>

ቀጥዩ ጠ/ሚኒስቴርና አደገኛው የጓዳ ውስጥ ድርድር!?! (ቬሮኒካ  መላኩ)

     የኦሮሞ አክቲቪስቶች አራት ኪሎ ምኒልክ ቤተመንግስት ለመግባት እጅግ በጣም ሻፍደዋል።  ስጋ  እንደተመለከተ ጩልሌ መንበሩን ነጥቆ ለመሮጥ ቸኩለዋል። ኦሮሞ ጠቅላይ ሚኒስትርነት አይገባውም የሚል ቅዤት የለብኝም ነገር ግን ስልጣኑን መውሰደድ ያለበት  በሀቅ ላይ በተመሰረተ  ይገባኛል ጥያቄ  ነው እንጅ  ጥሎ ማለፍ ባለበት የቆረጣ intrigue (ሴራና ተንኮል)  መሆን የለበትም።
አሁን በተጨባጭ ጆከሩ ያለው ህውሃት እጅ ላይ ነው። ህውሃት እጩ  ባለማቅረቡ ያለው 45 ድምፅ  ቀጣዩን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመምረጥ እጅግ ወሳኝ ነው ። ቴክኒካሊ የሚቀጥለውን ጠቅላይ ሚኒስትር የሚወሰነው  በህውሃት ድምፅ ብቻ ነው ማለት ነው።
ህውሃት ይሄን ጆከር እንደ ቂል ካርታ ተጫዋች እንደማያባክነው ግልፅ ነው።  በዚህም መሰረት የሚቀጥለው ጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚወሰነው እጩ ያቀረቡት  3ቱ ድርጅቶች  ከህውሃት ጋር በሚያደርጉት ድርድር ነው ማለት ነው። ይሄን ድርድር አደገኛ የሚያደርገው በህዝቦች ላይ የሚደረግ ቁማር ጨዋታ በመሆኑ ነው።
ጉዳዩ እንደሚከተለው ነው 
በመርህ ደረጃ ደኢህዴን የራሱን 45 ድምፅ ለሽፈራው ሽጉጤ ይሰጣል ተብሎ ይገመታል ። ብአዴንም 45ቱ ድምፅ ለደመቀ መኮንን ኦህዴድም 45ቱን ድምፅ  ለዶክተር አቢይ አህመድ ሲሰጥ የጨዋታው ወሳኝ  ድምፅ የህውሃት 45 ድምፅ መሆነየ ነው ።
አደገኛው የጓዳ ውስጥ ድርድር የሚሆነው
1 ~ ህውሃት በድርድር ድምፁን ለኦህዴድ መስጠት ከወሰነ የድርድሩ ማጠንጠኛ  ህውሃት  ከኦህዴድ ጋር በአማራ  ህዝብ ላይ የምትደረግ አደገኛ ጨዋታ ለመጫወት በመስማማት ነው።
2~ ህውሃት ድምፁን ለብአዴን እጩ ለመስጠት ከብአዴን ጋር ተደራድሮ ከወሰነ ያ የድርድር ዋና ማጠንጠኛ የኦሮሞን ህዝብ ትግል ላይ በማሴር  ለመጉዳት  በመስማማት ነው ።
3 ~ ህውሃት ድምፁን ለዴኢህዴን ለመስጠት ከወሰነ በኦሮሞና በአማራ ላይ ጨዋታውን ለመጫወት ወስኗል ማለት ነው።
ይሄ ሂደት  ቀጣዩን ጠቅላይ ሚኒስትር በጓዳ ውስጥ ድርድር የህውሃት ሎሌ ያደርገዋል ማለት ነው።
አሁን ዘወር ዘወር ብዬ ስመለከት የኦሮሞ አክቲቪስቶች ጉዳይ የጤና አይመስልም ። አቢይ አህመድ  ምኒልክ ቤተመንግስት ሲገባ  የኦሮሞ ችግር በአንድ ጀምበር ይፈታ  ይመስል ማክላላታቸው ግራ የሚያጋባ ነው።
የስልጣን ባሮ ሜትራቸው  ከፍ እያለ  ነው ይልቁንስ ይሄን አደገኛ ሴራ በመገንዘብ  ነገሩን ችላ በማለት ለስር ነቀል ለውጥ መታገሉ ይበጃል ባይ ነኝ።
Filed in: Amharic