>
5:13 pm - Wednesday April 19, 5189

የኢትዮጵያ ህዝብ የሽፋን እና የስውር መንግስቱን ለይቶ ማወቅ አለበት (ዶ/ር ብርሀነ መስቀል አበበ) 

በኢትዮጵያ ሁለት መንግስታት አሉ። አንደኛው ህወሃት የኢትዮጵያ መንግስት እያለ የሚጠራው   የውሸት መንግስት ሲሆን ሌላኛው ከውሸት መንግስቱ ጀርባ በህወሃት ታጣቂዎች፣ ሰላዮች፣ ነጋዴዎችና ሙሁራን የሚመራው የስውር መንግስት ነው።
የውሸት መንግስቱ አለማ የኢትዮጵያ ህዝብን በመደለል የህወሃትን የፓለቲካና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት መረጋገጥ ነው። የስውር መንግስቱ አለማ የውሸት መንግስቱን መዋቅሮችና ፓሊሲዎች ለህወሃትና ተባባሪዎቻቸው የኢኮኖሚና የፓለቲካ የበላይነት ለማረጋገጥ መስራት ነው።
 የውሸቱ መንግት መሪዎች እንዳሉ ኦሮሞዎችና አማራዎች ሲሆኑ ከፊል ዝርዝራቸውን እንደሚከተለው ማየት ይቻላል። እነዚህም፣
 1ኛ፣ ፕሬዚደንት –ኦሮሞ
2ኛ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሪ –ኦሮሞ
3ኛ፣ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር — አማራ
4ኛ፣ የፓርላማ አፈ ጉባኤ — ኦሮሞ
5ኛ፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሪ — ኦሮሞ
 6ኛ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ቃላ አቀባይ — ኦሮሞ
 7ኛ፣ ገንዘብ ሚኒስትር — ኦሮሞ
8ኛ፣ መከላከያ ሚኒስትር — ሲልጤ
 9ኛ፣ ፍትህ ሚኒስትር — አማራ  እያለ የውሸት መንግስቱ ዝርዝር ይቀጥላል።
ማንም ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው በተግባር ገና ከልተፈተነው  የዶ/ር አብይ ስልጣን በስተቀር ሁሉም የውሸት መንግስቱ ቦታዎች ወይ በባዶ ደሞዝ በልታዎች የተያ ወይም የህወሃት እጅ አዙር አገዛዝ ቃለ አቀባዮች የተያዙ ናቸው።
በተቀራኒው የስውር መንግስቱ መሪዎች እንዳሉ ሁወሃቶች ብቻ ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝብ አብዛኞቹን የስውር መንግስቱን መሪዎች እንኳን መልካቸውን ትክክለኛ ስማቸውንም አያውቅም።
ስውር መንግስቱ መዋቅር እውነተኛ መገለጫ ኮማንድ ፓስት ተብሎ የተዘረገው የህወሃት ወታደራዊና የስለላ መዋቅርና ተባባሪዎቻቸው ናቸው።
የኮማንድ ፓስቱ አደረጃጀትና መዋቅር የኢትዮጵያ ህዝብ የራሱ መከላከያ፣ ደህንነትና ፓሊስ እንዳሌለው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።  ይህ መዋቅር የውሸት መንግስቱ መዋቅር እውቅናና ፍቃድ ውጭ የተዋቀረ ህወሃት ብቻ የሚቆጣጠረውና ሲፈልግ activate የሚያደርገው ስውር መንግስት ነው።
በ1991 የኢትዮጵያ ህዝብና የወቅቱ የፓለቲካ መሪዎች በነዝላልነት ከመቶ  ሃያ አመታት በላይ እድሜ ያለውን የኢትዮጵያ መከላከያ “ህወሃት የደርግ ወታደር ብላ” ስትሰይመውና ስታፈርሰው  በመቀበል አሁን መከላከያ አልባ አገርና ህዝብ እንድንሆን እንዳደረገን አምኖ መቀበል ከዚህ ውርደት ለመውጣት የመጀመሪየው እርምጃ ነው።
