ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለዳግም እስር ከተዳረገ ዛሬ በስድስተኛው ቀን በህመሙ ምክኒያት ሆስፒታል ገብቶል።
ትላንት መጋቢት 20/2010 ዓም
ትላንት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ስጠይቀው አሁን ያለቡት የእስር ክፍል “ለሰው ሳይሆን ለበግ የሚሆን አይደለም” ብሎኝ ነበር። በሰአቱ ሆኔታው ሳየው የጀርባውና የወገቡ ህመም ክፍኛ እንዳመመው ቢያስታውቅም ምንም እንዳልተፈጠረ አደርጓ አዋርቶኝ ለጀርባ እና ለወገቡ ህመሙ የመጣሁትን ማስታገሻ መዳኒት ሰጥቼ ወደ ቤት ብመለስም ሃሳቤ ግን ተመስገን ጋር ፖሊስ መመሪያ ነበር።
ዛሬ መጋቢት 21/2010 ዓም

ጠዋት 3:37
በዚህ ስአት በአራት ፖሊሶች ተጅቦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍል ከተማ የወረዳ 8 እና 9 የሆነው ጤና ጣቢያ ተመስገንን ይዘን ደርስ። ጤና ጣቢያው ህክምናውን ለማድረግ ከሞከረ በኃላ የተመስገን ህመም ከአቅሜ በላይ ነው በማለት እሪፈር ለዘውዲቱ ሆስፒታል ፃፋ ተመስገንን ይዘን ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ሄድን።
ዘውዲቱ ሆስፒታል ከደረስን ሰአታት ቢያልፈን የተመስገን ህክምና እስካውን አላለቀም እኛም ጭንቅ አርግዘን ዘውዲቱ ሆስፒታል እንገኛለን።
በተመስገን ላይ ለሚደርሰው ነገር ሁሉ መንግስት ሀላፊነቱን ይወስዳል።
ከሰአት 9:03
መጋቢት 21/2010 ዓም
ጎሳዬ ተፈራ
በዚህ በኩል ስንት ዋጋ የከፈሉትን የነፃነት ታጋዮች እያስበላን በተፋፋመው ትግል ላይ የፈላ ዘይት ደፍተን እንደሞላለት ሠው ስለ አብይ እናወራለን:: ባይገባን ነው እንጂ ለእነ አብይም እዚህ መድረስ የትግል እርሾዎቹ ከዘግናኝ የእስር ቆይታ በሁዋላ ከሠውነት ግብር ወጥተው ተፈቱ ተብለው አፍታም ሳይቆዩ ለዳግም እስር የተዳረጉት እነዚህ በዘመናት ሊተኩ የማይችሉ ብርቅዬ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው:: አሁንም የአብይን ወሬ ቆም አድርገን ወደ አለመኖር እየተገፉ ስላሉት ጀግኖቻችን ላይ እንድንሠራ በእግዚአብሔር ሥም ለምናችሁአለሁ:: በሁዋላ ካመለጡን ይሄም የጉዋጉዋንለት ድልም ህልም ሆኖ ይቀራል::
ጓደኞቼን ጥዬ ሆስፒታል አላድርም” ያለውን
ተመስገንን ደጋግፈን ወደ ጣቢያ መልሰነዋል

ዘውዲቱ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ የቆመው የፖሊስ መኪና ውስጥ ተመስገን መግባት ስላቃተው እኔ እና ሁለት ፖሊሶች ደግፈን ነን ተሸከመን ያስገባነው።
እንግዲህ ተመስገንም ከነ ህመሙ ወደ ጓደኞቹ እየሄደ ነው።
ከግልህ ህመም በላይ የሀገር ህመም የሚሰማህ ከግለህ መዳን በላይ የጓደኞችህ ሁኔታ የሚያሳስብህ ተመስገን እንግዲህ የኢትዮጵያ አምላክ አብሮ ይሁን ከማለት በለይ ምን እላለሁ።
ቀን 10:50
መጋቢት 21/2