>

"ትግራይ ካለ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ ካለ ትግራይ ሞተር አልባ መኪና እንደማለት ነው!!!" ዶ/ር አብይ በመቀሌ (ትርጉም በኢዬብ ብርሃነ)

 ዶ/ር አብይ በመቀሌ ሙሉውን ንግግር በትግሬኛ ነው ያደረጉት 

“ትርጉም በእዮብ ብርሀን”
ዶ/ር አብይ በትግራይ ያደረጉት ንግግር የአቶ መለስ ዜናዊን “ይህች አገር የመቶ ዓመት ታሪክ ነው ያላት” ድሪቶ ትርክቶችን አፈርድሜ አስበላው።
”…ትግራይ ማለት የአገራችን ታሪክ እንደ እንጀራ ተለውሶ ኢትዮጵያ ጠላቶች የህፍረት ማቅ ለብሰው የተሰናበቱባት የኢትዮጵያ አካል ናት። የጥንታዊ ኢትዮጵያ መፈጠሪያ መጀመሪያ ብቻ ሳትሆን  የዛሬዋም ኢትዮጵያ ማገር የሆነች ክልል ናት። …
ብዙዎች እንደሚሳማሙበት ትግራይ የኢትዮጵያዊነት መድሃኒት የተቀበረባት ምድር ናት።
ትግራይ የአገራችን ታሪክ መኩሪያና ስልጣን መፈጠሪያ የሆነው የአክሱም ሃውልት የተሰራባት ምድር ናት።
ትግራይ በነጃሺ አድርጎ የእስልምናና የክርስትና ምድር ናት።
ትግራይ የማንነታችን የነጻነታችን መሰረት የሆነው አድዋ ያለባት ክልል ናት።
የ3 ሽህ ዓመታት ያስቆጠረው ታሪካችን መሰረት የሆነው ከሽሬ ማይ አድራሻ አካባቢ  የተገኘባት ናት።
ትግራይ ዘረያእቆብና ማህሌታዊ ያሬድን የመሰሉ ታላላቅ ሊቃውንትን ያፈራች ናት።
.
ትግራይ ካለ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ ካለ ትግራይ መኪና ካለ ሞተር እንደማለት ትርጉም የለውም።
የትግራይ ወጣቶች የዓያቶቻችሁን ታሪክ ጠብቃችሁ ጽናትን፣ ሕዝባዊ ፍቅርን ያዙ፣ የአገራችሁ ዋልታ ሁኑ፣ ድህነትን ለማጥፋት ታገሉ…።
የትግራይ ሕዝብ በጥሩም ሆነ በመጥፎም ወቅት በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር ሕዝብ ነው። በጭቆና ውስጥ እንኳን ከሌላው ህዝብ ጋር አብሮ ዴሞክራሲ ለማጣት የሚታገል ሕዝብ እንጂ፣ በኢትዮጵያዊነቱ ፍጹም የማይደራደር በደሙ ውስጥ የሰነቀ ኢትዮጵያዊነት የሰነቀ ሕዝብ ነው።
አንዳንድ ቦታዎች በኦሮሚያና በአማራ በተፈጸሙት አዝነናል። በኦሮሚያና አማራ አንዳንድ ችግሮች ሲፈጠሩም አጋርነታቸውን ሕዝቡ አሳይቷል። ሕዝባችን ለተፈናቃዮች አዝመራ ሰብስቦ አጋርነቱን አሳይቷል። ይሄ የአንድ አማራ አርሶአደር ታሪክ ነው።
ማነው ከማን ጋር ነው ያልተሳሰረ? ኢትዮጵያ በአሸዋ ላይ የታነጸች የምትፈርስ አገር ሳትሆን በመሰረት ላይ የተገነባች አገር ናት።
እንግዳ አክባሪ ሕዝብ ነው። የትግራይ ሕዝብ በዘር ሳይመርጥ ከሁሉም ጋር የሚዛመድ ሕዝብ ነው። ከማንም ጋር የሚጋጭበት ታሪክ የለውም። ይህን ልንጠብቀው ይገባል።
በቅርቡ የተፈናቀሉ አሉ። በሁሉም የአገራችን ክልል ዜጎች የትም ሄደው መስራት እንደሚችሉ መረጋገጥ አለበት።
የትግራይ ሕዝብ እንደ ቀድሞው ከወንድሞቻችን የኤርትራ ሕዝቦች ጋር እንደቀድሞው የነበረውን ወንድማማችነት ወደ ነበረበት ለመለስ ከኤርትራ መንግስት ጋር በሰላማዊ መንገድ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
…. ክብር ይስጣችሁ ያቅነለይ፣አመሰግናለሁ፣ ገለቶማ!”
Filed in: Amharic