>
4:28 am - Thursday March 30, 2023

በህገወጥ መንገድ ዱከም ላይ የሚቸበቸበዉ የወሎ ኦፓል (ሚኪ አምሀራ)

የወሎ ኦፓል በአለም ቁጥር አንድ ኦፓል ነዉ፡፡ ከዚህ በፊት የአዉስትራሊያዉ ኦፓል ቁጥር አንድ ሁኖ ቢቆይም አሁን ግን ወገል ጠና የሚገኘዉ ኦፓል የአለም ገቢያን ተቆጣጥሮታል፡፡ አማራ ክልል ከሰሊጥ ቀጥሎ ትልቁ ወደ ዉጪ የሚላክ እቃ ነዉ፡፡ ነገር ግን ስለ ኦፓል ኤክስፖርት በዜናም ይሁን በማንኛዉም መንገድ ሰምተን አናዉቅም፡፡ ለምን ሚለዉን መልሱ ወዲህ ነዉ፡፡ በ 2015/16 በአለም የኦፓል ገቢያ ዉስጥ ኢትዮጵያ 28 ሺህ ኪሎ ግራም አቅርባለች፡፡ በ2012/13 14 ሺህ ኪሎ ግራም አቅርባለች፡፡ በ2013 የተቆረጠ እና ፖሊሽድ የሆነ የወሎ ኦፓል 100 ኪሎ ግራሙ 2.5 ሚሊየን ዶላር ተሽጧል፡፡ እንግዲህ 28 ሺህ ኪሎግራሙን በዚህ ስሌት ብናስበዉ በመቶ ሚሊየን ዶላር ወይም በ 10 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር አካባቢ ነዉ፡፡ ይህ ሪፖርት የአለም ባንክና የ አሜሪካ ጂኦሎጅግካል ሰርቬየ ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ግን ለዉጭ አቀረብኩት ያለዉ ኦፓል በ2012/13 4500 ኪሎ ግራም ነዉ፡፡ ሌላዉን 10ሽህ ኪሎግራሙን አላዉቅም ብሏል፡፡ ያ ማለት በህገወጥ መንገድ ነዉ የወጣዉ ማለት ነዉ፡፡
ነገሩ እንዲህ ነዉ የህወሃት ሀገወጥ ነጋዴወች የኦፓል ምርቱን ሰወችን ከአሜሪካ እና ከቻይና ድርስ በማስመጣት እዛዉ ወገል ጠና ላይ ሳይቀር ይሸጡታል፡፡ አዲስ አበባ ላይ ዱከም የቻይኖች የኢንዱስተሪ መንደር ዉስጥ አንዱ ትልቁ ህገወጥ ገቢያ የሚካሄድበት ቦታ ነዉ፡፡ የህወሃት ባለሃብቶችና በላስልጣኖች ከቻይናወች ጋር በመደራደር ይሸጡላቸዋል፡፡ ከዱከም የሚወጣ የኢንዱስተሪ ምርት ጋር ተቀላቅሎ የፋብሪካ ምርት ነዉ ተብሎ ይወጣል፡፡ ባንኮክ ሄዶ ኦፓሉ ምርመራ ይደረግለታል፡፡ ከዛም የቻይና እና ህንድ ገቢያ ይቀርባል፡፡ በዚህ መንገድ ህወሃትና ቻይና ተባብረዉ ስማግል አድርገዉ በየ አመቱ ከ 10 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ኦፓል ከሃገር ያወጣሉ፡፡ ይህ እንግዲህ ግብር እንዳይከፈልበት ይሆናል፤ ቆፍረዉ የሚያወጡ ገበሬወች ክፍያ አያገኙም፤ የአማራ ወጣት አይጠቀምም፡፡
ገበሬወችንና ወጣቶችን ሲያስቆፍሯቸዉ የሚዉሉት በደሞዝ ነዉ፡፡ ሙሉ ቀን ሲቆፍር እየዋለ በወር የሚያገኙት ከ 9መቶ እና አንድሽህ ብር አይበልጥም፡፡ የሚሸጠዉ ግን የት እየለሌ ነዉ፡፡ ለምሳሌ ከደላንታ የህወሃት ደላላ 20 ግራም ኦፓል በ 2500 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ) ብር ይገዛል፡፡ ዱከም ላይ ለቻይና ባለሃብቶች እንድ ግራም በ 4500 ብር ይሸጣል፡፡ ወገል ጠና ላይ በሁለት ሽህ አምስት መቶ የተገዛዉ 20 ግራም አዲስ አበባ ላይ ለቻይና ባለሃብት ወደ 90 ዘጠና ሺህ ብር ይሸጣል ማለት ነዉ፡፡ አለም ገቢያ ላይ ደግሞ ከ 10ሺህ ዶላር በላይ ይሸጣል፡፡
