>
5:09 pm - Thursday March 3, 7408

ከተፈናቃዮች የጣር ድምጽ የሚሰማ የድረሱልን ጥሪ (ደምሰው ይላቅ)

ከቢሻንጉል ጉምዝ ክልል በግፍ ተፈናቅለው በባህርዳር ቀበሌ 11 አባይ ማዶ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ በፀጥታ ሀይሎች ታግተው ያሉ ወደ 1000 በላይ የሚሆኑ የአማራ ብሄር ተወላጆች እጅግ አሰቃቂ በሆነ አያያዝና ለእርሃብና እንግልት ተዳርገዋል።በዚህም የተነሳ
   1ኛ -ከከተማዋና አካባቢው ህብረተሰብ እንዳይጠይቃቸው  በፀጥታ ሰራተኞች በመከልከላቸው ለከፋ እርሃብ ጥምና ብርድ ተዳረገዋል።
    2ኛ -ሲርባቸውና ሲማረሩ ወደ ነበሩበት ክልል ይመለሳሉ በሚል የፀጥታ ሀይሎች ዛቻና ማዋከብ ይፈፅሙባቸዋል
     3ኛ -የተለያዩ የሚዲያ ሰዎችና ግለሰቦች አንዳያናግሯቸው በፀጥታ ሰዎች ተከልክለዋል።ተፈናቃዮችም መውጣትና መግባት አይችሉም።ተፈናቃዮችም። በአማራ ክልል መንግስትና የፀጥታ ሰራተኞች እንዲህ ሲያደርጉን በእነዚያማ ለምን እንፈርድባቸዋለን እያሉ ነው።በአጠቃላይ አሁን ያለንብት የስቃይ ህይወት እጅግ አስከፊ በመሆኑ እርሃብ ጥምና ብርድን መቋቋም አልቻልንም።ህይወታችን ከመጥፋቱ በፊት የባህርዳር ከተማና አካባቢ ነዋሪዎች:የሀይማኖት አባቶች:ይመለከተናል የሚሉ የመንግስት አካላት ይድረሱልን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
 (ስለተፈናቃይ ወገኖቻችን) – ቅዳሜ እኩለቀን 
ከድሮዉ ጎጃም መተከል (የአሁኑ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል) ተፈናቅለዉ ወደ ባህር ዳር ለአቤቱታ መጥተዉ የነበሩ የአማራ አርሶአደሮች 8 ተወካዮች ለአንድ ቀን በባህር ዳር ሁለተኛ ፓሊስ ጣቢያ ታስረዉ መለቀቃቸዉን ገልጸዉልናል፡፡ ይሄንን ህዝብ በትኑ ካልበተናችሁ ግን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት 6 ወር ትታሰራላችሁ ተብለዉ ነበር፡፡
ትላንት ማታ አባይ ማዶ ቴሌ ፊት ለፊት ከሰነበቱበት ግቢ የተባረሩ ሲሆን ወይ ወደ ቤንሻንጉል ክልል ተመለሱ ወይም ደግሞ አማራ ክልል ወደ ዘመዶቻቸሁ ተበተኑ ተብለዋል፡፡ እነርሱም ዘመዶቻችን እንኳን ለኛ ለነርሱም በቂ የርሻ መሬት የላቸዉም ብለዋል፡፡  ትላንት ሌሊት ያደሩበት የአባይ ማዶ ቅዱስ ገብርዔል ቤተ-ክርስቲያን አስተዳዳሪዎችም ዛሬ ደግመዉ እንዲያድሩ ከፈቀዳችሁላቸዉ ትጠየቃላችሁ ተብለዋል፡፡ የቀበሌ 11 ወጣቶች ዛሬ በገበያና በየሰፈሩ እየዞሩ ለወገኖቻችን ለምግብ የሚሆን ገንዘብ መዋጮ እየሰበሰቡ እንደሆነም ተረድተናል፡፡
የተወሰኑት ተፈናቃዮች በግዳጅ ወደ ፍኖተ ሰላም እንደተጫኑ ታዉቋል፡፡ የምዕ/ጎጃም ዞን መስተዳድርና ወረዳዎችም የናንተ ጉዳይ ከአቅማችን በላይ ነዉ ፤ ክልሉ መፍትሄ ካልሰጣችሁ እኛ ጋር እንዳትመጡ እንዳላቸዉ ገልጸዋል፡፡  የአቤቱታ ደብዳቤ ለጠ/ሚ/ር ጽ/ቤት አስገብተዉ በስልክ እየተከታተሉ ቢሆንም ጠ/ሚ/ሩ እስከአሁን ቢሮ አልገቡም ተብለዋል፡፡
ተወካዮችን ማግኘትና የአቅማችሁን መርዳት የምትፈልጉ በዉስጥ መስመር መልዕክት አስቀምጡልኝ፡፡
ፍትህና አስቸኳይ መፍትሄ ለተፈናቃይ ወገኖቻችን!
ዛሬም ከመተከል (ቤንሻንጉል ጉሙዝ) የተፈናቀሉ አማራ ወገኖቻችን ያለአንዳች መፍትሔ በአንድ ግቢ ውስጥ ታግተው አሉ:: ብአዴን ወደመጣችሁበት ተመለሱ ቢልም ከ3 ጊዜ በላይ ተመሳሳይ ችግር ስለገጠመን ከቤንሻንጉል መንግሥት ጋር ተነጋገሮ ዋስትና ካልሰጠን አንመለስም ብለዋል:: ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠዋል::
የአባይ ማዶ ሰፈር ሰዎች ምግብ ቢወስዱም ማስገባት ተከልክለዋል:: ወገኖቻችን ፈጣን መፍትሔ እየጠበቁ ነው:
Filed in: Amharic