>

አዲሱ የትግሬ ወያኔ ሴራ በአብደራፊ ከተማ (አለማየሁ ሀይሌ)

በምዕራብ  ጎንደር ዞን ከሱዳን  25/35ኪሜ ርቀት ላይ የምተገኘዉና የበርሐዉ ፈርጥ ሆና ከታላቁ አንገረብ ወንዝ ዳር የተንጣለለችዉ አብደራፊ/ምድረ ገነት የተባለችው  ዉብ ከተማ በወያኔ  እየተሴረባት ነዉ፡፡ በትናትናው  ዕለት የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በከተማዉና በአካባቢው  ህወሀት ሆም ብሎ ከ1984 ጀምሮ ያሰፈራቸና አሁንም ከትግራይ አምጥቶ እያሰፈራቸዉ ያሉ ትግሬዎች በትግርኛ ካልተማርንም እያሉ ነባሩ የአማራ ነዋሪ ላይ ችግር እንደፈጠሩ ተሰምቷል ፡፡  ከሁለት ሳምንት በፊት ለሥራ ወደቦታው በተጓዝኩ ጊዜ እዳስተዋልኩት ከተማዋ በተጠና መልኩ ከሌላዉ የአማራ ከልል ተለይታ ወደትግራይ  ቀድመዉ ከተወሰዱት ዳንሻ፣ ማይካድራና ሁመራ ጋር በወያኔው ሱር ኮንስትራክሺን ድርጅት በአስፋልት ተገናኝታለች፡፡ የሚገርመው የተሰራዉ አስፋልት  ይችን ከተማ ብቻ ከሁለቱም አቅጣጫ ወደትግራይ ብቻ በማገናኘት ሌላዉን የአማራ ክልል ሳይነካ በማለፍ አብዛኛው የከተማዋ የመጓጓዣ እንቅስቃሴ ከረዳትና ሾፌርም ሳይቀር ወደትግራይ ነዉ የሚጭኑት፡፡ከተማዋን በሁለት ቀበሌ  አንገረብ ና አዲስ አለም በሚባሉ ቀበሌዎች በመክፈል በአዲስ አለም ቀበሌ  ትግሬዎች አሁንም ከትግራይ  እየመጡ የቀበሌ  መታወቂያ እደተሰጣቸዉ ነዉ፡፡ አማራዉ በሚበዛበት አንገረብ ቀበሌ ለአማራ የቀበሌ መታወቂያ ማግኘት ፈታኝ ነዉ፡፡ ብአድን የተባለው ድንዝዝ ድርጅት የወረዳ ዋና ከተማነቱን ከአብደራፊ አንስቶ 20ኪሜ ወደዉስጥ አብርሀጂራ አፈግፍጓል፡፡  ከአመታት በፊት በከተማዋ ላይ ወያኔ የራሱ ለማድረግ የሚሰራዉን ተንኮል በዚሁ በማህበራዊ ሚዲያ አንድ ወንድማችን አገርቶን የነበረ ሲሆን እኔም በመጋቢት 2010  ጉዞየ ይኽ እዉነት መሆኑን አረጋግጫለሁ ፡፡ ሁሉም አማራ ለዘላቂ መፍትሔ ትኩረቱን ወደዚያው ያድርግ፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዛሬ

የህወሓት -አባላት — በጎንደር — አርማጭሆ አብደራፊ ከተማ — አንደኛ ደረጃ ት/ቤት — ተማሪዎች — በክፍል በተቀመጡቀት — በእሳት — አቃጥለውታል ::

ህወሓት የበቀል እርምጃውን አጠናክሮ ቀጥላል ፡፡
ዛሬ መጋቢት 19 ቀን 2010 ዓ/ም ከጥዋቱ 2:45 ሲሆን በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ አብደራፊ ከተማ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በክፍል በተቀመጡቀት በእሳት አቃጥለውታል ፡፡
ይህን ቃጠሎ የፈፀሙት የህወሓት አባላት ሲሆኑ እነዚህ ይህን እኩይ እና አስነዋሪ ዘግናኝ ስራ የፈፀሙት የህወሓት ደህንነቶች ሲዝቱ እንደነበር እና በአካባቢው ለሚገኙ የብአዴን ሰዎች ቢነገራቸውም ችላ በማለታቸው ይህ ድርጊት ሊፈፀም ችላል።
ቀደም ሲል አብደራፊን ወደ ትግራይ ክልል ለማካለል ጥረት ሲያደርጉና በአካባቢው በተደጋጋሚ ህወሓቶች ችግር ሲፈጥሩ የአካባቢው ህብረተሰብ እየሰሩት ባለው በደል በመማረር እነዚህ የህወሓት ደህንነቶች ከቦታው በራሳቸው ጊዜ ከቦታው ለቀው ከወጡ በኃላ የነዚህ የደህንነት ልጆችም ከትምርት ቤት በራሳቸው ጊዜ የለቀቁ ቢሆንም አሁንም የተለያዩ ብቀላዎችን ሲሰሩ ቆይተው በዛሬው ቀን ግን እጅግ አረመናዊ እና ዘግናኝ ስራ ነው የፈፀሙት በአጠቃላይ 8 ክፍሎችን ቆልፈው ነው ያቃጠላቸው በጥቃቱ በረካቶች በእሳት ተቃጥለዋል ፡ ቡዙዎች ተጎድተዋል ከፍተኛ የጥይት ተኩስ እየተሰማ ነው ፡፡ ያለውን ነገር እየተከታተልን እናሳውቃለን ፡፡
አግ7 ዘመቻ ነፃ ትውልድ
Filed in: Amharic