>

የኦሮሞ ሕዝብ የሚታገለዉ ለመገንጠልና ትልቅ ኦሮምያን ለመመስረት ሳይሆን ለጋራ ሀገራዊ አንድነት ነዉ

አሰፋ ኢትዮጵያ

ወያኔ የኦነግን ባንድራ ተጠልሎና የኦረምን ህዝብ #መመሳሰል የኦረሞ ህዝብ ትግል በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት እንዳያገኝ በማሰብ ሰሞኑን   ማህበራዊ ሚዲያ ተጠምዷል።  የኦረሞ ሕዝብ የሚታገለዉ ለመገንጠልና ትልቅ ኦረሚያን ለመመስረት ሳይሆን እንደማንኛዉም ኢትዮጵያዊ መብቱን ለማስከበርና በወያኔ አገዛዝ የሚደርስበትን ግፍና በደል ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ ጋር በመተባበር ለማስወገድና ለጋራ ሀገራዊ አንድነት ነዉ። ይህ የኦረሞ ሕዝብም ሆነ የቄሮወች አቋም ነዉ።

የኦነግን ዓላማ ግን የሚያራግበዉና የሚያናፍሰዉ በግራም በቀኝም መተንፈሻ አጥሮት ተወጥሮ ያለዉ የወያኔ አገዛዝ ነዉ። ወያኔ በዚህ ሰዓት ደግሞ አደለም አንድ ኦነግ ከቻለች በሺህ የሚቆጠር ኦነግ መመስረት ትፈልጋለች። የኦረሞን ህዝብ ከሌላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ለማስገለል ስትል ሰሞኑን ደግሞ የኦነግን ባንድራ እንደነጠላ ኩታ አጣፍታ ብቅ ብላለች። ይህም የሚያሳየዉ የወያኔ ስልጣን ባለበት መቆየት የሚችለዉ ብሄርን ከብሄር ከማጋጨት በተጨማሪ አንድን ብሄር ስም የዉሸት ስም በመስጠት እንደ ተገንጣይና እንደ ብሄርተኛ በማስመሰል ለሌሎች አስመስሎ ማቅረብ ነዉ። ይህንንም ላለፉት 27አመታት ወያኔ በኦረሞ ህዝብ ላይ ሲያካህደዉ የነበረ ገሀድ እዉነታ ነዉ።

በዚህም ወያኔ በኦረሞ ብሄርተኝነት ላይ ላለፉት20 አመታት ዉጤታማ ሁኖ መዉጣት ችሏል። ዉጤታማ ከሆነባቸዉም አንዱና ዋናዉ የኦረሞን ህዝብ እንደ ብሄርተኛና እንደ ተገንጣይ አስመስሎ ለሌሎቹ ብሄሮች በማቅረብ በሌሎች ብሄሮች የኦረሞ ህዝብ እንድገለልና እንድጠላ አድርጎታል። ሁለተኛዉ መንገድ ወያኔ ዉጤታማ የሆነበት የኦረሞ ምሁራንና ፖለቲከኞችን በኦነግ ስም ወደ ማሰቃያ ካምፕ ለማጋዝና በማሰር ለመብቱ እንዳይጮህ ለማፈን ተጠቅሞበታል። ሦስተኛዉ ደግሞ የኦረሞ ወጣቶችን በኦነግ ስም በማስመሰል በጂምላ በየትምህርት ቤቱና በተለያዩ የኦረሞ ጫካወች ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ ደረስኩባቸዉ እጃቸዉን አሳልፈዉ እንድሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆናቸዉ ጀግናዉ የመከላከያ ወታደራችን ባደረሰባቸዉ ጥቃት ሊደመሰሰሱ ችለዋል በማለት ምንም ሳይፈራ በሚዲያ ለሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በመልካም ተጋድሎ ዜና ሲያሰማም አመታት ተቆጥረዋል። በሰዓቱም በኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ ተሰሚነት ስለነበረዉና የተወሰነም ድጋፍ ስላገኘ ከ1995ዓ/ም ጀምሮ በኦረሞ ህዝብ ላይ ግልጥ ጦርነት በማወጅ ለስርዓቴ ህልዉና ያሰጉኛል ያላቸዉን የኦረሞ አካባቢወች ካፀዳና ከገደለ በሗላ በተለይ ጀግናዉን የነፃነት ታጋይ የህዝብን ልጂ አቶ ለገሰ ወጊን ካስገደለ ወዲህ ተአሁን በሗላ ኦነግ የሚባል የለም ኦነግን በጀግናዉ የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን ሌት ተቀን ባካሄድነዉ እልህ አስጨራሺ ዉጊያ ሙሉ በሙሉ ደምስሰነዋል በማል አወጀ።

