱ የወያኔው መንግስት  ጤና አውታር  ከ 12-24 አመት እድሜ ውስጥ ባሉ ወጣቶች ላይ ያካሄደውን ጥናት ይፋ አድርጎ የሚያስደነግጥ መርዶ አሰምቶናል። ለህውሀት ድል ነው። ለሀገሪቱ ግን ቶሎ መፍትሄ ካላበጀንለት የቁልቁለት መንገድ ነው። ሪፖርቱ እንደሚለው 51 በመቶ የሚሆኑት በተጠቀሰው እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች በኢትዮጵያ የአደንዛዥ እጽ ሱሰኛ ሆነዋል። (ጫት ሐሺሽ ፤ሺጋራ ) እና 46 በመቶ የአልኮል ሱሰኛ ሆነዋል። ይህ ትውልድ ጉዞው ወዴት ነው ? መጨረሻውስ ምንድነው? ከወያኔ ያስተዳደር ስልት አንጻር ይህ ለህዝብ ይፋ የተደረገ ቁጥር በብዙ የተቀነሰ መሆን ስላለበት እውነተኛው ቁጥር በኔ ግምት 70-80% ሊሆን ይችላል።
አውሮፓውያን ሰሜን አሜሪካ መተው ሲሰፍሩ የሀገሬው ነባር ዜጎች (Aboriginals) እጅግ ተፋልመዋው ነበር። ይሁንና የግድ  መሬት መቆጣጠርና ቅኝ መግዛት ስለነበረባቸው በጦር ሀይል የበላይነት የሚከፍሉትን መስዋትነት ከፍለው  አካባቢውን ሲቆጣጠሩ ፤ህዝቡን በአእምሮ የሚያላሽቁበት የረጅም ጊዜ እቅድ ነበር በቶሎ  የነደፉትት። የወረሩት ህዝብ ጤናማ ተተኪ ትውልድ እንዳይኖረው ማድረግ። እንዴት? በቂ ትምህርት እንዳያገኝ ብሎም  በእጽ እና በአልኮል ተመርዞ እንዲነፍዝ በማድረግ። ይህንን ተግባር ለማሳካትም መጀመሪያ ህዝቡን የመሽንገል ስራ ጀመሩ።  “ሀገሩ የናንተ ነው፤  እኛ ልናለማና ልናሰለጥን ነው የመጣነው” እያሉ ወንጌል እየሰበኩ ፤ እያባበሉ ፤ ያገሬው ሰዎች ስራ ቢሰሩም ታክስ እንዳይከፍሉ እንዲያውም ገንዘብ በነጻ  እያደሏቸው በዙሪያቸው ዘመናዊ መጠጥ ቤቶችን ፤ ሃሺሽ ቤቶችን  በያይነቱ  ሱቆችን በብዛት ያስፋፉ ጀመር።
ለወትሮ አሳ እያጠመዱና እያደኑ በብርድና በቅዝቃዜ እየተሰቃዩ በነጻነት ይኖሩ የነበሩት ነባር ዜጎች ፤ አውሮፓያውያኑ ያስተዋወቋቸውን መጠጦች ሲቀማምሱ ሀሺሹንም መለማደድ ሲጀምሩ ኑሮ ቀለል ያለላቸው እየመሰላቸው እጽና መጠጥ የሚያዘወትሩት የደስታ ምንጫቸው ሆነ። በቀላሉ የሚያገኙትም ሆነ። ለመግዣም የሚሆን ሳንቲም የማይቋረጥ ሆነ። አውሮፓውያኑ በዚያ አላበቁም።ልጆቻችሁን እኛ እናስተምርላችኋለን እናሳድግላችኋለን በማለት በርካታ የአዳሪ ትምህርት ቤዮችን ከፍተው የሶስት አመት ህጻን ሳይቀር ከቤተሰብ እየነጠቁ በትምህርት ስም የባሰ አእምሮአቸው የሚሽመደመድበትን ብልሃት ቀየሱ። እጽና አልኮልን በዙሪያቸው ማስፋፋትን እና ያለቁጥጥር የፈለጉትን እንዲያደርጉ መፍቀድን ጨምሮ።
ህውሀት ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ ጀምሮ ይህን አይነት ስልት ስራ ላይ እንዲውል አድርጓል።በትምህርት ተቋማት ዙሪያ ወጣቶች በሚያዘወትሩት አካባቢ፤ የጫት መሸጫ የሺሻ ማጨሻ ሱቆች ከምጊዜውም በላይ እንዲስፋፉ በመደረጉ ወጣቶች እየተማሩ ሳለ ለእረፍት ወተው ጫት ቅመው ክፍል የሚገቡበት ሁኔታ ሊፈጠር ችሏል። ማሪዋና የሚባለውን ሀሺሽ በጠላ ውስጥ እያደረጉ በብዛት ወጣቶች እንዲለምዱት ተደርጓል። ይህ ነገር ባጋጣሚ የተስፋፋ ንግድ አይደለም ። የህውሀት ደህንነት ክፍል በሚያሰማራቸው ግለሰቦችና የገንዘብ ድጋፍ የሚከናወን ትውልድን የማምከን ፕሮጀችት ነው። ኢትዮጵያዊ ባህልና ልምድን የሚያጠፉ ርካሽ ባህሎች ፤ እርቃን መደነሻ ቤቶች፥ የወሲብ ፊልም ማሳያ ቤቶች በብዛት፤ የውጭ አገር ፊልሞች ወዘተ… መስፋፋታቸው ባጋጣሚ አይደለም። የንግድ ስሞች ያካባቢ ስሞች በእንግሊዝኛ መለወጣቸው ያጋጣሚ አይደለም። ከትግራይ በስተቀር የትምህርት ተቋማት የጥራት ደረጃ መውረድ ባጋጣሚ የመጣ አይደለም።