>

"በዘራችን እየተጠቃን ነው...ይህን ቀንበር መሸከም አንችልም" (መምህር ጌታ አስራደ)

          በ ጌታቸው ሽፈራው
” ማዕከላዊ ሲደበድበን የነበረ እና የተገዛ ምስክር ነው የመሰከረብን። እኛ የተከሰስነው በሀሰት ነው። መንግስት ሊገለብጡ ነው ተብለን ተከሰን አንዳችንም መሳርያ የለንም።  እኛ እየተጠቃን ያለነው በዘራችን ነው።
እውነት ፍትህ የምትሰጡ ቢሆን ማን እየዘረፈ እና እየመዘበረ እንዳለ ይታወቃል።  ማን እየሰረቀ እንዳለ፣ በዚህ ሀገር ወንጀለኛው ማን እንደሆነ ይታወቃል።  ቤተሰባችን ተበትኗል።    ተሰቃይተናል። አካላችን ተጎድቷል። ይህ ወንድማችን እጁ ተጎድቷል። ይህኛው ወንድማችን አንድ እጅ የለውም። (የተቆረጠውን እጁን እያነሳ)።  ልብስ ማጠብ እንኳ ስለማይችል ወደ እኛ ዞን እንዲመጣ ለምነን ነው የመጣ ው። ልብስ እንኳ የምናጥብለት እኛ ነን።  ማዕከላዊ ተገርፈናል። ፍትህ የማትሰጡን ከሆነ ልታሰናብቱን ይገባል። ይህን ሁሉ ቀንበር መሸከም አቅቶናል። በዘራችን ነው እየተጠቃን ያለነው። ፍትሕ እስካላገኘን ድረስ መጮሃችን እንቀጥላለን።” የጎንደር ዩኒቨርሲቲው መምህር ጌታ አስራዳ ዛሬ ሚያዝያ 16/2010 ዓም ለ19ኛ ወንጀል ችሎት የተናገረው
Filed in: Amharic