>

ከስዩም ተሾመ የተላለፈ መለዕክት፦ (በዳንኤል ሽበሺ )

<ለመላው ክርስቲና አማንያን እንኳ ለስቅለተ ዕለትና ለትንሣዔ በዓል በሰላም አደረሰን! በዓሉ የሰላም የደስታ ይሁን! ለሀገራችን መጪው ዘመን ብርሃን፤ ወደ ሰው ልጅ ክብር የምንመለስበት ዘመን ይሁንልን! ፍትህ የሰፈነባት፤ ያለፈውንና አሁን የተቆለለብንን መከራ የምንረሳበት ዘመን ይሁንልን !” ስዩም ተሾመ – ከአአ ፖሊስ እሥር ቤት> በማለት ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ መለዕክቴን አስተላለፍልኝ አደራ ብሎኛልና ይኸው አድርሽያለሁ፡፡
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ፍትህ! ፍትህ! ፍትህ!! ለስዩም ተሾመ!
ፍትህ! ፍትህ! ፍትህ!! ለሁሉም ግፍ እስረኞች!
ወጣቱ ምሁር ስዩም ተሾመ በዋናነት የሚታወቀው በአምቦ ዩኒቨርስቲ በመምህርነት፣ የቲንክታንክ ድሬ-ገጽ ፀሐፊነት፣ የተለያዩ ጥናታዊ ጹሁፎችንና ትንተናዎችን (በተለይ ፖለቲካዊና ማኀ/ዊ ጉዳዮችን) በማቅረብ የሚታወቅ ሲሆን፤ ከታሰረበት ጊዜ ጀምሮ ደንነቱን ጨምሮ ስለ አጠቃላይ ሁኔታ እኛ ጓደኞቹ ስንከታተል ቆይተናል፡፡ ዛሬም እንደ ልማዳችን ወደዛው ማቅናታችን አልቀረም፡፡ <አሁንም ማዕከላዊ አለመዘጋቱን አስተውሰው ከእሱ ጋር ወደ 32 የሚጠጉ እስረኞች ወደ አዲሳባ ፖሊስ ህንፃ እንደተዛወሩ ነግረውናል፡፡ የነፃነት ቀናችን ሩቅ አይሆንም! ፍትህ! ፍትህ! ፍትህ! ፍትህ! ለሀገራችን! ሰላም፡፡

 “ከማዕከላዊ አንወጣም!”   አቶ ታዬ ደንደዓ

 በማዕከላዊ ታስረው የነበሩ እስረኞች በሙሉ በትላንትናው ዕለት ጠዋት ከማዕከላዊ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን  መዘዋወራቸውን ይታወቃል፡፡ ከሰዓት በኃላም እስረኞችን ከጠያቂዎችን ማገናኘትም ተችሏል፡፡
በማዕከላዊ እስረኞቹ “እቃችሁን ያዙ!” ተብሎ ኹሉም ሲዘጋጅ፤ አቶ ታዬ ደንደዓ እና መምህር ስዩም ተሾመ “ከማዕከላዊ አንወጣም!” በማለታቸው በኃይል ተገፍትረው በግዳጅ እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ ከማዕከላዊ አንወጣም ያሉበት ምክንያት ሲገልፁ “ማዕከላዊ ዘጋነው ብላችሁ ፕሮፖጋንዳ ልትሰሩ ነው፤ የምትዘጉት ከሆነ እኛም ነፃ መውጣት አለብን፤ ያለበለዚያ አንወጣም!” ብለው ቢከራከሩም ኹለቱንም በኃይል እንዳስወጧቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከማዕከላዊ ሲወጡ የኦሮሚያ የሚኒሻ ኃላፊ የኾነውን ኮነሬል ኢያሱን ጨምሮ ከ30 በላይ የነበሩ ሲኾን፤ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሲገቡ ከሰንዳፋና ከሰበታ የመጡ ብዛት ያላቸው ወጣቶች ማግኘታቸውን ገልፀዋል፡፡
አሁን ስላሉበት እስር ቤት እነ ስዩም ሲገልፁ፡- በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ 4 ጨለማ ቤቶች አሉ፤ እዛ ውስጥ የሰንዳፋና የሰበታ ወጣቶች ከፍተኛ ድብደባና ቶርቸር እንደ ደርሶባቸዋል፤ በእስረኞቹ ሰውነት ላይ ያለውን ጠባሳ በአይናቸው እንዳዩ፤ ልጆቹም የደረሰባቸውን ቶርቸርና ግርፋት ልክ እንደገቡ እንደነገሯቸው” ገልፀዋል፡፡ እነ ስዩም ከገቡ በኃላ ልጀቹ ማንንም እንዳያገኙ ቀኑን ሙሉ ተቆልፎባቸው የሚውሉ ሲኾን አየር ማግኘት የሚችሉትም፤ ሌሎች እስረኞች ለምሳ በስድስት ሰዓት ላይ ወደ ክፍላቸው ከገቡ በኃላ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡
     ማዕከላዊ ቢዘጋም ገራፊዎቹ ሥራቸውን ቀጥለዋል፡፡
Filed in: Amharic