>

"መንግስት የማይቀበለው ባንዲራ ይዘው መፈክሮችን ስለሚያሰሙ እንዳልጠየቅ ብዬ ነው የተለየሁት " (ኦቦ በቀለ ገርባ)

ጋዜጠኛ መልካም ሰላም ሞላ ኦቦ በቀለ ገርባ በኦሮምኛ ተናግረውታል የተባለውን ማብራሪያ የአማርኛ ትርጉም አቅርባለች።
ኦቦ በቀለ፣ 
“ዛሬ ኦቦ በቀለ ገርባ ለምን አቀባበል እንዳልተደረገላቸው ለOMN በሰጡት ቃለ መጠይቅ ግልፅ አድርገውታል
ኦሮምኛ ለማትችሉ ትርጉሙን እነሆ
ለኔና ለእስክንድር ነጋ ትልቅ አቀባበል ሊያደርጉልን እንደነበረ ቀድመው ነግረውን ነበር ይሁን እንጂ እኔ እንደዚህ አይነት አቀባበል ነግሬያቸው ነበር ምክኒያቱም ይመጣሉ ተብለው የተነገሩን በሺዎች የሚቆጠሩ እንደሆኑ ነው እነዚህ ሰዎች ሲመጡ ደግሞ መንግስትየማይቀበለውን ባንዲራዎች ይዘው ሊመጡ ይችላሉ በዛ ላይ የተለያዩ መፈክሮችን ቢያሰሙ እኔ እንደዛ አይነት በመገኘቴ ሊያስጠይቀኝ ይችላል ብዬ በመስጋቴ ነው በዛ ላይ ነገ ወደ ኢትዮጵያ መመለሴ አይቀርም ባለው ህግ ስር ስለምተዳደር ያኔ ደግሞ ሊያስጠይቀኝ ይችላል ከማለት ስጋት ተነስቼ ነው በዛ ላይ ውስጤ ያላመነበትን ነገር ሃላፊነት ውስጄ ችግር ውስጥ መግባት ስላልፈለኩ ነው ለዛ ነው እንጂ ስለ እውነት ትልቅ አቀባበል ሊደረግልን ታስቦ ስልክ ራሱ ለብዙ ጊዜ ነበር የተደወለልን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሊቀበሉን እንደተዘጋጁና ከመቶ በላይ መኪኖች እንደተዘጋጁ ነግረውን ነበር ነገር ግን እኔ ነኝ እንደማልፈልግ የነገርኳቸው ይህንንም የወሰንኩት በራሴ ነው ይሁን እንጂ የኛ ሰዎ የምገባበትን ሰአት የሚያውቁ አቀባበል አድርገውልኛል እኔም ከዛ በላይ አልፈልግም ነበር ስላዘጋጁልኝም አቀባበል በጣም አመስግኜ በራሴ ፍላጎት እንደቀረሁ ላሳውቅ እወዳለሁ”
Filed in: Amharic