ድሮም ቢሆን ያለዉ የወያኔ ኦነግ እንጂ የኦረሞ ኦነግ የለምና ይህም ወያኔ የእራሱ ስራ መሆኑን ላልተረዳዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ጀብደኝነት እራሱን አስመስሎ አሳምኖ አቅርቧል። ከዛያችን ሰዓት ወያኔ ኦነግን ደምሰሰነዋል ኦነግ የሚባል የለም የምትለዋ ዜና ለህዝብ ይፋ ተወጣች ጀምሮ ኦነግ የሚባልም በኦረሚያ ክልል ዝር ሳይል አመታት ተቆጠሩ ነገሮችም ተቀየሩ።ያልተቀየረ ነገር ቢኖር የኦረሚያ ህዝብ ትግል ነዉ። ይህ የኦረሚያ ትግልም በትክክል የኦረሞ ህዝብ ትግል ነዉና የወያኔ እጅ ስለሌለበት ከኦረሚያ አልፎ ወደ አማራና ደቡብ ክልልም ተሸጋገረ። በተለይም በአማራ ክልል ባህር ዳርና ጎንደር የተካሄደዉ ሰላማዊ ሰልፍ የኦረሞን ህዝብ ትግል የአማራዉ ህዝብ የተረዳበትና ያመነበት ትግል ነበር። አጠቃላይ ያለፉት 4እና 5ተከታታይ አመታት ትግል የኦረሞን ማንነትና ለምን እንደሚታገል ሌሎቹ ብሄሮች የተረዱበት ትልቅ አጋጣሚ ተፈጥሯል። ይህ እድል ሊፈጠር የቻለዉ ግን የወያኔ መጠቀሚያ የሆነዉ ኦነግ በመጥፋቱና የኦረ ህዝብም የትግል አላማዉን ለሌሎቹ ብሄሮች በግልፅ ማሳወቁ ነዉ። የኦረሞ ህዝብም በየአደባባዩ የታቃዉሞ ቦታወች የሚያሰማዉ ድምፅ ”ወያኔ ይዉደም”…. ”መብታችን ይከበር” …” በገዛ ሀገራችን እንደ ሁለተኛ ዜጋ መታየታችን ይቁም!” ”እኛ የኦረሞ ህዝቦችና የቄሮ ወጣቶች የምንታገለዉ ለመገንጠልና ትልቅ ኦረሚያን ለመመስረት ሳይሆን የጋራ ሀገራችንን ኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅና በወያኔ ከፋፋይነትና ብሄርተኝነት የተስፋፋባትን ልዩነት ወደ አንድነ ለማምጣት ነዉ” በሚለዉ የሁል ግዜም መፈክራቸዉ አቋማቸዉን ገልፀዋል።

በዚህም በኦረሞ ህዝብ ሀገራዊ የትግል መፈክር የወያኔ ባላወች በየአቅጣጫዉ ተወዛወዙ ቡለናቸዉ ላላ ለድንጋጤና ለጭንቀት ወያኔወች ተጋለጡ። ምክናየቱም የኦረሞ ህዝብ ዉስጣዊ ማንነት መላዉ ኢትዮጵያኖች በግልፅ ታወቀ የኦረሞ ህዝብ በጭራሺ ከኢትዮጵያዊነቱ የሚነጥለዉን ማንኛዉንም ድርጅት እንደጥላትነት ቆጠረ በወያኔ የተነጠቀዉን ኢትዮጵያነቱን በየአደባባዩ አስመሰከረ ኦረሞ ኢትዮጵያ ያልሆነባት ሀገር በጭራሺ እንደለለችና ወደፊትም እንደማትኖር ሌሎች ብሄሮችም አወቁ።

