>

የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሐላፊ ሆኖ የተመደበው ማነው???" (ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ)

የካቢኔ እና ሌሎች ወሳኝ ቦታዎች ምደባ የሚያመላክተው ህውሓት የፓርቲ (ፕሮፓጋንዳና ድርጅት) ስራ ቁልፍ ተግባር አድርጐ መውሰዱን ነው። በመንግስት ውስጥ የፓርቲ ስራ መስራት ወሳኝ የስራ ሂደት ሆኗል። በሌላ አነጋገር መንግስትንም ሆነ ባለስልጣናቱን ( ሚኒስትሮችን ጨምሮ) የሚመራው የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሐላፊው ይሆናል።
 እናም አሁን አንድ ጥያቄ እንድንጠይቅ እንገደዳለን፣
 ” ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ተስተካካይ አንዳንዴም የበዛ ስልጣን ያለው የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሐላፊ ሆኖ የተመደበው ማነው?”
#ማስታወሻ:- የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሐላፊ ስልጣንና ሐላፊነት በከፊል፣
  #1ኛ : የፓርቲውን የፕሮፐጋንዳ እና ድርጅት እቅድ ያወጣል፣ ያስፈፅማል። መንግስታዊ ተቋማትን ለርዕዬዓለማዊ ተግባር ያውላል።
   #2ኛ: በመንግስት ውስጥ የፓርቲ አመራር ይሰጣል። ( ፓርቲ አዛዥ፣ መንግስት ታዛዥ ይሆናል)። ፓሊሲ በማዘጋጀት ለመንግስት አስፈፃሚው ይሰጣል።
  #3ኛ:  መሪና ፈፃሚ የሆኑ ካድሬዎችን በመምረጥ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ይመድባል።
  #4ኛ:  የመንግስት አፈፃፀም ይቆጣጠራል። ተገቢውን እርምት ይወስዳል።
  #5ኛ: ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ወደ ቢሮክራሲያዊ ማእከላዊነት እንዳይለወጥ ጠንካራ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል። እርምጃ ይወስዳል።
                        ***
ከዘጠኝ ቀን በፊት የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ማነው/ማናት? ብዬ ጠይቄ ነበር። ዛሬ ሪፖርተር ምላሹን ሰጥቷል። ተጋዳሊት ፈትለወርቅ ( ሞንጆሪኖ) የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሆና በታስክ ፎርሱ ተሹማለች። ከዚህ በኃላ ፣
*  ፓርቲ መንግስትን እስከመራ ድረስ ( የካቢኔ ሹመቱ ይህን ስለሚያሳይ) መንግስት የሚመራበትን የፓርቲ እቅድ የምታወጣው እሷ ናት። ለፓለቲካ ሹመት የሚቀርቡ ሰዎች ለፓርቲው ሊቀመንበር ከመቅረባቸው በፊት የሚገመገሙት በእሷ ነው።
* የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል ከመሆኗም ባሻገር፣ ካቢኔው የሚወያይበትን ሰነድም ሆነ አዋጅ ፓለቲካዊ (ፓርቲያዊ) ትርጉም የምትሰጠው እሷ ናት።
* ከተቃዋሚ የፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ድርድር የምታደርገው እሷ ናት።
ማስታወሻ: ድሮና ዘንድሮ ይለያያሉ የሚል ክርክር ለምታነሱ ወዳጆቼ የግንባሩ መርህ የሆነው አብዬታዊ ዲሞክራሲና ማእከላዊነት ያልተለወጡ መሆኑን ልብ እንድትሉ እፈልጋለሁ። የድርጅት ጽህፈት ቤት ሓላፊ ቁልፍ ስልጣን እንዳለው ለማወቅ ደግሞ ለማና ዶክተር አቢይን ምሳሌ መውሰድ ትችላላችሁ። ለማ ፕሬዝዳንት ሲሆን ዶክተር አቢይ የፓርቲው ጽህፈት ቤት ሐላፊ ነበር።
Filed in: Amharic