የአካባበዊ ወጣት እዳይጠቀም የህወሃት ቀማኞች መጀመሪያ ያደረጉት ኮምቦልቻ ኮሌጅ ዉስጥ ይሰጥ የነበረዉን ኦፓል እንዴት ማምረት እና እንዴት ተቆርጦ እንደሚሸጥ ይሰጥ የነበረዉን የኮሌጅ ስልጠና አስቆሙት፡፡ ለወጣቶቹ ብድር እንዳይሰጥና የኦፓል መቆፈሪያ ማሽኖችንና መቁረጫወችን ከቀረጥ ነጻ እንዳያስገቡ አደረጓቸዉ፡፡ ይህ የሆነዉ ገቢያዉን በራሳቸዉ ያስኬዱታል ብለዉ ስለፈሩ ነዉ፡፡ አሁን ወጣቱንና ገበሬዉን በመቆፈሪያ እና በባዴላ እጅግ ኋላ ቀር በሆነ መንገድ ሲያስቆፍሯቸዉ ይዉላሉ፡፡ ለወር ገቢ የማትሆን ገንዘብ ይከፈሏቸዋል፡፡ ወደ 3500 ገደማ ወጣቶች፡፡ የህወሃት ባለስለጣን ግን ሆቴልና ቪላ ሰሩበት፡፡ በሄሊኮፍተር ሁሉ ወገል ጠና ድረስ እየመጡ በዚህ መልኩ ነዉ ስማግል የሚያደርጉት፡፡ በአንጻሩ የወሎ ወጣት ይሄ ሃብት እያለ ስደት እና እንግልት ላይ ነዉ፡፡ ወገል ጠና በቢሊየን ብር በየአመቱ እየሰጠች አንዲት የረባ ሆስፒታል እንኳን የላትም፡፡ የገበሬዉ መሬት ያለካሳ ይነጠቃል፡፡ ብአዴን በነገራችን ላይ ይሄን አያዉቅም፡፡ ኦፓል ምንድን ነዉ ብትለዉ እራሱ ዉሃ ጠርጎ ያመጣዉ አሽዋ ነዉ የሚለዉ፡፡ በርግጥ በረከት ያዉቃል፡፡ የቅርብ ዘመዱ ወይም ወንድሙ በቢዝነሱ ስላለበት፡፡
መፍትሄዉ
——–
ማሽኑን ወጣቶች በነጻ እንዲያስገቡ እና ያመረቱትን ምርት እዚሁ ባህርዳር ላይ እራሳቸዉ አለም አቀፍ ጨረታ እያዘጋጁ እንዲሸጡ፡፡ወጣቶቹና ገበሬዎቹ ተደራጅተዉ እንዲሰሩ ብድር መፍቀድ፤ የኮምቦልጀቻ ቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠናዉን እንዲጀምር፡፡ እያንዳንዷ ግራም ኦፓል ተቆጥራ ለክልሉና ለአካባቢዉ ህዝብ ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ እንዲመቻች፡፡እኒህን ኮንትሮባንዲስቶች ወጣቱ እራሱ አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ ማጥፋት አለበት ከዛ አካባቢ፡፡ በሰላም ካልወጣ እርምጃ መዉሰድ ነዉ፡፡
ምስሉ ላይ ምታዩት ወጣት እንዲህ ሲቆፍር ዉሎ የቀን ገቢዉ ከ 1 ዶላር በታች ነዉ፡፡ ከድህነት ወለል በታች ማለት ነዉ፡፡ ነገር ግን የምታዩት ምርት አንዷ እንክብል ኦፓል ብቻ በአስር ሺዎች የምትሸጥ ናት፡፡ከዚህም በላይ ለጤና እና ደህንነት አደጋ የተጋለጠ ነዉ፡፡ ያለምንም መከላከያ ነዉ ማእድን እየቆፈረ ያለዉ፡፡
CC/ ANDM CC office ANRS Communication Affairs Office North Wollo RayaKobo Communication Office
Filed in: Amharic