>

የማያልቅ ሰቆቃ! (ጌታቸው ሽፈራው)

 አብይ ሶማሊ ሄደ፣ የጦሩ አናቶችም ጋር ሄደ። እነዚህ ሰዎች ግን የሚመለሱ አይደሉም። ዛሬም ንፁሃን በፈንጅ አለቁ።
እመኑኝ! አብይን እጅ ወደላይ ያሰኙታል። የደህንነትና መከላከያ መዋቅሩ የእነሱ ነው። ለስሙ አብይ የጦሩ አዛዥ፣ የደህንነቱ አዛዥ ነው። እንደጠቅላይ ሚኒስትር። የትህነግ/ሕወሓት ሰዎች ሲፈልጉ አምቦ፣ ሲፈልጉ ወልዲያ፣ ወይንም ሀረር አሊያም ጎንደር አመፅ የመሰለ ነገር እንዲቀሰቀስ ያደርጋሉ። አብይ “አረጋጉ” ብሎ ይፈርማል! እነሱ ደም በደም አድርገውት ይመለሳሉ! ያዘዘው አብይ ነው!
በአብይ ዘመን ብዙ ገና ብዙ ነገር ያደርጋሉ! ሁለት ድምፅ ያገኙት አብይ ተማርሮ ሁለት እጁን አውጥቶ “በቃኝ”  እንዲል ያስገድዱታል!
ከጅምሩ ከሕዝብ አላትመውታል። በወልቃይት! ዛሬም ቀጥሏል። ንፁሃን ኦሮሞዎች ተገድለወል፣ ቆስለዋል!  የአብይን ተስፋ ገና ያጨልሙበታል! ይህን ለማድረግ ከበቂ በላይ አቅም አላቸው፣ ልምዱም አላቸው! የሚያሳዝነው ንፁሃን ማለቃቸው ነው!
Filed in: Amharic