>

መቶ ዓመት የገነቡት በአንድ ሰዓት እንደሚወድም ያላወቁ ህውሓታውያን (ቶማስ በቀለ)

የትግራይ ኢንዱስትሪ ፓርክ ። 
ሌላው ይሙት ይታሰር ይጨቆን !
መቶ ዓመት የገነቡት በአንድ ሰዓት እንደሚወድም ያላወቁ ህውሓታውያን በኢትዮጵያኖች መቃብር ላይ እነርሱ በሥልጣኔ መኖር ምኞታቸውና ዓላማቸው መሆኑን ከዚህ ምስል መረዳት ይቻላል ።

ከአማራው ጀኔረተር እየተነቀለ ተወስዶ ወደዚህ ሥፍራ ለመብራት መጠባበቂያ እንደተተከለ ማሳያ ነው ። ደኖች የተጨፈጨፉት ገበሬው ለማዳበሪያ ለመሬት ግብር የገበረው ለራሱ መንገድ ለማሰራት የተሻለ ለውጥ ለማምጣት አይደለም ። ለዚሁ ዞን ወርድና ስፋት መዘርጊያ ነው ።

እነ ጣና በለስ ኃይል ማመንጫ ለትግራይ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተዘረጉ ናቸው ። ልማትና እድገቱን እንደ ሀገር ባንቃወምም በእኛ መቃብር ላይ ለመኖር ማሰብ ግን ለእድገታቸው ዋስትና አይሆንም ።

የኦሮሞ አንጡራ ሀብት ተጠርጎ የገበሬው መሬት በችርቻሮ ተቸብችቦ ለትግራይ ኢንዱስትሪ እድገት/ Tigrai industrial highland/ማስፋፊያ ሆኗል ማለት ነው ።
የጋምቤላ መሬት 90% በህውሓት ካድሬዎች መወረሩ የግቡ ፍፃሜ ለጋንቤላውያን ሳይሆን ለትግራይ ይልቁንም ለስብሓታውን ኢንዱስትሪ ሎጅ ነው ።

የጉራጌ ሆስፒታል ግንባታ ታጥፎ ፕሮጀክቱ ወደ መቀሌ መጓዙ ከመርካቶ ግንባር ቦታ በታክስ ጫና መባረሩ ለሌላ አይደለም ለዚሁ ኢንዱስትሪ ማደራጃ ነው ። በዚህ እነ ዶ/ር ካሱ ኢላላ ታላቁን ሚና ተጫውተዋል ።

ከጅቡቲ መቀሌ የተነጠፈው የባቡር ሀዲድ መንገድ ለኢንፖርት ኤክስፖርት ምልልስ የኢንዱስትሪውን ምርት ለማቀላጠፍ የታሰበ ነው ።
ኢትዮጵያኖች ያለምንም ርህራሄ በጠራራ ፀሐይ የሚገደሉበት ምሥጢሩ የኢንዱስትሪው ዞን ህልውና ጉዳይ ስለሆነ ብቻ ነው ።

ኦህዴድና ብአዴን ደህዴን ለዚህ ምላሻችሁ ምን ሊሆን እንደሚችል ባይገባኝም ለደማችን ሁሉ ነገ ዋጋ ትከፍላላችሁ ። በፓርላማ እጃችሁን ያወጣችሁ ሕዝባችሁን ለትግሬ ወያኔ አሳልፋችሁ የሰጣችሁ ሁሉ ታሪክ ይፋረዳችኋል።

እኛ ትግራይ በኢትዮጵያ ሥር እስካለች ድረስ ከፍታዋ አያስቀናንም ከጀርባው የታሰበው ሴራ ግን ለትግራውያን ጭምር ጥፋት በመሆኑ ከመቃወም አልፈን የሞት ሽረት ትግል ላይ ነን ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ በፊትም አሸናፊ ነው አሁንም ይሄን አምባገነናዊ መንግስት የሚደመስስበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ።
ልትጠፋ ያለች ከተማ 
ነጋሪት ቢጎሰም አትሰማ !!

Filed in: Amharic