>

ለመቶ አመታት ይቆያል ተብሎ የተፎከርለት "እምበር ተጋዳላይ " የሻገተ አምባሻ ሆኖ ቀርቷል  (ቬሮኒካ መላኩ)

የቀጠናው ጂኦፖለቲካዊ ሁኔታ በፍጥነት እየተቀየረ ነው።  የአሜሪካ አፍሪካ ጉዳዮች ደስክ ሀላፊ  የሆነው Ambassador Donald Y. Yamamoto ኤርትራ ገብቷል።
 ኢትዮጵያ ውስጥ አብይ አህመድ ስልጣን ይዟል ።
አብይ  ካቢኔውንና  አንዳንድ ቁልፍ ቦታወችን በታማኞቹ አስይዟል።  ሱማሊያ ውስጥ ስልጣን የያዘው ወያኔን የሚጠላው  ፎርማጆ ነው።  የደቡብ ሱዳኑ ሳልቫ ኬርና  ከጅምሩም ቆሌው ከወያኔ ጋር አይገጥምም ።
ኬኒያ የፖለቲካውን አየር በማሽተት የሀይል ሚዛኑን ለክታ  በፍጥነት የምትሸበለል ስማርት አገር ነች።  ለመቶ አመታት ይቆያል እየተባለ ሲፎከርለት የነበረው “እምበር ተጋዳላይ ” የሻገተ አምባሻ ሆኖ ቀርቷል ።
የባድመ ነገር እያበቃለት ይመስላል ። ኢትዮጵያ አሁን ባድመን ሳትወድ  በግዷ በወርቅ ሰሀን አስቀምጣ ለኤርትራ መስጠቷ አይቀርም። ለወራት ተዳፍኖ የነበረው  ወልቃይትና ራያ የሚባል እሳትም ነፋስ አግኝቶት እየጋመ ነው። አማራ በርስቱና በሚስቱ ሰፋጣ እንደማያውቅ አፍሪካ ያረጋገጠው ሀቅ ነው። አማራ ሆይ ”  ጠጣሩ እንዲላላ በረገበው በኩል የላላውን ወጥር”  እንድል ባለቅኔው  አጀንዳህን ሁሉ ወልቃይትና ራያ ላይ ወጥር።
Filed in: Amharic