>

የይስማከ ወርቁን ውለታ የመመለስ ጥሪ ! (ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ)

     ድሮም ለሕይወት ጉጉ አይደለሁም ። ምንም ነገር አያጓጓኝም ። በሕይወት ውስጥ ከደስታ ሀዘን እንደሚበልጥም አስባለሁ ። ዛሬ ግን ከነዚያ ሁሉ የከፋ ይመረረ ሀዘን ስሜት ነው የተሰማኝ ። መጽሐፍ በዚህ ዘመን አይሸጥም በሚባልበት ፣ 20 ሺህ አሳትሞ መሸጥ ብርቅ በሆነበት በዚህ ዘመን 200 ሺህ ኮፒ መሸጥ የቻለ ፣ በአጭር ዓመት የመጽሐፍ ህትመቱን ኢንዱስትሪ መምራት የቻለው የ13 መጻሕፍት ደራሲ ይስማከ ወርቁ በደረሰበት የመኪና አደጋ መናገር ተስኖት ማየት ልብ ያደማል ።
       ካለመናገርም በላይ በስርዓት ማሰብ አለመቻል ፣ ለተደራራቢ ህመሞች መዳረግ ውስጥን ያቆስላል ። ስንቱን እንዳልጻፈ ፣ መጻሕፍቱ በጉጉት እንዳልተጠበቁ ፣ ማሳተሙ ቀርቶ ገና ጽፎ ሳይጨርስ የሽያጩ ገንዘብ ተቆጥሮ እንዳልተሰጠው ይስማከ ዛሬ ሕይወት ርቃዋለች ። ወደ ውጭ ሄዶ ይታከም ዘንድ የኢትዮጽያውያን ውለታ መላሽነት ይጠበቃል ። ይስማከን አሳክሞ ወደ ጤንነቱ መመለስ ውለታ መስራት ሳይሆን ውለታውን መመለስ ነው ።
የባንክ ቁጥሩ (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ )
1000243275408
ስልክ ቁ. 0904388666
Filed in: Amharic