>

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ነገር. . . (ክፍል ፩) - [አቻምየለህ ታምሩ]

ብሔተኝነት የሚባለው ነገር  የኢትዮጵያ ችግር የሚሆነው አማራ ብቻ ሲያነሳው የሆነ ይመስላል።  በርግጥ እኔ ብሔርተኛነት የሚባለው  የነገድ  እንቅስቃሴ አቀንቃኝ  አይደለሁም። የነገድ ብሔርተኛነትን የማላቀነቅነው ብሔርተኛነት የሚለው  የፖለቲካ  እንቅስቃሴ  ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ  የገባባበትንና ሕጋዊ የሆነበትን አውድ ስለማውቅ ነው። ነገር ግን ብሔርተኛነትን ጉዳይ  ከአማራ የመደራጀት አስፈላጊነት ጋር መለያየት ይገባል፤ የአማራ በአማራነት መደራጀት የአማራ ብሔርተኛነት ማራመድ ማለት አይደለምና።
አማራ የሚኖረው ሊያጠፉትና በመቃብሩ ላይ አገር ለመመስረት በታገሉና ዛሬም እየተጋሉ ባሉ የትግራይ  አውሬዎች ተከቦ ነው። በአውሬ ተከቦ የሚኖረው አማራ ራሱን የማይከላከል ከሆነ እጣ ፋንታው እየተበላ ማለቅ ብቻ ነው። አማራ በአውሬ መካከል ሲኖር  ተበልቶ ላለማለው ራሱን ሊከላከል የሚችለው ራሱን ካደራጀና የሚበሉትን ጨካኝ  አውሬዎች መከላከል ከቻለ ብቻ ነው።  ለዚህም ነው የአማራ መደራጀት ጉዳይ የህልውና ጉዳይ እንጂ ፖለቲካ የማካሄድ ጉዳይ አይደለም ስንል የከረምነው።
ከሰሞኑ  ሲስተጋባ የተመለከትነው  የአገዛዙ  ፖለቲከኞች  ንግግር ግን በእውነቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምን ያህል ከአማራ አንጻር እንደቆመ  በድጋሜ ያረጋገጠ ማሳያ ነበር። ይህንን  አስተያየቴን አንድ ሁለት አብነቶች በማቅረብ  ማስረዳት እፈልጋለሁ።
ባለፈው ሰሞን አብይ አሕመድ መቀሌ ላይ ባደረገው ንግግር የወልቃይትን የማንነት  ጥያቄ አሳንሶና ክዶ ተራ የውሃና የመንገድ ጉዳይ ሲያደርግ ኦሮሞው አብይ አሕመድ አማራን ስለሚጠላ ነው፣ የነስጠኛ ስርዓት አራማጅ  ነው በሚል በማንነቱ የከሰሰው  አልነበረም። አብይ አሕመድ ግን አማራ ቢሆን ኖሮና የውሃና የመንገድ ጉዳይ ያደረገው ከአማራ ውጭ የሆነን የማንነት ጥያቄ ቢሆን ኖሮ በማንነቱ ብቻ የነፍጠኛ ስርዓት አስቀጣይ፣ የድሮ ስርዓት አራማጅ፣ማንነታችንን ለማጥፋት አማራ ዛሬም አይተኛም፣ ጁነይዲ ሳዶ ናዝሬት ላይ  እንዳለው «ኢልሜን ቦፋ ቦፋደቴ» ወይንም «የእባብ ልጅ እባብ» እየተባለ መከራውን ይበላና  በብሔርተኛ ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች ጉባኤ ተጠርቶ «ኢልሜን ቦፋ ቦፋደቴ» የሚል  ይዘት ያላቸው  በርካታ ወረቀቶች ይቀርቡበት ነበር።
አንድም  የተረጋገጠ የታሪክ ምንጭ ሳይኖር በተገነባው የአኖሌ ሀውልት ዙሪያ ባህር ዳር ላይ የተነሱ ጥያቄዎችን አስመልክቶ በብሔርተኛ ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች  የተሰጠውን ግብረ መልስ አይተናል። ግብረ መልሶቹ በጠያቂዎቹ  ማንነት ላይ በማነጣጠር  «ቀድሞስ ከአማራ ምን ይጠበቃል» የሚሉ እንጂ የተነሳውን ጥያቄ በጥያቄነት ወስዶ በመመርመር  ለተነሳው ጥያቄ  የታሪክ ምንጭ  ማስረጃ አጣቅሰው  ለጥያቄው መልስ የሰጡ ብሔርተኛ ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች አላጋጠሙኝም። አብይ የማንነትን ጥያቄ ሲክድና ሲያሳንስ የማንነት ጥያቄ የማይነሳበት፤ አንድ የአማራ ተወላጅ ግን ጥያቄ ሲያነሳ በማንነቱ ብቻ የሚወገዝበት  የኢትዮጵያ ፖለቲካ ገጽታ ነው።
ሁለተኛ አብነት ባህር ዳር ላይ አሁንም  አብይ አሕመድ የተናገረውን የሚመለከት ነው። አብይ አሕመድ የአማራ ብሔርተኛነት አደገኛ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ተናግሯል። ለአብይ አሕመድ የብሔርተኛነት እንቅስቃሴ አደገኛ ደረጃ ላይ መድረሱ የታየው እንቅስቃሴውን  የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰዎች ስላቀነቀኑት  ብቻ ነው።  እንደሚታወቀው አብይ  አሕመድ  ቃለ መሀላ የፈጸመው «ሕገ መንግሥቱን» ለማስፈጸም ነው። ይህ ሕገ መንግሥት የብሔርተኛነት ሰነድ ነው። የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 ማንኛውም «ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝብ» ባሻው ጊዜ አገር የመመስረት መብት ያጎናጽፋል። ይህ የብሔርተኝነት እንቅስቃሴ ነው። አብይ አሕመድ ቃለ መሀላ የፈጸመው  የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 39 ለማስከበር ጭምር  ነው።
የብሔርተኛነት ፖለቲካ የማንቀሳቀሻ ሞተር የሆነውን አንቀጽ 39ኝን ለመጠበቅ ቃለ መሀላ የፈጸመ ጠቅላይ ሚንስትር የአማራ ብሔርተኝነትን ሊነቅፍ የሚያስችል የሞራ ልዕልና  የለውም። የብሔርተኛነት ፖለቲካ የማንቀሳቀሻ ሞተር የሆነውን አንቀጽ 39ኝን ለመጠበቅ ቃለ መሀላ የፈጸመ ጠቅላይ ሚንስትር የአማራ ብሔርተኝነትን አደገኛ ደረጃ ላይ መድረስ ከተቸ በእንግሊዝኛ አጠራር  double standard ነው አለያም ብሔተኝነት የሚባለው ነገር   ችግር ሆኖ   የታየው አማራ ብቻ  ሲያነሳው ነው ማለት ነው። ይህ ደግሞ  የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምን ያህል ከአማራ አንጻር ወይንም በጸረ አማራነት  እንደቆመ  የሚያሳይ ነው።
Filed in: Amharic