>

እውን አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ነው? (ጌታቸው ሽፈራው)

ከሁለት አመት በፊት ነው! የትህነግ/ህወሓት ባለሀብቶች ብረት በርካሽ ዋጋ ይፈልጋሉ። ሊሸጡት ነውኮ! ሲያስቡ በህሊናቸው ከትህነግ ጎን በመሆናቸው ብቻ እንደቤታቸው የሚያዩት አየር መንገድ ይመጣላቸዋል። ወደ አየር መንገዱ ኃላፊ ተወልደ ዘንድ ይሄዳሉ። የጋራዡን ጉዳይ የሚቆጣጠረው ሰው እንዲጠይቁት ይልካቸዋል።
የጋራዥ ኃላፊውን ሲጠይቁት ፈቃደኛ አልሆነም።  ብረቶቹ የሚመጡት ከቀረጥ ነፃ ነው። ከአየር መንገዱ ብቻ ነው። የትህነግ ባለሀብቶች ደግሞ ይህን በነፃ የመጣ ብረት በውድ መሸጥ ይፈልጋሉ።
በእርግጥ በግላቸው አይደለም የጠየቁት። የብረታብረት ኮርፖሬሽን እንደሚፈልገው አድርገው ሰነድ አቅርበዋል። የጋራዡ ኃላፊ አልፈቅድላቸው ሲል ወደ ተወልደ አቀኑ። ተወልደ ለጋራዥ ኃላፊው ደብዳቤ ፃፈ! ይሰጣቸው ብሎ! የጋራዥ ኃላፊው ደብዳቤውን ይዞ ብረቱን እንዲወስዱ አደረገ። ምን አማራጭ አለው?
ከጊዜ በኋላ ጉምሩክ ከአየር መንገድ ውጭ ማንም የማያስገባቸው ብረቶችን መርካቶ ያገኛል። የአየር መንገድ ጋራዥ ኃላፊው ይታሰራል። እሱ የተወልደን ደብዳቤ ይዟል። ስለዚህ ነፃ ተባለ። ወደ እነ ተወልደ መዝለቅ አይቻልም።
~ኃይለመድህን አበራ አውሮፕላን ይዞ የጠፋው ሀገሩን ስለሚጠላ አይደለም። አየር መንገዱ የአንድ ቡድን ስለሆነ ነው! የትህነግ! የቡድን፣ የትህነግ!
~አንድ ቴክኒሻን ለምን  ከነዳጅ በርሜል ስር ተደብቆ ጠፋ? አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ስላልሆነ ነው! በዓዳ ከሆነ ቆይቷል!
~ለመሆኑ አንድ የአየር መንገድ ቴክኒሻን፣ ፓይለት፣ ሌሎችም ሰራተኞች የሚከፈላቸው አየር መንገዱ ከሚያገኘው ገቢ ጋር ሲነፃፀር  ብዝበዛው በባርነት የመኖር ያህል አይደለም?
የኢትዮጵያ ብሮድብካስት ባለስልጣን
በኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን የበረራ ተቆጣጣሪዎች ችግር ምክንያት የቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ የበረራ አገልግሎት መስተጓገሉ ተገለጸ፡፡
የኤርፖርቶች ኦፕሬሽን ማናጀር አቶ ንጉሴ ሙሉጌታ በሰጡት መግለጫ የበረራ ሰራተኞቹ ተቃውሟቸውን ማሰማት የጀመሩት ከትላንትናው እለት ጀምሮ ነው ብለዋል፡፡
እናም በአሁኑ ሰዓት የአየር መንገዱ አለም አቀፍ በረራዎች ሙሉ በሙሉ መቆማቸውን ነው የተናገሩት፡፡
የሲቪል አቪዬሽን ዋና ዳይሬክተር ኮ/ል ወሰንየለህ ሁነኛው በበኩላቸው አለም አቀፍ በረራዎቹ ሙሉ በሙሉ የተቋረጡ ሳይሆን አሁን በተፈጠረው ችግር የበረራ መስተጓጉል ነው ያጋጠመው ብለዋል፡፡
ይህንንም በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚስተካከል ነው የተናገሩት፡፡
የበረራ ተቆጣጣሪ ሰራተኞቹ የሚያቀርቡት ጥያቄ ከበዓል ቀናት አበል ክፍያ እና ሌሎች ጉዳዮች መሆኑን ነው ኮ/ል ወሰንየለህ ሁነኛው የገለጹት።
Filed in: Amharic