>

የወልዲያ ጉዞ አንድምታ:- እርማችንን ልናወጣ አልመጣንም! (ተመስገን ደሳለኝ እስክንደር ነጋ አንዷለም አራጌ)

ቴዎድሮስ አለማየሁ
ሀዘናችሁ የብቻችሁ አይደለም፣ ህመማችሁን ብቻችሁን አትታመሙ፣ ድካማችሁንም ለብቻችሁ አትደክሙም፣ ይልቅስ የፈሰሰው እንባ እስኪደርቅ፣ ብሶታችሁ እስኪመክን፣ ተስፋችሁ እስኪያብብ፣ ሃሳባችሁ ማርፊያ እስኪያገኝ ልዝንተ – ዓለም ቀና ብላችሁ እስክትቆሙ፣ በኢትዮጵያችን ሰማይ ስር ፍትህና ነፃነት እስኪሰፍን ድረስ  ትግሉ የጠየቀውን ማንኛውንም ዋጋ እንከፍላለን እንጂ እርማችንን አልቅሰን አወጣን ብለን የሰላም እንቅልፍ አንተኛም። የገዛ ዜጎቹ በከፈሉት ግብር በተገዛ ጠብ-መንጃ መልሶ እነሱኑ የማይገድል መንግስት እስኪመጣ ድረስም  እረፍት የለንም። እነዚህ በአፀደ-ስጋ ያለፉትም ቢሆኑ ነገ ታሪክ በክብር የሚዘክራቸው መሆኑን እናረጋግጥላችዋለን።
     ዛሬ በግላጭ የሚጨፈጭፉንም ትላንትና (በ1983)”በቀይ ሽብር ያለቁ” እያሉ አፅም ሰብሰው በየቀበሌው ህዝቡን ሰብስበው ዳስ ጥለው በእንባ ሲያራጩ የነበረበትን ኩነት ዘንግተው፣ የኮነኑትን ተግባር ይበልጥ አጠናክረው መቀጠላቸው እውነት ነውና እኛም ህይወታችንን ገብረን ታሪክ እንደምንቀየር ቃል እንገባላችሁለን።
ወልዲያ ላይ ጥር12/2010ዓም የተገደሉ ወገኖቻችን ቤተሰቦች ጋር ለቅሶ ሲደርሱ የተሰማቸው ስሜት የገለፁበት መንገድ ነው።
(የፎቶው መግለጫ) ተመስገን ደሳለኝ እስክንደር ነጋ አንዷለም አራጌ።
– ባንዲራ የያዙበት ኮምቦልቻ ነው።
– በማታ የተነሱት ፎቶ  ወልዲያ አደባባይ ላይ ነው።
ከጀርባቸው ቤተክርስቲያን  የሚታይበት ደግሞ ጥር 12 ቀን ጭፍጨፋው የተጀመረበት ሲሆን፤ ቤተክርስቲያኑም በዕለቱ ለዘግናኙ ዕልቂት በምክንያትነት መንግስት የተጠቀመበት  የወልዲያ ሚካኤል ደብር ነው።
መጋቢት 10/2010 ዓም
Filed in: Amharic