>

የህወሀት ጉጅሌዎች መፈንጫ የሆነው የብር ሸለቆ የእርሻ ልማት (ሚኪ አምሀራ)

– Economy
የብር ሸለቆ እርሻ ልማት በፍኖተሰላም አካባቢ የሚገኝ ሰፊ የእርሻ ልማት ነዉ፡፡ባጋጣሚ በዚህ እርሻ ልማት ምክንያት መሬቱን ተቀምቶ ፍኖተ ሰላም ከተማ የአንድ የመንግስት ቢሮ ዉስጥ በጥበቃነት ተቀጥሮ 6 ልጆቹን የሚያሳድግ ምስኪን አማራ እንዴት ከመሬቱ ተነቅሎ እንደተባረረ አዋራኝ፡፡ ኑሮየን አስተካክል ይሆናል ብሎ ወደ ደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ ሄዶ ለተወሰነ አመታት እዛ እንደኖረ ከዛም መሬቱና ምርቱ በሳት ተቃጥሎበት የዛሬ ሶስት አመት አካባቢ እንደተመለሰ አጫወተኝ፡፡
የእርሻ ልማቱ የማን ነዉ
የብርሸለቆ እርሻ ልማት ጃቢጠናህ ወረዳ ዉስጥ በፍኖተ ሰላምና ቡሬ መካከል ወደ ደቡብ ከማንኩሳ ከተማ ከ5-8 ኪሎ ሜትር ተገንጥሎ የብር ወንዝ ተፋሰስ ላይ በሰፊዉ ተንጣሎ የሚገኝ የእርሻ ቦታ ነዉ፡፡ ይህ ሰፊና ደልዳላ የእርሻ መሬት ቀይ አፈር (ላይ በር) እና ጥቁር አፈር (ታች በር) ተብሎ የሚከፋፈል ሲሆን በሁለቱ መካከል የወያኔ ወታደር ማሰልጠኛ (ብር ሸለቆ) ይገኛል፡፡
የላይኛዉ ክፍል ወይም ላይ በር ተብሎ በአላሙዲ ስም የተያዘ ነገር ግን የትግራይ ባለስልጣናት እንደሆነ ሰዉ ያዉቃል የተለያየ የእርሻ ልማት ያለዉ ሲሆን በቆሎ፤ጤፍ፤ማንጎ፤ሻይ ቅጠል እንዲሁም የቅባት እህሎች ይመረቱበታል፡፡
የታችኛዉ ክፍል ታች በር እጅግ ሰፊ የእርሻ ቦታ ሲሆን በሺወች የሚቆጠሩ የአማራ ገበሬዎች በ19 90ወቹ መጨረሻ አካባቢ ተፈናቅለዉ ወደ ጉራ ፈርዳ እንዲሰደዱ የተደረጉበት ጡረታ በወጡ የህወሃት ኮሎኔሎችና አሁን እዛዉ ብርሸለቆ ማሰልጠኛ ዉስጥ ያሉ የህወሀት መኮነኖችና እንዲሁም በነሱ አማካኝነት ከትግራይ በመጡ ቤተሰቦቻቸዉ የተያዘ ሲሆን፡፡ በተለይ በ1999 አ.ም ባካባቢዉ በነበሩት የህወሀት ወታደሮች ከብቶቻቸዉን እንዲያስሩ፤የሚያርሱትን መሬት እንዳያርሱ ጥብቅ ትዛዝ አስተላልፈዉ ገበሬዎች እንዴት እርስታችን ሳንሞት በቁም እንወረሳለን ብለዉ በማመፃቸዉ ከፍተኛ ድብደባና እንግልት የደረሰባቸዉ ሲሆን ይሄን ያነሳሳሉ የተባሉ የአካባቢዉ ታዋቂ ሽማግሌወችም የደረሱበት ሳይታወቅ ይሄዉ 10 አመት ሆናቸዉ፡፡
የአማራ ገበሬወች ጉዳይ
ከላይ አንደጠቀስኩት በጠመንጃ አፈሙዝ መሬታቸዉን በጠራራ ፀሀይ የተዘርፉ ሲሆን ግማሾቹ ወደ ደቡብ ክልል ተሰደዉ ወያኔ እዛም ተከታትሎ ሄዶ ከጉራ ፍርዳ እንዳባረራቸዉ እናዉቃለን፡፡ ነገር ግን መጀመሪያዉኑም ከመኖሪያቸዉ ያፈናቀላቸዉ የራሱ የህወሀት ወታደርና ባለሃብት ነበር፡፡ ግማሾቹ እዛዉ ከወያኔ መኮነኖችና መሬቱን ከወሰዱት የትግሬ ባለሃብቶች እንደገና በኪራይ በመከራየት ሲያርሱ ይኖራሉ፡፡ መከራየት አቅሙ ያለፈቀደላቸዉ ገበሬወች ደግሞ ሚስትንና ልጆቹን ይዞ በቀን 6 ብር እየተከፈለዉ ሲያርም፤ሲያጭድና ሲወቃ ይዉላል፡፡ በአካባቢዉ ከፍተኛ የሆነ የመሬት ጥበት እንዲሁም ብዙ የህዝብ ቁጥር ያለዉ ሲሆን የህወሀት ኮሎኔሎች በማናለብኝነት የተራ ገበሬን መሬት በመንጠቅ ከፍተኛ በደል እያደረሱ ይገኛሉ፡፡ ጎጃም አካባቢ ባሉ ከተሞች በልመና ኑሯቸዉን እየገፉ የሚኖሩት ከ98 ፐርሰንት በላይ መሬታቸዉ በዚህ አካባቢ የተቀሙ ሰወች ናቸዉ፡፡ አሁን የህወሃት ወታደሮች የያዙት የመሬት ስፋት 20km x30 km ባጠቃላይ ከ 600 መቶ ሰኩየር ከ.ሜ. በላይ የሚሆን የምስኪን አማራ ገበሬ መሬት ተዘርፎ ለወታደር መጠቀሚያ ሁኗል፡፡
