>

መልእክት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ [አቶ በቀለ ገርባ]

አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ እንዳሉት ሰላም ከፍ ባለ ድምጽ ተራራ ላይ ወጥቶ በመጥራት አይመጣም። ሰላም እንዳይኖር ያደረገው የኢህአዴግ አገዛዝ ነው። ህዝቡማ ምንጊዜም ሰላም ወዳድና ሁሌም ሰላማዊ ነው። ስለዚህ ህዝቡ ለሰላሙ ዘብ ይቁም ብሎ ጥሪ ማድረግ እምብዛም ቦታ የለውም። በመሆኑም እውነተኛ ሰላም እንዲሰፍን ከተፈለገ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጽፈት ቤቱ ተመልሶ ፣ ካቢኔውን ሰብስቦ በኣራት ነገሮች ላይ ውሳኔ መስጠት ነው።

👉🏻 የሰላም ጠንቅ የሆነውን የኣስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማንሳት፣

👉🏻 የህዝቡን የልብ ትርታ ለማየት የፖለቲካ እስረኞችን በችርቻሮ መፍታትን አቁሞ ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች በኣስቸኳይ እንዲፈቱ ትእዛዝ ማስተላለፍ፣ ከሃያ ሰባት አመታት ጀምረው በጨለማ ቤቶች ውስጥ ታጉረው የሚሰቃዩ በኦነግ ስም የታሰሩትን ጨምሮ ።

👉🏻 በየመንደሩና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ተበትነው ሰላም የሚነሱትን የመከላከያና አጋዚ ጦር ወደ ካምፓቸው እንዲመለሱ ትእዛዝ ማስተላለፍ።

👉🏻 ከእውነተኛ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር እውነተኛ ድርድር ለማድረግ ለሁሉም በግልጽ ይፋዊ ጥር ማድረግ።

እነዚህ አራት መሰረታዊ ጉዳዮች ትክክለኛ መልስ ካገኙ ህዝቡ ለሌሎች ጥያቄዎቹ መልስ ጊዜ ሊሰጥ ይችላል። ሰላም የሚመጣውም ያኔ ብቻ ነው። ህዝብ ሰላም የሚያጣው ጦርነት ስላለ ብቻ አይደለም። የኢትዮዽያ ህዝቦች ጦርነት ሳይኖር ሰላም አጥተው ለዘመናት እየኖሩ ናቸው። በተለይም በኢህአዴግ የኣገዛዝ ዘመናት የሃገሪቱ ህዝቦች ሌላው ቀርቶ የኣእምሮ ሰላም ለማግኘት አልቻሉም። ስለዚህ ምናልባት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግጭት ከለሌ ሰላም ይኖራል ብሎ አስቦ ከሆነ ፍጹም ስሕተት ነው። ሰላም እንዲኖር ዳር ዳር መሄድ ሳይሆን የህዝቦችን ጥያቄ መመለስ በቂ ነው።

ምንጭ

ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳ

Via: Gizachew Soboksa

Filed in: Amharic