
…
የእኛን ጥቅም በተመለከተ ጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ሲያራምድ ከነበረው ፀረ አማራ አቋም ፈፅሞ የተለየ ነው። ለማነፃፀር ሁለት ምሳሌዎችን ብቻ ላቅርብ።
…
1ኛ~ የሱዳንን መሬት ወረራ በተመለከተ።
ሀይለማሪያ ደሳለኝ በጎንደር በኩል ስላለው በሱዳኑ ጦር ሰራዊት የተወረረ መሬት በፓርላማ ሲጠየቅ እጅግ በሚያሳዝንና በሚያናድድ ሁኔታ << የበጠበጡትና የሱዳንን መሬት የወረሩት የጎንደር ሽፍቶች ናቸው> > ብሎ እንደነበር መርሳት የለብንም። በፓርላማ ላይ ለአገሩ እየሞተና መሬቱን ላለማስነካት መስዋእት የሆነን ህዝብ “ሽፍታ ” ብሎ መጥራት እጅግ አሳፋሪና በታሪክም ሆነ በሞራል ይቅር የማይባል ወንጀል ነው።
በአንፃሩ አቢይ አህመድ ስለዚሁ የድንበር ጉዳይ ሲጠየቅ የኢትዮጵያን ጥቅም ባስከበረ መልኩ በአስቸኳይ እንደሚፈታው አስረግጦ ተናግሯል።
…
2ኛ~ የወልቃይትን ጉዳይ በተመለከተ።
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ስለወልቃይት ሲጠየቅ በፓርላማም ሆነ በጋዜጣዊ መግለጫ ” ኢትዮጵያ ውስጥ የማንነት ጥያቄ ሙሉ በሙሉ መልስ አግኝቷል ። በዚህም መሰረት የወልቃይትም ጉዳይ ቀድሞ የተመለሰ ስለሆነ የማንነት ጥያቄ ሊቀርብ አይገባም ።”” በማለት ተናግሯል።
አብይ አህመድ ይሄን የሀይለማሪያምን አይን ጋርዶት የነበረ አሻጥር በመግፈፍ ለወልቃይት የማንነት ጥያቄ እውቅና ሰጥቷል ። በወልቃይት ጉዳይ አብይ ትልቅ ድልድይ ተሻግሯል ።
…
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የወልቃይት ማንነት ጥያቄ በህገመንግስቱ መሰረት መልስ ያገኛል ሲል በህገመንግስቱ መሰረት የወልቃይት ጉዳይ የወልቃይቴውች እንጂ አረም ለማረም የመጡ የሰፋሪዎችን ድምጽ እንደማያካትት መታወቅ አለበት ።
ከ20 አመታት በፊት የስልጤዎች የማንነት ጥያቄ በህገመንግስቱ መሰረት ሲመለስ ስልጤ ማንነት ብቻ ያላቸው ሰዎች በተሳተፉበት ሁኔታ ብቻ ነው። ስለሆነም የወልቃይቴዎች የማንነት ጥያቄ የሚስተናገደው Exclusively በወልቃይቴዎች ብቻና በወልቃያቴዎች ብቻ ነው ። ይሄ መታወቅም መሰመርም አለበት።
…
በእኔ እምነት አብይ ከፖለቲካ አንፃር ትልቅ ድልድይ ተሻግሯል ። መርህ አልባና ሳይንሳዊ ያልሆነ ትችት የትም አያደርሰንም ። አብይ ነገ ጧት ወልቃይትን በስጦታ ወረቀት ጠቅልሎ እንድሰጠን የምንጠብቅ ከሆነ ተሳስተናል። ከአብይ የሚጠበቀው የመጫዎቻ ሜዳውን Fair እንዳደርግልን ብቻ ነው ። መጫዎቻው ፌይር ከሆነ በወልቃይት ጉዳይ አማራ በታሪክም ፣ በህግም ሆነ በጉልበት ተጋጣሚውን 60 ለ 0 በሆነ ውጤት የሚያሸንበት እንደሆነ አምናለሁኝ።
