>
5:13 pm - Friday April 18, 5919

የታሰርኩት መንግስት ምንድን ነው የምትፅፈው ሲለኝ ምን አገባህ ብዬ ነው! (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

ታሪኩ ደሳለኝ
አሁን እነ ተመስገንን ጠይቄ ነው የወጣሁት ተመስገን በማስታገሻም መዳኒትም ቢሆን  ደና ነው። በንግግራችን ማሀል ተመስገን እንዲህ አለኝ
“ተመስገን እስክርቢቶ እፈልጋለሁ?” አለ
ሰጠነው ይሄኔ የተሰበሰቡት ፖሊሶች ወደተመስገን ቀረቡ ከማሀላቸው አንዱ ፖሊስ
 ፖሊሱ “ለምን ፈልገከው ነው?” አለው
ተመስገን “ልፅፍበት?” አለው
ፖሊሱ “ምን ልትፅፍበት?” አለው
 (ተመስገን በላ ማመን)
ተመስገን “ምን ልትፅፍበት ነው ያልከው?” አለው
 ፖሊሶቹ በአንገታቸው አዎ አሉ
ተመስገን “ምን አገባችሁ! …. ማንም ምንድን ነው የምትፅፈው እንዲለኝ አልፈቅድለትም! የታሰርኩትም መንግስት ምንድው የምትፅፈው ሲለኝ ምን አገባህ ብዬ ነው!! አለቸው
ይሄን ግዜ ፖሊሶች ተሰበሰቡ እስክንደርም ድንገት መጣ እስክንድር የተሰበሰቡትን ፖሊሶች እየተመለከተ
እስክንደር “ምንድን ነው? አለ
አንዱ ፖሊስ ጉዳዩን ነገረው
እስክንደር “ያሳሰረን ጉዳይ ይሄ ነው ምን እንደምንፅፍ ማንም አያገባውም”አለ
በጣም ገረመኝ ተመስገን ሲናገር እስክንድር በቦታው አልነበረም በተነሳው ጉዳይ ግን የሰጠው መልስ ከተመስገን ጋር ተመሳሳይ ነው።
ዛሬም እነዚህ ብርቱዎች! ዛሬም እነዚህ ኩሩዎች! ዛሬም እነዚህ ድንቅ የኢትዮጵያ ልጆች ከነ ክብራቸው ከአቋማቸው ዝንፍ ሳይሉ በቆሙበት ልክ እንደቆሙ ይገኛሉ።
ቀን 10:45
መጋቢት 24/2010 ዓም

የፖሊስ መምሪያው አክርሞት (ታሪኩ ደሳለኝ)

ዛሬ መጋቢት 24/2010 ዓም ፖሊስ መምሪያ ስሄድ ተመስገን ተሽሎት አየው ይሆን ወይ? እያልኩ ነበር በጠዋት ቁርስ ይዘን የደረስነው። የመጣነውን ቁርስ እያስቀመጥን “እነ ተመስገን አልኩ” ተጠሩ መሰኮቱ ላይ አይኔን ተክዬ ጠበኩ። የሚጠራው ልጅ ተመስገን እስክንደር እያለ ነው። ዛሬስ ማን መቶ አሞታል ብሎ የሚነግረኝ እያልኩ አስቤ ሳልጨርስ ተመስገን ከነ ፈገግታው እስከርፑን አድርጉ በመስኮቱ ብቅ ሲል አየሁት። ሆኔታው ደና ይመስላል ተመስገን አልኩኝ።
“ተሻለህ?” አልኩት  “ደና ነኝ” አለኝ ደስ ብሎኝ እያወራሁ እስክንደር ነጋ መጣ ተገቢውን ሰላምታ ተለዋወጥን “ዛሬ በማስታገሻም ቢሆን  ደና ነው” አለኝ።
 ስላሉበት ሁኔታ ጠየኳቸው ለውጥ እንደሌለ ነገሩኝ። እነሱ የብርቱ ብርቱ ቢሆኑም በርቱ አልኳቸው። እነ በፍቃዱ እን ይድኔን እነ ስንታየሁን እነ አንዷለም አናገርኳቸው ጥንካሬቸው ደስ ያሰኛል። “አዲስ ነገር ምን አለ?” አልኩኝ ” ክፍላችን ውስጥ ምርጫ አድርገናል”  አሉኝ “የምን ምርጫ?” አልኩኝ እየሳቁ “ኮሚቴ ነው” አሉኝ ዝርዝሩን ነገሩኝ ” በፍቃዱ ሀይሉ የመዝናኛ ሃላፊ፣ እስክንደር ነጋ የስፖርት ሃላፊ እና ተመስገን ደሳለኝ የክፈሉ ሃለፊ አሉኝ”። ይሄ የመደበኛ እስረኛ ባህሪ ነው እንግዲህ ያለ ክስ ቃል ሳይሰጡ እኔ ነኝ ያሰርኳቸው የሚል ተቋም ሳይኖር መታሰራቸውን  ማመናቸው እና ለሁሉም ነገር እራሳቸውን ማዘጋጀታቸውን ተረዳሁ።
ወደ ማህሌትና ወይንሸት ክፍል ሄድኩኝ አየዋቸው መንፈሳቸው ጠንካራ እንደሆነ ያስታውቃል። ስላሉበት ክፍል ተነጋገርን በዚህ ጠበብ ክፍል 17 እንደሆነ ተረዳው ገፋ ቢል ክፍሉ 9 ሰው የሚይዝ ነው ወደዚህ ክፍል ሲመጡ ከነሱ ጭምር 6 ነበሩ ዛሬ 17 ሆነዋል። በማሀል ማህሌት ወደ እስረኞቹ ዞራ አንዲት ልጅን “ነይ ሰለም በይው” አለቻት  ልጅቷ ዛሬም መኖሮ ገራ አጋባኝ እመቤት ትባላለች 10 አመቷ ነው እነ ማህሌት ክፍል ካየዋት ዛሬ 4ኛ ቀኖ ነው። መታ ሰላም አለችኝ። እጅ እጄን ስታዬኝ ማህሌት “ከረሜላዋን ጨረሳለች” አለችኝ “ተመልሼ እመጣለሁ” አልኩት ይቺ የአስር አመት ልጅ ምንም ታድርግ ምንም በዚህ ሁኔታ እስከመቼ እዚህ ልትሆን ነው አልኩ።
ተመስገን ደሳለኝ፣እስክንደር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ ማህሌት ፋንታሁ፣ዘላለም ወርቃገኘሁ፣በፍቃዱ ሀይሉ፣ስንታየሁ ቸኮል፣ ወይንሸት ሞላ፣ይድነቃቸው አዲስ፣ተፈራ ተስፋዬ፣አዲሱ ጌትነት ዛሬም በፖሊስ መምሪያ ውስጥ ተጉረው ይገኛሉ።
መጋቢት 24/2010 ዓም
Filed in: Amharic