>

ህወሀት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ መዶሎቱ ተጋለጠ!!!

 ነኣምን ዘለቀ
እንደ አስተማማኝ የውስጥ ምንጫችን መረጃ የህወሃት አባል የሆኑ ባለስልጣናትና ባለሃብቶች ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እንዲደረግ እየወተወቱ እንደሚገኙ ታወቀ!!
አዲሱ ጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር አቢይ አህመድ ወደ ጠቅላይ ሚንስተርነት ቦታው በህዝብ ትግል ከወጡ ጀመሮ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ካድሪዎች፣ ወታደራዊ መኮንኖች እንዲሁም ዘራፊ ባለሃብቶች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መዘፈቃቸውን በየጊዜው ከህወሃት መንደር አፈትልከው የሚወጡ መረጃዎች በመጠቆም ላይ ናቸው።
በዶ/ር አቢይ አህመድ የጠቅላይ ሚኒስተርነት ስልጣን ስጋት የገባቸው እነኝህ ህወህታዊያን በጠቅላይ ሚንስተሩ አስተዳደር ላይ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት መደረግ አለብት እያሉ እየወተወቱ እንደሚገኙ ታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አቢይ አህመድ በተለይ በባለፈው ወር በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል ባለሃብቶችን ሰብስበው ሌብነትንና ዘረፋን አምርረን መዋጋት አለብን ሲሉ መደመጣቸውን ተከትሎ፣ የሃገሪቱን ሃብት እንደልባቸው ሲዘርፉ የነበሩ የህወሃት ባለሃብቶች በአደባባይ ተሰደብን እያሉ እደሚገኙ የመረጃ ምጮቻችን ጠቁመዋል።አክለውም እንዳሉት እነኝህ ዘራፊ ባለሃብት ተብየዎች <<#አንዱ_ለፊ #ሌላው_ዘራፊ>> በማለት ጠቅላይ ሚኒስተሩ በተደጋጋሚ በእየ መድረኩ የአገሪቱ የኢኮኖሚ ስርዓት ምን ያክል መዛባቱን በማመላከታቸው የተነሳ ህወሃታውያኖቹ <<እንዴት እንዲህ በአደባባይ ይዘልፈናል፣ እኛ እኮ ለዚህ የበቃነው ለ17 ዓመታት የወገኖቻችን ደምና አጥንት ገበረን፣ደርግን ጥለን ነው>> በማለት ያዙኝ ልቀቁኝ እያሉ ይገኛሉ ተብሏል።
በዚህም ምክንያት የህወሃት ባለሃብቶች በጠቅላይ ሚኒስተሩ ላይ ጥርስ ነክሰውባቸው እንደሚገኙ ከደረሱን መረጃዎች ለመረዳት ተችሏል።በሆኑም ባለሃብቶቹ በጠቅላይ ሚኒስተሩ ላይ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እንዲደረግ አጥብቀው እየወተወቱ ነው ተብሏል።
ሌላው ደግሞ የህወሃት ካድሪዎች ጠቅላይ ሚኒስተሩ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፍልስፍና የወጣ፣እታይ እታይ ባይ፣ ህወሃትን ከህዝብ ጋር ለመለየት እየጣረ የሚገኝ፣የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ወደኋላ የገፋ፣ከቡድን መብት ይልቅ የገለሰቦችን መብት ለማስቀደም እየጣረ ያለ ጠቅላይ ሚንስተር እንዴት የህወሃት/ኢህደግን ልማታዊ አስተሳሰብ ሊያስቀጥል ይችላል? የሚል ፕርፖጋንዳ በመንዛት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣በተጨማሪም እነኝህ የህወሃት ካድሪዎች ጠቅላይ ሚኒስተሩ ከአቢዮታዊ ዴሞክራሲ ይልቅ ወደ ሊብራል አስተሳሰብ ጭልጥ ብሎ ገብቷል። ስለዚህ አቢዮታዊ ዴሞክ ራሲ እየተሸረሸረ ነው፣በአስቸኳይ ይህ ይህን ጠቅላይ ሚኒስተር ማስቆም ካላችልን ስርዓታችን አደጋ ላይ ነው።
እናም ሰውየን ማስቆም የምንችለውም በአፋጣኝ ወታደራዊ መፈንቅለ ምንግስት ሲደረግ ብቻ ነው ሲሉ ሰሞኑን በተለያዩ የተግራይ ክልል ከተሞች በተካሄዱ ሚስጥራዊ ስብሰባዎች ላይ ሃሳባቸውን ማንጸባረቃቸውን ወስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃዎች አመላክተዋል።
በአጠቃላይ በዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣትና ከመጡም በኋላም በዚህ አንድ ወር ውስጥ ባከናወኗቸው፣በተለይም በየመድረኩ ኢትዮጵያዊነትን አበክረው በመስበካቸው የተነሳ፣ በዚህም ህወሃት በኢትዮጵያ ላይ ላለፉት 43 ዓመታት የፈጠረውን የቅጥፈት ትርክት ለመናድ በመጣራቸው ምክንያት፣ ጠቅላይ ሚንስተሩ በህወሃት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣በካድሪዎች፣ በባለሃብቶቹ ብቻ ሳይሆን በህወሃት የጦር አበጋዞችም ጭምር የመረረ ጥላቻ እንዲገጥማቸው ሆነዋል።
እነኝህ የህወሃት የጦር አበጋዞች በፌድራል መንግስት የህወሃት ሰዎች ተገፍተዋል፣በመረጃና ድህንነት መስሪያቤቱም ግፊቱን እየታዘብን ነው፣ ይህ የመገፋት ሂደት ወደ መከላከያ ሰራዊቱም ዘልቆ ይመጣል ስለዚ ከአሁኑ መላ ሊዘየድለት ይገባል እያሉ ናቸው።
መላ ይሆናሉ ከተባሉት መካከል የህወሃት የጦር አበጋዞች የእራሳቸውን ህገ-መንግስት ፍጹም በተጻረረ መልኩ ጠቅላይ ሚኒስተሩ በመከላከያሰራዊቱ ውስጥ ሃላፊነት እናዳይኖረው ማድረግ፣ ስለመከላከያሰራዊቱ የተመለከት ማንኛውም ሪፖርት እንዳይርሰው ማስቻል፣ይህ ካልተሳካ ድግሞ ወታደራዊ መፈንቅለመንግስት ማካሄድ ምርጫ የለለው አማራጭ ነው ማለታቸው ተነግሯል።
ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከህወሃት አባል ውጭ በሆኑ አንዳንድ ከፈትኛ መኮንኖች ሳይቀር ለህወሃት ምቾት የማይሰጡ ጥያቄዎች መነሳታቸውን ተከትሎ፣ በተለይ ተራው መከላከያ ሰራዊት ለህወሃት የጦር አበጋዞች አንታዘዝም የሚሉ ስሜቶች እየተንጸባረቁና እየተስፋፉ በመምጣታቸው ምክንያት መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ይቻላል ወይ የሚለው ጉዳይ፣በአንዳንድ የህወሃት የጦር አበጋዞች ያልተመለሰ ጥያቄ ሆኗል ተብሏል።
Leaked News አፈትላኪ ዜናዎች!!
Filed in: Amharic