>

ህወሃት ሙስሊሙን ህዝብ መናቅ ያቁም!!! (ሲሳይ አጌና)

 ከትላንት ጀምሮ የህወሃት የፌስቡክ ተከፋዮች “የመጀመሪያው ሙስሊም ጠቅላይ ሚኒስቴር ሊሾም ነው!” የሚል ተራ ወሬ እያናፈሱ ነው። ይሄ እንግዲህ የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ማማለል መሆኑ ነው።
እውነት የኢትዮጵያን ሙስሊሞች በዚህ ሰውዬ ማጓጓት ይቻላል? ይሄን ማሰቡስ የሙስሊሙን ኡማ መናቅ አይሆንም!!
እውነቱን ለማውራት ደመቀ መኮንን ተክለአረጋይ ስለሙስሊሙ የሚገደው ሙስሊም ነው?? የአህባሽ አስተምህሮ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ በግድ እንዲጫን ሲታገሉ ከነበሩት ከነሽፈራው ተክለማሪያም ጋር ሆኖ ሲያደርግ የነበረውን ዘመቻ አናውቀውም?? ያን ተከትሎ ስንት እና ስንት ሙስሊሞች በአደባባይ በስናይፐር ደረት ደረታቸውን  እየተባሉ አልተደፉም?? በሺህ የሚቆጠሩ ወደ ማእከላዊ እና ወዳልታወቁ እስርቤቶች አልተጋዙም ? አሸባሪ ተብለው አልተሰቃዩም/አሁንም እየተሰቃዩ ያሉ ለቁጥር ያዳግታሉ፤ የተለቀቁት ኮሚቴዎቹ ብቻ ናቸው፤ እነሱም አምስት እና ስድስት አመት በግፍ ታስረው ነው የተለቀቁት/ ከምንም በላይ ጥያቄው አሁንም ባልተመለሰበት ጊዜ ላይ ደመቀ የሚባል አህባሽ ወደፊት መጣ አልመጣ ለሙስሊሙ ምኑም ነው።
ኡስታዝ እህመዲን ጀበል ከእስር ከተፈታ በኋላ ከዞን ዘጠኙ አባል በፍቃዱ ጋር በኢትዮ ቱዩብ ላይ ባደረገው ቃለመጠይቅ “ጥያቄያቹ ተመልሷል ወይ?” ብሎ ሲጠይቀው “አያገባቹም የሚል መልስ ተመልሶልናል፤በመግደል ተመልሶልናል፣በማሰር ተመልሶልናል” ነው ያለው። እናም አይደለም በእስልምና ስም ሙስሊሙንም እስልምናንም የሚጠየፈውን ደመቀን ትክክለኛ ሙስሊም ጠቅላይ ሚኒስቴር ብታመጡ እንኳን የሙስሊሙ የሃይማኖት ነጻነት መብት እስካልተከበረ ድረስ ማንንም ሙስሊም አትሸውዱም !! አትልፉ!!
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጥያቄ ለምን ኦርቶዶክስ መራ፣ለምን ጴንጤ መራ? ሙስሊም መምራት አለበት የሚል አይደለም። ማንም ይምራ ግን ፍትሃዊ መሪ ይምጣ የሚል ነው!!
Filed in: Amharic