>

በረከት ህወሃትን በኦህዲድ እያስፈራራ ከደመቀ ጀርባ ሆኖ አራት ኪሎ ለመግባት አድፍጧል!!! (ደረጀ ገረፋ ቱሉ)

እውን ህወሃት ለበአዴን እጅ ይሰጣል?እኔ አላምንም።
1993 ለህወሃት ጥሩ ዓመት አልነበረም።በኤሪትራ elites እና በሻዓቢያ የትዕብት እብጠት አንጀታቸው ያረረው የትግራይ ቤሄርተኞች የኢትዮ ኤርትራን ጦርነት አስታከው ሸዓቢያን ለማስተንፈስ የነበራቸውን ህልም የኤርትራዊያን ደም አለባቸው ተብለው በሚታሙት በበረከት ፣በአቦይ እና በመለስ ከሽፎባቸዋል።
በዚህ እርር ድብን ያሉት የትግራይ ቤሄርተኞቹ ሲዬ እና ተወለደ አዲስ መፈክር ፅፈው ተማማሉ።
“ከሻዓቢያ መልስ ወደ መለስ” የሚል አጭር መፈክር።
ይህም ሳይሳካላቸው የትግራይ ቤሄርተኞች ዳግም በነ አቦይ ፣መለስ እና በረከት ጥምረት ተሸንፈው ከልጅነት እስከ እውቀት በየጥሻው ተዋድቀው ለስልጣን ካደረሱት ድርጅታቸው ተባረሩ።
ትግራይ አሸንፋ በመሸነፏ አለቀሰች።ወደ ውጭ ሳይሆን ወደ ውስጥ !!እየተፈኑ ማልቅስ ያቃጥላል።
እሄው እስከዛሬ የትግራይ ቤሄርተኞች እየተፈኑ ስለሚያለቅሱ አልወጣላቸውም።እነ ተስፈ ኪሮስ እና እነ ሴቭ አደነ ዛሬም ድረስ እዬዬ እንዳሉ ነው።
ግና ምን ያደርጋል ዛሬ ሌላ ቀን ነው!!
እሄው ዛሬ ደግሞ ደግም ለነበረከት እጅ ለመስጠት ጥቅት ቀናት ሳይሆን ጥቅት ሰዓታት ቀርቶአቸዋል።
ወደ መለስ፣ በረከት እና አቦይ ጥምረት ስነመለስ፦ የበረከት እና የመለስ ጥምረት እስከ መለስ እለተሞት ድረስ አለፈረሰም ነበር።አቦይ ከጥምረቱ እንደተገለሉ የአደባባይ ምስጥር ነው።ከመለስ ህልፈት በኃላ አቦይ እና በረከት እላይ እላዩን ወዳጅ ቢመስሉም አንዱ የአንዱን ጉድጓድ እየማሰ ነው።
አቦይ በረከትን ቀብሬዋለሁ ብለው ዘና ብሉው ነበር።እውነትም በረከት ከአይን እስክሰወር ድረስ አባረውት ነበር። ዛሬ ግን ሌላ ቀን ነው።በረከት ከደመቀ ጀርባ ሆኖ አራት ኪሎ ለመግበት አድፍጧል።
በረከት ህወሃትን በኦህዲድ እያስፈራራ ከደመቀ ጀርባ ሆኖ አራት ኪሎ በራፍ ላይ ነው።በረከት እሄንን ካደረገ እና ከተሳካለት ማንንም አላሸነፈም።ህዋሃትን ግን ለብቻውን ሁለቴ በሎጬ ማሸነፉ ነው።አንዱ መጋቢት 1993 ሲሆን ሌላኛው ደግሞ መጋቢት 2010 መሆኑ ነው።
በረከት ህወሃትን በኦህዲድ አስፈራርቶ ህወሃቶች ሙሉ በሙሉ ድምፃቸውን ለደመቀ ከሰጡ ያነገሱት ደመቀን ሳይሆን በረከትን እንደሆነ ያውቃሉ።ብዙ ሰው በረከት ኤርትራዊ ስለሆነ ለትግሬ ጥሩ ነው ይላሉ።እኔ ግን እንደዛ አይመስለኝም።በረከት ጎንደሬነትን እና ኤርትራዊነትን ያጣመረ ስነልቦና ያለው ኩሩ ኢትዮጵያዊ ነው።ይህ ስነልቦና ለተጋሩ ምን እንደሆነ እኔ ከተጋሩ በላይ አላውቅም።እናም እዚህ ውስጥ አልገባም ለማለት ነው።
ስናጠቃልል ደመቀ ከተመረጠ ደመቀ ለብቻውን አይመጣም።ደመቀን ተከትሎ የሚመጡ የሚኒልክ ስነልቦና ያላቸው የሸዋ ፖለቲከኞች አይጠፉም።ደመቀ እራሱ የመጀመሪያ ስራው የታማበትን ነገር ማክሸፍ እንዳለበት እና የኃይሌን ስህተት ለለማድገም መፍጨርጨሩ አይቀርም።የኃይሌ ስህተት ምን ነበር እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ።የኃይሌ ስህተት ግልፅ እና አጭር ነበር።በራሱ ከመወሰን ህዋሃቶችን ያባብላል ሲባል ነበር።ደመቀም በዚህ ይታማል።እሱም ይህንን ያውቃል።ስለዚህ የኔ ፍርሃት ደመቀ reaction ውስጥ እንዳይገባ ነው።ይህ ከሆነ ደግሞ ህወሃቶች የፈሩት ደረሰ ፣የጠሉት ወረሰ ማለት ነው።
ህወሃቶች ልክ እንደዛሬው ኦሆዲድን እንደሙሙ ከመፍራታቸው በፊት የሚጠሉትም ሆነ የሚፈሩት አንድ ነገር ነው። ስልጣናቸውን የአማራ elites እንዳይነጥቁአቸው በጣም ይፈራሉ።የሚጠሉትም ይህው ነበር።ዛሬ ግን ቀኑ ሌላ ነው እየተባለ ነው።ይህንን ለማወቅ ቃናት ሳይሆን የሰዓታት እድሜ ብቻ ነው የቀረን!!
እሄ ካልሆነ ህወሃት ቤአዴንን እየሸወደ ይሆን? እኔ ይመስለኛል። ለማንኛውም በቀጣዩ ፅሁፌ ይህንን ለመዳሰስ እሞክራለሁ።

Filed in: Amharic