
ይሄኔ ይሄንን አድማ የመቱት ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃ ዜጎቹ ብንሆን ኖሮ ጥያቄያችን እንኳን በ24 ሰዓታት ውስጥ ሊፈታ፣ ሊመለስ፣ ሊከበር፣ ሊስተካከል ይቅርና በገፍ ከመባረር በተጨማሪ የመንግሥት ሥራ በማስተጓጎል ወንጀል እንዲያም ሲል በአሸባሪነት ተከሰን ዘብጥያ እንወርድ ነበር፡፡ እነሱ ስለሆኑ ግን የሆነው ሆነ “ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች!” አይደል የሚባለው? ሕገወጥ ክፍያውን አግዶት የነበረው አካል ግን መከራውን ማየቱ ነው፡፡
በእውነት! ያውም በዚህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት እንዲህ ዓይነት ድፍረት ተገኝቶባቹህ ልትማሩ??? ሆሆ ፍዳችሁን ነበረ እንጅ የምትቆጥሩት!!!
አየ አንች ሀገር!
ለወርቆቹ ወርቅ ምድር፤
ለተቀረው ሀገረ አሳር፤
እኮ እስከመቸ ይቻል ይህ ቀምበር???
ፍትሐዊ ካልሆነ አምባገነን ሕግ ፍትሕ አይገኝም
ዉብሸት ሙላት
የሥራ ማቆም መብትን በተመለከተ የኢትዮጵያ የአሠሪና ሠራተኛ ሕግ ‘አምባገነንም አምባግናኝም’ ነው። በአዋጅ ቁጥር 377/96 የአየር መንገድ አገልግሎት “እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ አገልግሎት” ተብሎ በአንቀጽ 136 (2) (ሀ) ላይ ስለተገለጸ በአንቀጽ 157(3) መሠረት በአየር መንገድ አገልግሎት የተሰማሩ ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ ማድረግ እንደማይችሉ ደንግጓል። ሕጉ በራሱ አምባገነን ስለሆነ ሊሻሻል ይገባዋል፤የሥራ ማቆም አድማ ያደረጉ የሲቪል አቪየሽን ሠራተኛ ወገኖች ላይ ምንም ዓይነት አሉታዊ እርምጃ ሊወሰድ አይገባም፤ ምክንያቱም ፍትሐዊ ካልሆነ አምባገነን ሕግ ፍትሕ አይገኝምና።