 ከሃያ ሰባት ዓመታት ጥበቃ በኃለም የህወሃት ታጣቂዎች የኢትዮጵያ መከላከያ ይሆናሉ ብሎ የሚጠብቅ ኦሮሞ ወይም አማራ ከለ ከአንድ ሚልዮን በላይ የኦሮሞ ህዝብ በ2017 ብቻ በነዚህ የህወሃት ታጣቂዎች መሬቱንና በብዙ ቢሊዮን የሚገመት ንብረቱን ተዘርፎና ተቀምቶ ሲሰደድ ያላየ ወይ ያልሰማ ወይም አውቆ የተኛ ጅል ብቻ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ መሬት፣ መሬት የመንግስት ነው በሚል የሸፍጥ ፓሊሲ ምክንያት የአባቶቻችንና የኛ የልጆቻቸው  መሬት ተቀምቶ የህወሃቶች ስውር መንግስት የግል ንብረት ሆኗል።
 በኦሮሚያ ከሶስት ሚልዮን ግማሽ በላይ የኦሮሞ ህዝብ መሬት በህወሃትና ተባባሪዎቻቸው ተወስዷል። በጋሚቤላና በቤኒሻንጉል ከግማሽ በላይ መሬታቸው በህወሃቶች ተነጥቋል። በአማራ የወሎና የጎንደር መሬቶች በህወሃት ትዕዛዝ ወደ ትግራይ ተካለዋል። በደቡብ ኢትዮጵያ በልማት ስም ለመስኖ ምቹ የሆኑት መሬቶች ሁሉ በህወሃቶች ተወስደዋል። የአዲስ አበባ ነባር ሰፈሮች ፈርሰው መሬታቸው በህወሃቶችና ተባባሪ ሌቦች ተቀምቷል።
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ “መሬት ላራሹ!” ብሎ በ1966 ቱ አብዮት የሞተለት ትግል አሁን ” መሬት ለህወሃት!” በሚል ተተክቶ የአገሩ መሬት ሁሉ የህወሃት ስውር መንግስት መሬት ሆኗል።
 የኢትዮጵያ ህዝብ የአገሩና የመሬቱ ባለቤት ለመሆን እንደገና ስርነቀል አብዮት ማድረግ አለበት።
የሌሎች ብሄር ነባር  ነጋዴዎች ከገበያ አውጥተው፣ የኢትዮጵያ  የገቢና የውጭ ንግድ እንዳለ  በህወሃቶች ተቀምቷል  ማለት ይቻላል።
የኢትዮጵያ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ማለትም  መብራት ኃይል፣ቴሌ፣ አየር መንገድ፣ አውራ ጎዳናና የመሳሰሉት በሙሉ በህወሃት የተያዙ ናቸው።
የመንግስት መ/ቤቶችና የከተማ መዘጋጃ ቤቶች በሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆኑ የህወሃት የፓላቲካና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት  አገልጋይ ሆነዋል።
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ መንግስት የለሽ ህዝብ ሆኗል። ያለው የውሸት መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ ለመሸወድና ከጀርባ ያለውን የህወሃት ስውር መንግስት ጥቅም ለማስጠበቅ የቆመ ኮፈን ነው።
ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን ኮፈንና ከጀርባው ያለውን ስውር የህወሃት መንግስት  አፈራርሶ የራሱን መንግስት ማቋቋም አለበት።
የኢትዮጵያ ተቃዋሚና ተራማጅ ኃይሎችም የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል በውሸት መንግስቱ በሚመራ የውሸት ምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብ የፓለቲካ ስልጣን በለቤት ይሆናል ብሎ ራስንም ሆነ ህዝብን ከማታለል ወጥተው ህዝቡ  ይህን ስውር የህወሃት መንግስት በማፍረስ  የራሱን መንግስትና መከላከያ ለማቋቋም በሚችልበት መልኩ  እየተቀኘ እንዲሄድ  ማድረግ የግድ ይላል።
Filed in: Amharic