>

የዶ/ር አብይ የእስር ማዘዣዋ ጉዳይ የገጽታ ግንባታ ወይስ??? (ዘውዱ ታደሰ) 

አቶ ለማ የጨፌ አባል ነው ዶ/ር አብይ የፓርላማ አባል እንደሆነ ይቷወቃል ይህ ማለት እነዚህ ሰወች ያለመከሰስ መብታቸው በህግ የተጠበቀ ነበር ማለት ነው ። ያለ መከሰስ መብታቸው በሸንጎው ሳይነሳ ማንም ሰው ሊነካቸው እንዳማይችል ማወቅ ያስፈልጋል  ። የእነዚህን ሰወች መብት በክልል ም/ቤት የአቶ ለማን ያለ መከሰስ መብት ለመግፈፍ ልሞክር ብትል እንካን አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ጨፌው 1 ድምፅም የድጋፍ ያወጣል ብዬ አላስብም እንደውም ለእንድዚህ አይነት ጉዳይ እሺ ብሎም ስብሰባብ አይቀመጥም ለማን አሳልፈው ይሰጣሉ ተብሎ ጭራሽ አይታሰብም ።
ዶ/ር አብይም የፓርላማ አባል እንካን ሆኖ ፓርላማው በህውሓት እጅ ነው ያለው ብንል እንካን ከ170 በላዩ የኦህዴድ አባላት ይቃወማሉ ብቻ ሳይሆን ስብሰባውን እረግጠው ሁሉ ሊወጡ እንደሚችሉ መገመት እንዴት ያቅተናል ። በዛን ቀውጢ ወቅት እንካን በቀናት በሰዓታት ውስጥ ምን ይፈጠራል ሀገሪቱ ውስጥ እየተባለ በተሰጋበት ሁኔታ ለማና አብይን ህውሓት ብታስር ኪሳራው ሚዛን ይደፍ ነበር ብዬ አምናለው ህውሓቶችም የህፃን ጫወታ ጭራሽ አይጫወቱም ። እንካን እነዚህን ሁለት ሚሊየን ደጋፊ ያላቸውን ሰዎችን አይደለም አንድ ሚ/ዲኤታ እንኲን ለማሰር ሙስና በሚል ተጠርጥሮ ሊታሰር ሲፈለግ በፓርላማው ያለመከሰስ መብቱ እዛው ቁጭ ባለበት እንደተነሳ አይተናል ለዚህም አቶ አለማየሁ ጉላጆ ሕያው ምስክር ናቸው ። ሰዎቹ በጣም እንዲታመኑ ዶ/ር አብይም ከህውሓት/ኢህአዴግ በተፃራሪ አቋም የቆመ ሰው ነው እንዲባል እና ከበሮ እንደ ሰሞኑ መደለቅ ስላቆመ ሌላው ስብዕና መገንቢያ እምነት ማሳደርያ ስልት ናት እኛ ደግሞ እንዳናምን ምንም ያየነው የተለየ የተጨበጠ ነገር የለም ንፋስ ብቻ ነው  ።
Filed in: Amharic