አሳዛኝ ዜና

ታምራት የሙዚቃ ሕይወቱን ፈር ያስያዘለትን እንቅስቃሴ ማድረግ የጀመረውም ድሬደዋ ከተማ ውስጥ ”ጨርቃጨርቅ” በተባለው የሙዚቃ ኪነት ቡድን ውስጥ በአማተርነት በማገልገል ነው። በ1999 አ.ም ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመምጣት ካዛንቺስ “ሀይልዬ ታደስ የምሽት ክለብ”ውስጥ ስራውን አሀዱ ብሎ ጀመረ። ከዛም ብዙም ሳይቆይ ”ሃኪሜ ነሽ መድሃኒቴ” በሚል ነጠላ ዜማ ለቀቀ። በመቀጠል ሁለተኛውንና በይበልጥ በሕዝብ የተወደደባችውን ”አንለያይም” እና “ካንቺ አይበልጥም” የተሰኙ አልበሞቹ ለአድማጭ ተመልካች አድርሰቀል። የመጨረሻ የሆነውን ስራውን አራተኛው አልበም “ከዛ ሰፈር” የተሰኘውን እንዳወጣም የሚታወስ ነው።
ታምራት ደስታ ባለትዳርና የልጆች አባትም ነበር።
ከታምራት ደስታ ጥዑመ ስራዎች መካከል:-
‘’ፀፀት ታቅፌ ብቻዬን… በናፍቆት ልቤ ሲላላ
በረዶ ቤቴን አየሁት ጓዳው ካሁኑ ሲላላ
ልቤን እምቢ አለው.. ብዙ ነው ነውጤ
ንጹህ ሰው ገፋኝ እያለኝ ውስጤ
አውቃለሁ በኔ ልብሽ ቢደማ
ይቅር ለእግዚአብሔር ማለት አይከፋም
አይቁረጥ ልብሽ ይዞ ጥላቻ
ማሪኝ የኔ አለም… የዛሬን ብቻ
ውበት ሸማዬ የክብር አርማዬ
ማሪኝ አልሙትብሽ
ምን አለኝ ሌላ ኩራቴ የምለው
ልታመን በፍቅርሽ
እመኚኝ ፍቅሬ እምላለሁ ቃሌን በአምላክ ስም እሰጣለሁ
አንቺን ብቻ ስል ዘውትር ታምኜሽ እኖራለሁ
ሲገርፈኝ ባየሽ ሀዘን መከራው
እያሳደደኝ የራሴው ሥራ
መች ሕሊናዬ እረፍ ይለኛል
ባሰብኩሽ ቁጥር ያቃጥለኛል’’
ለቤተሰቦቹ መጽናናትን እንመኛለን!!!