>

ብዛት ያለው የወያኔ ሰራዊት ተደመሰሰ! (ሙሉነህ ዬሀንስ)

♦የሞተውና ቁስለኛው ከሃምሳ በላይ ነው!
♦ብዛት ያለው ከብሬን እስከ ክላሽን መሳሪያ ተማርኳል!
ሰሜን ጎንደር 
ማክሰኞ መጋቢት 11 2010
በትናንትናው እለት ሰሜን ጎንደር ጠገዴ ወረዳ ውስጥ በደፈጣ ውጊያ ብዛት ያለው የወያኔ ሰራዊት  ተደመሰሰ። በኮንቮይ መልክ ከጠገዴ ወደ ማርዘነብ አቅጣጫ ሲጓዝ የነበረው የአጋዚ ሃይል ለጊዜው ልዩ ቦታው በማይገለፅ አካባቢ ሲደርስ በተሰነዘረበት ድንገተኛ ጥቃት መከላከል እንኳን ሳይችል ክፉኛ ተደቁሷል። የሟችና ቁስለኛው ቁጥር በጥቅሉ አምሳ ያክል እንደሚደርስ ተነግሯል። የተረፈውም እግሬ አውጭኝ ብሎ ተበታትኗል። ከብሬን እስከ ክላሽን ብዛት ያለው መሳሪያ ተማርኳል። ተወርዋሪ የደፈጣ አጥቂዎቹ ከነሙሉ ድላቸው ከቦታው ተወርውረው ተሰውረዋል። ይህ ሃይል አርማደጋ በርሃን፣ ተከዜ ተፋሰስን ይዞ አብዛኛውን ቆላ ወገራ የሚያካልል ጥቃት የሚሰነዝር በወያኔ እጅግ የሚፈራ ሃገር በቀል ሃይል ነው። ከዚህ በላይ ማለት አያስፈልግም።
የወያኔ ሰራዊት በመላው አማራ በተለይ ሰሜን ጎንደር ላይ ትጥቅ ለማስፈታት እያደረገ ያለው ሙከራ ከባድ ዋጋ እያስከፈለው ይገኛል። የወያኔን ተንኮል ቀድሞ የተረዳው መሳሪያ ታጣቂ ገበሬ በየጎበዝ አለቃው ተደራጅቶ ጠላትን እየቀጣው ነው። በዚህ ሰሞን ሮቢት አርማጭሆ የተመዘገበውን ድል ማስታወስ በቂ ነው። ጥሪቱን አሟጦ የገዛውን የድንበር መጠበቂያና የህልውና ዋስትናውን መሳሪያህን አውርድ የተባለው ህዝብ በወያኔ የእብሪት ድርጊት እልህና ቁጭት ውስጥ ገብቶ በሙሉ ወኔ ገጥሟል። ከበርሃው ጀግኖች የመጣው መልእክት ህዝባችን ከጎናችን አይለየን የተቃጣብንን ጦርነት አክሽፈን እናሸንፋለን ብለዋል።
ግዚአብሔር ለተገፉ ሃይልና ድልን ይሰጣል!
ድል የህዝብ ነው!
ሙሉነህ ዮሃንስ
Filed in: Amharic