የጉልበት ብዝበዛ
ይህ የእርሻ ልማት ለትምህርት ያልደረሱ የአማራ ወጣቶችን በተለይም ምስራቅ ጎጃምና አዊ ዞን አካባቢ የሚገኙ ልጆችን በቀን በአማካኝ ከ3 እስከ 6 ብር ብቻ በመክፈል ከፍተኛ የሆነ የጉልበት ብዝበዛ የሚካሄድበት ቦታ ነዉ፡፡ ህጻናትን ከትምህርት ቤት በማስቀረት በቀን 3 ብር መክፈል ምን አይነት አረመኔነት እና በደል እንደሆነ ለሁሉም ሰዉ ግልጽ ነዉ፡፡ እንዲሁም አልፎ አልፎ ገንዘብ የለንም በማለት ልጆችን በማስፈራራትና እስር ቤት ነዉ ምናስገባችሁ በማለት የሰሩበትን ሳይከፍሉ የሚቀሩበት ጊዜም አለ፡፡ይህ እንግዲህ የሚሆነዉ በወላጆቻቸዉ ንብረት ላይ ነዉ፡፡
የሚመረተዉ ምርት የት ይገባል
በዘህ እርሻ መሬት የሚመረተዉ ጤፍና በቆሎ ወታደሮቹ አገር ዉስጥ ገቢየያ ላይ የሚቸበችቡት ሲሆን ነጭ ቦለቄዉን ደግሞ ወደ ናዝሬት ከተማ ማበጠሪያ በረንዳ ተወስዶና እዛ ተበጥሮ ለዉጭ ገቢያ ይቀርባል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን የፌደራል መንግሰትም የአማራ ክልል መንግስትም የሚያዉቀዉ ነገር የለም፡፡ ሙሉ በሙሉ በወያኔ ኮሎኔሎችና ፌደራል ላይ ባሉ በህወሃት ባለስልጣኖች ብቻ የሚታወቅ ሲሆን ገቢዉ ለነዚሁ ሰወች የግል ጥቅም ብቻ የሚዉል ነዉ፡፡
ልክ እንደ ብር ሸለቆ ሰቲት ሁመራ ሰፊ የመንግስት የሚባል በኮሎኔሎች የተያዘ የእርሻ ልማት ነበር፡፡ ይሄን የእርሻ ልማት ግን ለትግራይ ገበሬዎች አከፋፍለዉ የሰጡ ሲሆን የአካባቢዉ ህዝብም በዚህ ተጠቃሚ ሁኗል፡፡ የሁመራን የእርሻ ልማትን ካከፋፈሉ በኋላ ግን ወታደሮቹ ወደ ብር ሸለቆ በመምጣት ገበሬዉን ቀምተዉ ማረስ ከጀመሩ ከ 10 አመት በላይ ሁኗቸዋል፡፡
አማራ ክልል ዉስጥ ብዙ አካባቢወች በምርትና መሬት እጥረት ምክንያት በሴፍቲኔት የሚኖሩ ሲሆን በሽወች የሚቆጠሩ ወጣቶችንና መሬት የሌላቸዉን ሰወች ሊታደግ የሚችሉ ምርታማ የሆኑ አካባቢች እንደ ብር ሸለቆ የእርሻ ልማት፤የአየዉ የእርሻ ልማት፤ ዘለቀ እርሻ ልማት፤የበለስና ጃዊ የእርሻ ልማት የትቂት የህወሃት ወሮበሎች መፈንጫ ሁኗል፡፡ በነዚህ አካባቢ የሚመረተዉ ምርትም ሆነ ገንዘብ ለአካባቢዉ ህብረተሰብ ምንም ጥቅም እንደማይሰጥ ይታወቃል፡፡ ለዚህም ነዉ በባለፈዉ ቆቦ አካባቢ በነበረዉ የህዝብ አመጽ የመጀመሪያ ሰለባ የሆነዉ ባካባቢዉ የገበሬዉን መሬት ዘርፎ የህወሃት ኮሎኔሎች ምርት የሚያመርቱበት የዘለቀ እርሻ ልማት ነበር፡፡
ብአዴን የመልካም አስተዳደር ችግር እቀርፋለዉ ካለ እነዚህን 5 ወይም 6 አካባቢ ከ 10 እና 15 ሰዉ ባልበለጠ የተያዙ ነገር ግን እስከ 50 እና 60 ሺህ የአማራ ገበሬና ወጣት ሊጠቀልል የሚችል የእርሻ ልማቶች ለህዝቡ ያከፋፍል፡፡ በአካባቢዉ ያለዉ ህብረተሰብም ጫና ማድረግና በየስብሰባዉ ማንሳት አለበት፡፡
cc// ANDM CC office ANRS Communication Affairs Office West Gojjam Government Communication Affairs Office
Filed in: Amharic