>
5:13 pm - Friday April 20, 7962

አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ መካር የለውም? (አቻምየለህ ታምሩ)

አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ  በወያኔ ሜዲያዎች እየወጣ በሚናገራቸው አስተያየቶች  በኢትዮጵያ ሕዝብ ቁስል ላይ እንጨት እየሰደደና በሕዝብም እየተጠላ መሆኑን የሚነግረው መካር የለውም?  መለስ ዜናዊ  ሲሞት ከእለት እስከ አርባ እየተመላለሰ ያለቀሰው «የአገር ሽማግሌው» አትሌት ኃይሌ የሕዝብ ልጅ የሆኑት እነ  እነጫልቱ ታከለ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ ኦኬሎ አኳይ፣ ዘሪሁን ገብረእግዚአብሔር፣ ማሙሸት አመማረ፣ ወዘተን ለምን እንደታሰሩ ያውቃል?  ጎብኝቷቸውን ያውቃል? እስር ቤት መሄድ ባይቻለው፣ ተፈቱ ሲባል በአካል ሄዶ መጠየቅ ባይችል ደውሎ ደስታውን ገልጿል? ነው የነ ኃይሌ «የአገር ሽማግሌነት» ወያኔ ለሚሰጣቸው የቤት ስራ  ብቻ መላላክ ነው? 12 አመታት ፈርደውባት ያንን ከጨረሰች በኋላ ደግሞ እንደገና በግፍ አስረዋት በቅርቡ ከጠባቡ እስር ቤት የወጣችው ጫልቱ ታከለ  የተናገረችውንና ፍጡር የሆነን ሁሉ የሚያሳምም የማጎሪያ ቤት ዘመን ቆይታዋን  አትሌት ኃይሌ ተመልክቶ እንደሁላችን ታምሞ ይሆን?
ለመሆኑ አትሌት ኃይሌን «ንጉሥ» ያደረጉት  ኢትዮጵያውያንስ  ላለፉት  አመታት  በሺዎች የሚቆጠሩት በትግራይ ወታደሮች በግፍ የተረሸኑት፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩት ንጹሐን  ደግሞ የትግራይ መርማሪዎች እንደ ክርስቶስ እየሰቀሉ፣ ሴቶችን ራቁታቸውን እያደረጉ፣ የእግርና የእጅ ጥፍራቸውን  እያወለቁ፣ ብልታቸው  ላይ  ውሃ የተሞላ ጠርሙስ እያንጠለጠሉ፣ መነኮሳትን ከገዳም እያወጡ ማጎሪያ  ቤት ውስጥ የሚያሰቃዩዋቸው አፋኝ አዋጆች እየተጠቀሱ መሆኑን ኃይሌ አያውቅ ይሆን?
እንዴት በሕዝብ ዘንድ «ንጉሥ» የሚል ክብር የተሰጠው ሰው  ኢትዮጵያውያን ከባድ የሕይወት መስዕዋት እየከፈሉበት ያለውን  የወያኔን የፀረ ሽብር ህግ፣ የፕሬስ አዋጅና ሌሎች አፋኝ አዋጆች  አለም ሁሉ እንዲሰረዙ እየጠየቀ  እሱ  ወያኔ የማህበራዊ ሚዲያን  እንዲቆጣጠር የሚያስችለው  ሌላ የአፈና  ሕግ ያወጣ  ዘንድ  ይወተውታል? ይህ በግልጽ የሚያሳየው  አትሌት ኃይሌና መሰሎቹ ከሕዝብ ርቀው አገዛዙ ጉያ ስር ስለሚውሉ  የኢትዮጵያ ችግር የአፈናና የጭካኔ አገዛዝ ውጤት መሆኑን አለመገንዘባቸውን ነው።  አትሌት ኃይሌ የኢትዮጵያን ሕዝብ ችግር ሳይገነዘብ  የሚሰጠው  «የመፍትሔ ሃሳብ» ደግሞ  ቀውሱን  የሚያባብስ እንጂ ፈውስ እንደማይሆን፤ እሱንም ጨርሶ በሕዝብ ዘንድ እንዲተፋና እንዲጠላ  እያደረገው መሆኑን የሚነግረው ወዳጅ ቢኖረው   ለኃይሌ ትቅል  ውለታ እንደዋለለት የሚቆጠር ይመስለኛል።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1794740577214550&id=100000358765743

Filed in: Amharic