በየክልሉ “ዩኒቨርስቲ ” የሚል ስም ተለጥፎባቸው ከዚያ በዲግሪ ተመረቀ የተባለ ወጣት የሚናገረው ወይም የሚጽፈው እንግሊዝኛ መጠነኛ የቋንቋው እውቀት ላለው ሰው የሚያስደነግጥ እንዲሆን የተደረገበት ሁኔታ ያጋጣሚ አይደለም። ለውጭ ሀገር ተስኮላርሺፕ ትምህርት ከሚላኩት የሀገሪቱ ልጆች በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሆኑበት ምክንያት ባጋጣሚ አይደለም። ሌላው ቀርቶ ለኮርያ ዘማች ቤተሰቦች ኮርያ የሰጠችውን የትምህርት እድል አባቶቻቸው ያልዘመቱ የትግራይ ልጆች በብዛት እንዲወስዱት የተደረገው ባጋጣሚ አይደለም። ብዙሃኑን ገድሎ አንድን ዘር የማንሳትፕሮጄክችት ነው። ይህን ማምከን ለኢትዮጵያ ህዝብ  ለነገ የማይባል ስራ ነው።
ወደ አውሮፓውያኑ ተንኮል ልመልሳችሁና “ተሳካላቸው ወይ ?” በሉኝ።አዎ ተሳካላቸው። የሀገሬው ነዋሪ           ( አቦሪጅናሉ ) በአልኮልና በሃሺሽ ተጥለቅልቆ ፤ተመርዞ ፤ የሚታደገው በመጥፋቱ ፤ መማር የማይችል፤  መስራት የማይችል ፤  የማይወድ ማሰብ የማይችል ሆነላቸውና ቅኝ ገዢዎች ተገላገሉ። ነባሩ ህዝብ እንዳለ ደህይቶ ወልዶም የሚያደኸይ ሆነ። ዛሬ አያትና የልጅልጅ ሲጋራ እየተቀባበሉ ሲያጨሱ ማየት ሰሜን አሜሪካ ውስጥ እንግዳ አይደለም። ከኬንያ ወይም ከሱዳን የስደት ካምፕ መተን ልጆቻችንን አስተምረን ለቁም ነገር ስናበቃ ፤ የሀገሬው ነባር ህዝቦች ልጆች ከመቶ አስሩ ሁለተኛ ደረጃን አይጨርሱም።ይህን ነገር ስጽፍ እያዘንኩ ነው የምጽፈው።ልጆቻቸው ጎዳና ላይ የሚተኙ  ወስደው የሚገሏቸው፤ የሚሰወሩ ፤ሴተኛ አዳሪዎች፤ ከሃሺሽ ጋር በተቆራኘ ወንጀል የሚታሰሩ ፤በሌላም ወንጀሎች የሚታወቁ ሆነው ቀርተዋል። እርግጥ በአሁኑ ሰአት እድሉን ማንም አይከለክላቸውም ለመማር። ያኔ ነጮች የጋቷቸው መተት ከትውልድ ትውልድ ዘልቆ አፍዟቸው በበለጸገች ሀገራቸው ውስጥ ደህይተው ከማንም በታች ሆነው መኖር ይዘዋል።
ህውሀት ለኢትዮጵያ ህዝብ ያቀደውም እየሰራ ያለውም እንዲህ እንዲሆን ነው። በተለይ በአማራው ክልል ውስጥ ያደረስውን ውድቀት ማየት በቂ ነው።ዛሬ እነሱ ባመኑት መሰረት 51 በመቶ ልጆቻችን ተመርዘዋል። ይህንን ቁጥር 80 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ አድርጉት ምክንያቱም ጥፋት ሲሆን መደበቅ ካልቻሉ ብዙ አሳንሰው ይናገራሉ ። ልማት ሲሆን የሌለም ይናገራሉ ካለም ብዙ ብዙ ጨምረው ይናገራሉ ። ካልዋሹ ያማቸዋልና።
ምንድነው መፍትሄው? እንዳነቃነቅናቸው መንግለን ነቅለን ቆሻሻ ጉርጓድ ውስጥ  አርቀን መቅበር።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።
Filed in: Amharic