ኦሮማራ የሚል ስያሜም በመሰየም ከአማራዉ ወገናቸዉ መቸም ቢሆን ማንም እንደማይነጥላቸዉ እንደማይከፋፍላቸዉ ደጋግመዉ ለጋራ ሀገራቸዉ ጥላት ለሆነዉ አገር አፍራሺ ወያኔ በሚገባዉ አማርኛ ነገሩት አዜሙለት። እነሆ ዛም ደግሞ ወያኔ የመተዉን ኦነግን ቀብሩን ከፍታ አፈሩን አራግፋ አለ ትለናለች። በሞያሌ ከተማም በግፍ የጨፈጨፋቸዉን ዜጎ ኦነግን ለመፋለም በግዳጂ ላይ ያለ አንድ ብርጌድ ሻለቃ ጦር በተሳሳተ መረጃ የወሰደ ግዲያ ነዉ አለ። ከዚያን እለት ጀምሮም በማህበራዊ መገናኛ የኦነግን ባንድራና ካርታ የታቀፉ ወያኔወች ተበራከቱ። እነዚሁ በኦነግ ባንድራ የተጠለሉ ፋሺስት ወያኔወች አልፈራና አልጠረጥር ብለዉ ጭራሺ የአማራዉንና የኦረሞዉን አንድነት ቢቻላቸዉ ለመናድ አስበዉ መሰለኝ በዘረኝነት የተምላ ስድብ ሁላ ሳይቀር ማስተላለፍ ጀምረዋል። በተለይ የፌስቡክ ተጠቃሚወች የማሳስባችሁ ነገር የኦነግን ካርታና ባንድራና እንድሁም ሌሎች የኦነግን መጠሪያ ለብሰዉ የዘረኝነት ፖለቲካን በአማራዉና በኦረሞዉ መካከል የጥላቻ ቃላት የሚያስተላልፉ ከዘረኛዉና ከተገንጣዩ የትግራይ ወንበደ ወያኔ የተመለመሉ የትግራይ ልጆች መሆናቸዉን እንድትረዱና ለሌሎችም እንድታስተዋዉቁ አሳስባለሁ። ህንን በተመለከተ በአማራዉም በኩል እነዚሁ በወያኔ የተመለመሉ የትግሬ ወንበደወች በሰፊዉ እንደተበተኑና አማራን በመምሰል የኦረሞን ህዝብ የሚሳደቡና አማራዉን ከኦረሞ ለማጋጨት እየሰሩ እንደሆነም ማወቅ የሚገባችሁ ዋና ጉዳይ ነዉ። ተገንጣይና ወገን ከፋፋይ ዘረኛ ሀገር አፍራሺ ኢትዮጵያ ጠል ጥገኛ ለመገንጠል የተዘጋጀ እራሱ ወያኔ እንጂ ሌላም ብሄር በፍፁም የመገንጠል አላማ የለዉም። የኦረሞ ህዝብ የሚታገለዉና የሚሞተዉ ለመገንጠልና የወያኔን አላማ ለመፈፀም ሳይሆን በገዛ ሀገሩና በገዛ ክልሉ በትግራይ ወሮ በላ ወንበዴ የሚካህድበትን የመብት ጥሰትና የገንዘብ ዝርፊያ ከወያኔ እጅ ለማስወጣትና ኦረሞ ስለሆነ ብቻ በትግራዊ ዘረኛ ስርዓት የሚፈፀምበትን የግፍ ግርፋትና እስራት እንድሁም የጂምላ ግድያወችን ከኦረሚያም ባለፈ ለመላዉ ኢትዮጵያዊ የታፈነ ህዝብ ነዉ።
አንድነት ሃይል ነዉ!!

 

Filed in: Amharic