
ከታች የታተመው በወያኔዋ ኢትዮጵያ በአማራ ላይ የታወጀ ግልፍ የዘር ማጥፋት እልቂት አዋጅ ነው። አማሮች የዘር ማጥፋት እልቂት የታወጀባቸው በሚኖሩበት ጎጃም መተከል ውስጥ ነው። እስከ ሚያዝያ 10/8/2010 ዓ.ም. ካልወጣችሁ እንፈጃችኋለን ተብለዋል። በጥቅምት ወር የተፈናቀሉት ባህር ዳር መጠጊያ አጥተው እየተንገላቱ መሆኑን ከሰሞኑ ልባችንን ሲያደማ የሰነበረ ገሃድ ነው።
«ቤንሻንጉል ክልል» በሚባለው ክልል ውስጥ የነውረኛው ብአዴን ወኪል ነኝ ባዩ ግለሰብ ትናንትና በቴሌቭዥን ቀርቦ እንደተናገረው «ባህር ዳር የሚገኙት የመተከል ተፈናቃዮች በጥቅምት ወር የተፈናቀሉ ናቸው፤ ከዚያ በኋላ ግን ሁኔታው ተረጋግቶ ችግሩ በሰላም ተፈቷል» ብሎን ነበር። ከታች የታተመው በአማራ ላይ የታወጀ መንግሥታዊ የዘር ማጥፋት አዋጅ የተሰራጨው ግን መጋቢት 16/2010 በተፃፈ ደብዳቤ ነው። ነውረኛው ብአዴን ይህንን ያህል ነው ከአማራ ጉዳይ የራቀ የፋሽስት ወያኔ ጉዳይ ፈጻሚ የሆነው።
በአማራ ላይ የታወጀ መንግሥታዊ የዘር ማጥፋት እልቂት ትዕዛዝ እነሆ፤
______________________________ ___
የበሎ ዴዴሣ ቀበሌ መስተዳደር
ዴዴሣ
ቀን 16/7/2010 ዓም
ማሳሰቢያ: ለበሎ ዴዴሣ የአማራ ነዋሪዎች በሙሉ
ይኸውም የአማራ ተወላጆች ለሆናችሁ በሙሉ እስከ መጋቢት 30/7/2010 ዓ.ም. ድረስ ወይም እስከ ሚያዝያ 10/8/2010 ዓ.ም. ሀብታችሁን ሆነ ንብረታችሁን ሽጣችሁ ሆነ አርዳችሁ የማትወጡ ከሆነ ግን በሕግ ተገዳችሁ እየታሰራችሁ ወዳችሁ ሳይሆን በግድ ተገዳችሁ በሕግ የምትወጡ መሆኑን እስከተሰጠው ጊዜ ገደብ ካልወጣችሁ በሚደርስባችሁ ችግር የቀበሌው መስተዳደር ተጠያቂ አለመሆኑን በዚህ ደብዳቤ መግለፃችን እናስታውቃለን።
ተያያዥነት ያለው መረጃ
የአማራ ብሄርተኝነትን ማን ፈጠረው?
ዳንኤል ተፈራ
የአማራ ብሄርተኝነት እንዲሥፋፋ ያደረገው ዋና ጉዳይ ምንድን ነው? የአማራን ብሄርተኝነትን የፈጠረው ማነው? ለምን? መልሡ ከባድ አይደለም። የፈጠረው ግፍ ነው። በደል። አማራን መሥደብ ለባለፉት 25 ዓመታት የፖለቲካ አፍ መፍቻ ነበር። አማራን ማፈናቀል ፋሽን ይመሥል ነበር። ሥልጣን ያሰጥ ነበር። የሥነልቡና ጦርነቱ አሠልቺ ነበር።

የሚታየው ነገር ምንድን ነው? ይሄን የፃፈው መንግሥት አምኖበት ማህተም የተቀበለ ሹም ነው ወይሥ ማን??? እኔ ለዚህ ደብዳቤ ማብራሪያ የምጠይቀው ሹሙን አደለም። መግሥትን ነው።