>

ዓቢይ አህመድና የኢትዮጵያ ፖለቲካ [ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም]

ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ብቻ ሳይሆን ባለፉት አርባ ዓመታት ውስጥ በግሉ በነጻነት አስቦ በአገር ጉዳይ ቁምነገሮች ላይ እንደዓቢይ አዲስ ነገርና የአስተሳሰብ እንከን የሌለበት ነገር ሲናገሩ አልሰማሁም፤ እኔ የሰማኋቸው ቅጭብጭቦች የዓቢይ ንግግሮች በሙሉ ሰውዬው የማሰብ ችሎታው የጠራ እንደሆነ ያረገጋግጡልኛል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት አርባ ዓመታት ውስጥ እንዲህ ያለ ባለሥልጣን ሰምቼ አላውቅም፤ ስለዓቢይ ብዙ ጥርጣሬዎችን፣ ወቀሳዎችና ነቀፋዎችን አንብብአለሁ፤ ሁሉም የሚያተኩሩት ከዚህ በፊት በነበረው የተመጠነ ሥልጣን ወይም ወደፊት ሊያሳይ ይችላል ተብሎ የተገመተውን ድካም በማጉላትና የድረጅት ተጽእኖን እንደማይቋቋም ከመተንበይ የሚነሱ ናቸው፤ ይህንን ዓይነት አስተሳሰብ አእምሮዬ አይቀበልም፤ በ1983 ዓ.ም. በዋሺንግተን ዲሲ ስለወያኔ ተመሳሳይ አስተያየት ሰጥቼ ነበር፤ በተግባራቸው ስጋት ውስጥ ጨምረው ኢሰመጉን እስከመመሥረት አደረሱኝ፡፡ በዚያን ጊዜ ተሳስቼ የምታረምበትን መሠረት ተከልሁ፤ ብዙ ሰው አልተከተለኝም፤ ሆኖም ድርጅቱ ህልውናው አለ፡፡
አሁንም ቢሆን ወደፊት እሳሳታለሁ ብዬ በመስጋት ዛሬ አውቄ ስሕተት አልሠራም፤ ስለዚህም ነገር ሳላበዛ ስለዓቢይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያገኘሁትን መረጃ በመንተራስ በአጭሩ አቀርበዋለሁ፡…
• በአደባባይ በወያኔዎች ፊት ስለኢትዮጵያ ሕዝብ የተናገረው፣ ስለሥልጣን የተናገረው፣ አዲስና ግሩመረ ነው፤
• ወያኔዎች ተማሩ፣ አልተማሩ፣ በኢትዮጵያ ሀብት ከየኪዮስኩ የምስክር ወረቀቶች ቢገዙም በሃያ ሰባት ዓመታት ያልደረሱበትን የእውቀትና የማሰብ ደረጃ ዓቢይ ከነሱ ስር ሆኖ ባገኘው እውቀት ከመቀመጫው ሳይነሣ በለጣቸው፤ (አንድ ሌላ ወያኔ ያሠለጠነው ወደአሜሪካ ኮብልሏል፤ ) ባለሥልጣኖች ከተማሩበት አገዛዙን ከወደቀበት የአስተሳሰብ አዘቅት ያወጣው ነበር ፡፡
• ወያኔዎች ዓቢይን በጸጥታ ለመስማት መገደዳቸው ከገባቸውና ከተጠቀሙበት ትልቅ ትምህርት ነው፤
• ዓቢይ በወያኔ በራስ አለመተማመን ሕመም ላይ በእግሩ ቆመበት፡፡
• ዓቢይ ብቻውን አይደለም፤ ጓደኛ አለው፡፡

Filed in: Amharic